“የፈውስ ቀን፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የፈውስ ቀን፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ሚያዝያ–ሐምሌ 1839 (እ.አ.አ)
የፈውስ ቀን
በእግዚአብሔር ሃይል ህሙማንን መባረክ
ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች በምዙሪ ታስረው እያለ፣ አንዳንድ ጠባቂዎች ወደ ሌላ እስር ቤት ወሰዷቸው። ጠባቂዎቹ ለእስረኞቹ ደጎች ነበሩ። አንድ ሌሊት፣ የጠባቂዎቹ መሪ ሊተኛ እንደሆነ፣ እና ጆሴፍ እና ጓደኞቹ አምልጠው ቢሄዱ ሊያቆማቸው እንደማይችል ለጆሴፍ ነገረው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥392–93
ጆሴፍ እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች አመለጡ። ቤተሰቦቻቸው ክውንሲ በሚባል ከተማ ውስጥ እየኖሩ አገኟቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥395–96
በክውንሲ ያሉ ሰዎች ለቅዱሳን ደጎች ነበሩ። ለቅዱሳን ምግብ እና ልብስ እናም መጠለያ ሰጧቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥377
ቅዱሳን በክውንሲ ያሉ ህዝቦች ላሳዩት ደግነት ምስጋናን አቅርበዋል። ነገር ግን ጆሴፍ የራሳቸው የሆነ የመኖሪያ ስፍራ እንደሚያስፈልጋቸው አውቋል። የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ሌላ ማንም ሰው የማይፈልገውን የተወሰነ መሬት ገዙ፣ እና ቅዱሳንም ወደዚያ ተዛወሩ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥399–400
መሬቱም በአንድ ትልቅ ወንዝ አጠገብ ነበር። እርጥበታማ እና ጭቃማ እና ትንኝ የሞላበት ነበር። ትንኞቹ አብዛኞቹን ቅዱሳን ወባ በተባለ በሽታ በጣም በሽተኛ አድርገዋቸው ነበር። አንዳንዶቹ ሞቱ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥402
ጆሴፍ ብዙ ሰዎች እንደታመሙ ባየ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ መሪዎችን ሰበሰበ እና ከእርሱ ጋር እንዲመጡ ጠየቀ። በጠዋቱ ጊዜ በሙሉ፣ ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ፣ ህመምተኞችን ሲጎበኙ እና ሰባርኩ ዋሉ። ህመማቸውንም ለመፈወስ የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይል ተጠቀሙ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥402
አንድ የጎበኙት ሰው ኢላይጃ ፎርድሃም ይባል ነበር። በጣም ታሞ ነበር፣ ባለቤቱም በቅርቡ የሚሞት መስሏት ነበር። ጆሴፍ ኢላይጃን እንዲፈወስ እምነት እንዳለው ጠየቀው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥402
ኢላይጃም፣ ‘’በጣም የረፈደ ነው ብዬ ፈርቻለሁ።’’ ጆሴፍ ኢላይጃን በኢየሱስ ክርስቶስ ያምን እንደሆነ ጠየቀው። ‘’አምናለሁ፣ ወንድም ጆሴፍ፣’’ በማለት መለሰለት።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥402
ጆሴፍም እርሱን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ባረከው። ኢላይጃ ተነሳ። ኢየሱስም ፈወሰው! ኢላይጃ ጆሴፍን እስከሚቀጥለው ቤት ድረስ ተከተለው እና ሌሎች ሰዎችን በመባረክም ረዳው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥402–3