በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ቴሊ ጌታን ታገለግላለች


‘’ቴሊ ጌታን ታገለግላለች’፣ ’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ቴሊ ጌታን ታገለግላለች፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሚያዝያ 1844–መጋቢት 1852 (እ.አ.አ)

ቴሊ ጌታን ታገለግላለች

ቤተክርስቲያኗን በቱቡዋይ መገንባት

ቴሊ እና ሌሎች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሚሲዮናውያን ሲደርሱ ሲመለከቱ።

ቴሊ የተባለች ሴት ቱቡዋይ በተባለች በአንዲት ትንሽ ደሴት ውስጥ ትኖር ነበር። የተለያዩ ቤተክርስቲያናት ሚስዮናውያን አንዳንድ ጊዜ ቱቡዋይን ጎብኝተዋታል፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ብዙ አይቆዩባትም ነበር። በ1844 ዓ.ም (እ.አ.አ)፣ አንድ ቀን ቴሊ ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሚስዮናውያን ወደ ቱቡዋይ መምጣታቸውን በሰማች ጊዜ ተደሰተች።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥1; 133፥8

ቴሊ እና ናቦታ ሚስዮናውያን ከእነርሱ ጋር እንዲቀመጡ ጋበዟቸው።

ሚስዮናውያኑ ወደተወሰኑ ትልልቅ ደሴቶች እየሄዱ ነበር። ነገር ግን በቱቡዋይ የነበሩ ህዝቦች እንዲቆዩ እና ወንጌልን እንዲያስተምሩ ፈለጓቸው። ቴሊ እና ባለቤቷ፣ ናቦታ፣ ሚስዮናውያን በቤታቸው መኖር እንደሚችሉ ነገሯቸው። ከሚስዮናውያን አንዱ፣ አዲሰን ፕራት፣ ለዚሁ ተስማማ።

ቅዱሳን1፥573–74

ቴሊ እና ናቦታ ከሚስዮናውያን ከአንዱ ጋር ምግብን በጋራ እየበሉ።

ቴሊ እና ናቦታ ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ ለአዲሰን አካፈሉ። የእነርሱን ቋንቋ እንዲናገርም አስተማሩት። አዲሰን ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተማራቸው።

ናቦታ እያየ ሳለ ቴሊ ስትጠመቅ።

መንፈስ ቅዱስ የአዳኙ ወንጌል እውነት እንደሆነ ለቴሊ እና ለናቦታ ነገራቸው። እነርሱ በቱቡዋይ የተጠመቁ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ናቸው።

ቅዱሳን1፥573–74

ቴሊ እና ሌሎች በቱቡዋይ ላሉ ህዝቦች ወንጌልን ሲያካፍሉ።

ቴሊ፣ ናቦታ እና አዲሰን የልብ ጓደኞች ሆኑ። አብረው ይጓዙ ነበር እናም በቱቡዋይ እና ሌሎች ደሴቶች ወንጌልን አስተማሩ። በቱቡዋይ ያሉ ሰዎች ለቅዱሳን በቤተክርስቲያኗ ባይቀላቀሉ ይሻል ነበር በሚሏቸው ጊዜ፣ ቴሊ ከቅዱሳት መጻህፍት እየጠቀሰች ቤተክርስቲያኗ እውነት እንደሆነች ታስተምር ነበር።

ቅዱሳን2፥2745

ቴሊ፣ ናቦታ እና ሌሎች ቅዱሳን በአንድነት ሲዘምሩ።

ብዙ ሰዎች በቱቡዋይ ወንጌልን እንዲማሩ ቴሊ ለመርዳት ትፈልግ ነበር። ምሽት በሆነ ጊዜ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን ወደ መዝሙር በመቀየር ብዛት ያላቸው ሰዎች ከእርስዋ ጋር እንዲዘምሩ ትጋብዝ ነበር። የቴሊን መዝሙሮች መዘመር ለብዙ ሰዎች ቅዱሳት መጻህፍትን እንዲማሩ እና የተማሩትን እንዲያስታውሱ ረድቷቸዋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥12

ቴሊ እና ቤተሰቧ ለአዲሰን ቤተሰብ አቀባበል ሰያደርጉ።

ከዓመታት በኋላ፣ የአዲሰንን ቤተሰብ ጨምሮ፣ ብዙ ሚስዮናውያን ወደ ቱቡዋይ መጡ። ቴሊ በቤቷ ተቀበለቻቸው። እርስዋ የቱቡዋይ ሴቶችን ለማገልገል፣ ከአዲሰን ባለቤት፣ ከሉዊዛ ጋር ሰራች።

ቅዱሳን2፥133–34

ቴሊ እና ቤተሰቧ ከሌሎች ጋር ወንጌልን ማካፈል ቀጠሉ።

ከጊዜ በኋላ፣ ሚስዮናውያን ቱቡዋይን እና ሌሎች ደሴቶችን ለቀው እንዲወጡ ተገደዱ። ነገር ግን ቴሊ ቅዱሳንን ማስተማሯን እና መምራቷን ቀጠለች። በቴሊ ምሳሌነት እና አገልግሎት ምክንያት፣ ቤተክርስቲያኗ በቱቡዋይ ጠንካራ ሆና ቀጥላለች።

ቅዱሳን2፥150–51