በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ናቩን ለቅቆ ወደ ምእራብ መሄድ


“ናቩን ለቅቆ ወደ ምእራብ መሄድ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ናቩን ለቅቆ ወደ ምእራብ መሄድ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሰኔ 1844–ሐምሌ 1847 (እ.አ.አ)

ናቩን ለቅቆ ወደ ምእራብ መሄድ

ቅዱሳን ለጌታ ቃል ይገባሉ እና የገቡትንም ቃል ይጠብቃሉ

ብሪገም ያንግ የናቩን ቤተመቅደስ መጠናቀቅ ሲቆጣጠሩ።

ጆሴፍ ስሚዝ ሞተ። አሁን ብሪገም ያንግ እና ሌሎች ሐዋርያት ቤተክርስቲያኗን ይመሩ ነበር። ብሪገም ያንግ ቅዱሳን ከዚህ በኋላ በናቩ ውስጥ ደህንነት እንደማይሰማቸው አውቀው ነበር። መሄድ ነበረባቸው። ነገር ግን በመጀመሪያ፣ ጌታ የቤተመቅደሱን ግንባታ እንዲያጠናቅቁ ፈልጓል። እነርሱ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ እና እንደቤተሰብ እንዲተሳሰሩ ፈልጓል።

ቅዱሳን1፥571579–80

ብሪገም ቅዱሳን በቤተመቅደስ ውስጥ ቡራኬን እንዲቀበሉ እየረዷቸው።

ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ሰዎች በዚያ ቃል ኪዳንን እንዲያደርጉ ቤተመቅደሱ ዝግጁ ሆነ። በሺዎች የሚቆጠሩ ቅዱሳን ወደ ቤተመቅደሱ መጡ። ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያገቡ ለመርዳት ብሪገም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በቤተመቅደስ ውስጥ ቆይተው ነበር። በመጨረሻም፣ እያንዳንዱ ሰው ናቩን ለቅቆ መሄድ እንዳለበት ብሪገም ተናገሩ።

ቅዱሳን1፥582

ብሪገም ቅዱሳን ናቩን ለቅቀው መሄድ እንዳለባቸው ተናገሩ።

ብሪገም በሚቀጥለው ጠዋት ሲነቁ፣ የበለጠ ቁጥር ያላቸው ቅዱሳን በቤተመቅደስ እየተጠባበቁ ነበር። ብሪገም እነርሱ በናቩ መቆየታቸው መልካም እንዳልሆነ ነገራቸው። በምእራብ ውስጥ አዲስ ቤት መፈለግ ነበረባቸው። እዚያም በደረሱ ጊዜ አዲስ ቤተመቅደስ መስራት እንደሚችሉ ቃል ገቡላቸው።

ቅዱሳን1፥582–832፥13–14

ቅዱሳን በቤተመቅደስ ቡራኬን ለመቀበል ብሪገምን ተማጸኑት።

ነገር ግን ቅዱሳኑ ከዚያ አልሄዱም። ወደ አዲሱ ቤታቸው ለመሄድ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ከጌታ ጋር ቃል ኪዳንን ማድረግ ፈልገዋል።

ቅዱሳን1፥583

ብሪገም ቅዱሳን በቤተመቅደስ ውስጥ ቡራኬን እንዲቀበሉ መርዳትን ቀጠሉ።

ብሪገም ፊቶቻቸውን ተመለከቱ እናም ሃሳባቸውን ቀየሩ። ቀሪውን የቀኑን ጊዜ አሳለፈው እናም በሚቀጥለው ቀን፣ ቅዱሳን በቤተመቅደስ ቃል ኪዳን ለማድረግ እንዲችሉ ረዷቸው።

ቅዱሳን1፥583

ቅዱሳን ናቩን ትተው ሲሄዱ እና ወደ ምእራብ ጉዞን ሲጀምሩ።

አሁን ቅዱሳን ከጌታ ጋር ቃል ኪዳንን ገብተዋል፣ ናቩን የመልቀቅ ጊዜ አሁን ነበር። ጌታ ለእነርሱ ስፍራን እንዳዘጋጀላቸው ብሪገም አውቀዋል። ይህንንም በራእይ ተመልክተዋል። እነርሱም ጉዞአቸውን ጀመሩ። የአየሩ ሁኔታ ቀዝቃዛ ነበር፣ እና መሬቱም ጭቃማ ነበር። ህዝቡም ታመሙ። በዚህ ጊዜ ምግብ አልቆባቸው ነበር።

ቅዱሳን2፥16–1820–21

ብሪገም እና ሌሎች በበረዶአማው ካምፕ ውስጥ እየኖሩ።

ቅዱሳን ገና ረዥም መንገድ ይቀራቸው ነበር። ብሪገም ይህ አይነቱን ረዥም እና ከባድ ጉዞ እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ በማሰብ ግራ ተጋቡ። ከእግዚአብሔር እርዳታን በመፈለግ ጸለዩ።

ቅዱሳን2፥46

ቅዱሳን በዊንተር ኳርተርስ እርስ በርሳቸው ይደጋገፉ ነበር።

ጌታ ለብሪገም ራእይን ሰጣቸው። ቅዱሳንን እንዴት መምራት እንዳለባቸው ለብሪገም አስተማረ። እርሱም እርስ በርሳቸው ተረዳዱ እና ድሆችንም ደግፉ አሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥1–8

ቅዱሳን ጉዞአቸውን በጸደይ ወደ ምእራብ ቀጠሉ።

ጌታም ቅዱሳን ከእርሱ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ማስታወስ እንዳለባቸው ተናገረ። ይህንንም ቢያደርጉ፣ እንደሚባርካቸው እና በመንገዳቸው ሁሉ እንደሚረዳቸው ተናገረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥4፣ 11፣ 42ቅዱሳን2፥47

አንድ ቤተሰብ ከመቃብር አጠገብ ተንበርክኮ።

አሁንም ጉዞው በጣም ከባድ ነበር። አንዳንድ ሰዎችም ሞቱ። ነገር ግን በቤተመቅደሱ ቃል ኪዳናቸው ምክንያት፣ ቅዱሳን የቤተሰብ አባሎቻችውን ዳግም እንደሚያገኟቸው አውቀዋል።

ዊልፎርድ ዉድሩፍ እና ብሪገም ያንግ በሶልት ሌክ ሸለቆ ሲደርሱ።

ከጥቂት ወራት በኋላ፣ የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን በ1847 (እ.አ.አ) ወደሶልት ሌክ ሸለቆ ደርሰዋል። ብሪገም ያንግ ሸለቆውንም እንዳዩ “ይህ ትክክለኛው ቦታ ነው” በማለት ተናገሩ። በራእይ ከተመለከቱት ጋር ተመሳሳይ ስፍራ ነበር። ይህ ቅዱሳን ደህንነት የሚሰማቸው ስፍራ ነበር። በዚህ ጌታን ሊያመልኩት እና ስራውንም በሰላም ሊሰሩ ይችላሉ።

ቅዱሳን2፥1764–67

በአለም ዙሪያ ያሉ ቤተመቅደሶች እና የቅዱሳን ውህደት።

በዓመታት መካከል፣፣ ብዙ ቅዱሳን ወደዚህ ደርሰዋል። እነርሱም ሰዎች ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን የሚገቡባቸውን ሌሎች ብዙ ቤተመቅደሶችንም ገንብተዋል። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማስተማር በዓለም ዙሪያ ሚስዮናውያንን ልከዋል። በየስፍራው የሰማይ አባት ልጆችን እየባረከች፣ የአዳኙ ቤተክርስቲያን ማደጓን ቀጥላለች።