በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት


“የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])

“የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት፣’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታኮች

ታህሳስ 1832–መጋቢት 1836 (እ.አ.አ)

የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት

ለጌታ የተለየ ቤት

ጆሴፍ እና ኤማ ስሚዝ እና ፊብ እና ስድኒ ሪግደን የከርትላንድ ቤተመቅደስ የሚገነባበትን ስፍራ ሲመለከቱ።

ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ቅዱሳን በከርትላንድ የተለየ ቤት የሚገነቡበት ጊዜው እንደሆነ ነገረው። ይህም ቤት ፣ ጌታ ህዝቡን የሚጎበኝበት እና ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን የሚገባበት ቤተመቅደስ ይሆናል። በቤተመቅደሱ ውስጥም ልዩ ስጦታን ይሰጣቸዋል። ስጦታውንም የመንፈስ ሃይል ስጦታ ብሎታል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥11995፥8Saints [ቅዱሳን]1፥205

ሀይረም ስሚዝ በቤተመቅደስ ስራ ለመርዳት ሲሄድ።

ቅዱሳን ቤተመቅደስ የመገንባቱን ስራ ወዲያው አልጀመሩም። ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ጌታ ቤተመቅደሱ በጣም አስፈላጊ እንደነበር አስታወሳቸው። ሀይረም ስሚዝ መሳሪያዎችን ለማሰባሰብ ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አመራ። እናቱም ወዴት እንደሚሄድ በጠየቀችው ጊዜ፣ በጌታ ቤት ስራ ላይ የመጀመሪያው መሆን እንደሚፈልግ ተናገረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥1–8

ስድኒ ሪግደን ቤተመቅደሱ እየተሰራ እያለ ሲመለከት።

በከርትላንድ ያሉ ቅዱሳን ቤተመቅደሱን መስራት ጀምረዋል። ብዙ የገንዘብ ወጪ አስከትሏል እና ብዙ ስራም ጠይቋል፡፡ እንደ ስድኒ ሪግደን ያሉ የቤተክርስቲያን አባላት ቤተመቅደሱን ለመስራት ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋል። የጌታን ትእዛዛት ለመከተል እና በቤቱም የእርሱን በረከቶች ለመቀበል ደስተኞች ነበሩ።

Saints [ቅዱሳን]1፥209–211

ስድኒ ለቤተመቅደሱ ስራ እርዳታን ለማግኘት ሲጸልይ።

ቅዱሳን ቤተመቅደሱን እየሰሩ እያሉ፣ የገንዘብ እጥረት ገጠማቸው። ስድኒ እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ተጨንቀው ነበር። ስድኒ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Saints [ቅዱሳን]1፥210–11

ኬሮሊን ቲፔትስ እርዳታ ለመስጠት እየደረሰች።

የቤተክርስቲያኗ አባላት ኬሮላይን ቲፔትስ የተባለች እና ቤተሰቦችዋ ብዙ ገንዘብ ቆጥበው ነበር። ኬሮላይን ቤተመቅደሱ እንዲሰራ ለመርዳት ቤተክርስቲያኗ ገንዘቡን እንድትበደር አደረገች።

Saints [ቅዱሳን]1፥211–13

ልጆች የተሰባበሩ መስተዎቶችን በማሰባሰብ ሲያግዙ

በከርትላንድ የነበሩ ብዙ ቅዱሳን ቤተመቅደሱን ለመስራት ረድተዋል። አንዳንዶች በድንጋዮች የተሞሉ ጋሪዎችን ወደ ቤተመቅደሱ ይነዱ ነበር። ሌሎች ለሰራተኞች አልባሳትን እና ምግብን ይሰሩ ነበር። ልጆችም የቤተመቅደስ ግድግዳዎችን ለመሞረድ እና ለማልበስ በዚህም እንዲያንጸባርቁ እና በጸሀይ ብርሃን እንዲያበሩ ስብርባሪ ብርጭቆዎችን ያሰባስቡ ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥210219221

የከርትላንድ ቤተመቅደስ ተጠናቀቀ።

ሳይቆይም የከርትላንድ ቤተመቅደስ ተጠናቀቀ! እርሱ ተስፋ የገባላቸውን በረከቶች ለመቀበል ቅዱሳን ወደ ጌታ ቤት ለመሄዳድ ደስተኞች ነበሩ።

Saints [ቅዱሳን]1፥221