በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ፓርሊ በካናዳ የሠጠው የሚስዮን አገልግሎት


“ፓርሊ በካናዳ የሠጠው የሚስዮን አገልግሎት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ፓርሊ በካናዳ የሠጠው የሚስዮን አገልግሎት” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሚያዝያ–ሰኔ 1836 (እ.አ.አ)

ፓርሊ በካናዳ የሠጠው የሚስዮን አገልግሎት

በጌታቃል ኪዳኖች ላይ ያለንን እምነት ማሳየት

የቤተክርስቲያን መሪዎች በከርትላንድ ቤተመቅደስ አቅራቢያ የእግር ጉዞ ሲያደርጉ።

የከርትላንድ ቤተመቅደስ ከተመረቀ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ወንጌልን ለመስበክ በሚስዮን አገልግሎት ሄዱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥81109፥22–23112፥28–29Saints [ቅዱሳን]1፥249

ፓርሊ ፕራት በባለቤቱ አልጋ አጠገብ ተቀምጦ።

ፓርሊ ፕራት ወንጌልን ማካፈል ይወድ ነበር። ነገር ግን ታንክፉል የተባለች ባለቤቱ ህመም ታምማ ስለነበረች በቤት መቆየት እንዳለበት ተሰማው። በተጨማሪም በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥249

ሂበር ኪምባል ፓርሊን እና ታንክፉልን ሲባርክ።

ሂበር ኪምባል፣ የፓርሊ ጓደኛ እና ከሐዋርያት አንዱ ለጉብኙት መጣ። እርሱ ለፓርሊ ቡራኬን ሰጠው እና በካናዳ ውስጥ ወንጌልን መስበክ እንዳለበት ተናገረ። በቡራኬውም ውስጥ፣ ታንክፉል ደህና እንደምትሆን ሒበር ቃል ገባ። ወንድ ልጅም እንደምትወልድ እና ጌታም ፓርሊ ፕራት የሚያስፈልገውን ገንዘብ እንዲያገኝ እንደሚረዳው ቃል ገባ።

Saints [ቅዱሳን]1፥249–50

ፓርሊ ታንክፉልን ሲሰናበት።

ታንክፉል እና ፓርሊ በትዳር ለ10 አመታት አብረው ቆይተዋል። ምንም ልጆች አልነበሯቸውም ነበር። ነገር ግን በጌታ የተስፋ ቃሎች ላይ እምነት ነበራቸው። ምንም እንኳ ከታንክፉል ርቆ በካናዳ መቆየት ከባድ ቢሆንበትም፣ ፓርሊ ወንጌልን ለማካፈል ሄደ።

Saints [ቅዱሳን]1፥250

ፓርሊ በካናዳ የሚስዮን አገልግሎቱ ላይ።

በካናዳ ውስጥ፣ ፓርሊ ሰዎችን ሊያስተምር የሚችልበትን ስፍራ ይፈልግ ነበር። በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እና በሌሎች ህንጻዎች ውስጥ ማስተማር ይችል እንደሆነ ጠየቀ። ሁሉም ሰው አይሆንም አለው።

Saints [ቅዱሳን]1፥252–53

ፓርሊ ጆንን እና ሌዮኖራ ቴይለርን ሲተዋወቃቸው።

ከዚያም ፓርሊ ጆንን እና ሌዮኖራ ቴይለርን ተዋወቃቸው። ኢየሱስ ክርስቶስን እና መጽሐፍ ቅዱስን ይወዳሉ። ጆን ፓርሊን ያስተማረው ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ልዩነት ያለው እንደሆነ ጠየቀው።

Saints [ቅዱሳን]1፥252–53

ፓርሊ እና ጆን ሲነጋገሩ።

ፓርሊ ስለኢየሱስ፣ ስለነቢያት፣ ስለጥምቀት፣ እና ስለመንፈስ ቅዱስ እንዳስተማረ ተናገረ። እናም እነዚህ ነገሮች በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነበሩ። ጆንም እንዲህ ሲል ጠየቀ፣ ‘’ስለ ጆሴፍ ስሚዝ እና ስለ መጽሐፈ ሞርሞንስ?’’ ፓርሊ ለጆን መጽሐፈ ሞርሞን እንደ መጽሀፍ ቅዱስ እውነት እንደሆነ እና ጆሴፍ ስሚዝም የእግዚአብሔር ነቢይ እንደነበር ነገረው።

Saints [ቅዱሳን]1፥253

ፓርሊ የተሰበሰቡ የቅዱሳንን ቡድን ሲያስተምር።

ጆን ፓርሊ የተናገረውን አመነ። መፅሐፈ ሞርሞንን አነበበ እና እውነት መሆኑንም አወቀ። ጆን እና ሌዮኖራ ጓደኞቻቸውን ጆሴፍን፣ መርሲን፣ እና ሜሪ ፊልዲንግን እና ሌሎችን ፓርሊ ሲያስተምር እንዲሰሙ ጋበዟቸው። ብዙ ሰዎች ተጠመቁ እናም በቤተክርስቲያኗ ተቀላቀሉ፡፡

Saints [ቅዱሳን]1፥254–55

ፓርሊ በካናዳ ያሉ ጓደኞቹን ሲሰናበት።

ፓርሊ ደስተኛ ነበር፣ ነገር ግን ወደ ቤቱ ወደ ታንክፉል መሄድ ፈለገ። በካናዳ ውስጥ ያሉ አዲስ ጓደኞቹን ተሰናበተ። እጃቸውን እየጨበጠ በነበረ ጊዜ፣ ቤተሰቦቹን ይንከባከብበት ዘንድ ለመርዳት ገንዘብ ሰጡት።

Saints [ቅዱሳን]1፥255–56

ፓርሊ እና ታንክፉል አብረው በካናዳ።

ፓርሊ ወደቤቱ ሲመለስ፣ ታንክፉል እጅግ የተሽሏት ሆና አገኛት። ፓርሊ ተጨማሪ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎችን ያዘ እና ወንጌልን ለማካፈል ወደ ካናዳ ተመለሰ። በዚህ ጊዜ፣ ታንክፉል አብራው ሄደች።

Saints [ቅዱሳን]1፥256

ፓርሊ እና ታንክፉል ሲተቃቀፉ።

ወዲያውኑ ታንክፉል እና ፓርሊ ልጅ እንደሚኖራቸው ተገነዘቡ። ሂበር ለፓርሊ የሰጠውን ቡራኬ አስታወሱ። በዚያ ቡራኬ ወቅት ጌታ ቃል የገባው በሙሉ የተፈጸሙ እንደሆኑ ተሰማቸው።

Saints [ቅዱሳን]1፥256