በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢላይጃ ኤብል


“ኢላይጃ ኤብል፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ኢላይጃ ኤብል፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1838 (እ.አ.አ)

ኢላይጃ ኤብል

የእምነት እና የብርታት ሚስዮን

ኤላይጃ ኤብል ኤኒስ ፍራንክሊንን ሲያጠምቅ።

ጌታ ኢላይጃ ኤብል የተባለን ሰው ሚስዮናዊ እንዲሆን ጠራው። ኢላይጃ ዩኒስ እና ቻርልስ ፍራንክሊንን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አስተማራቸው። ስለ መፅሐፈ ሞርሞን እና ስለ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ነገራቸው። ዩኒስ እና ቻርልስ እርሱ ያስተማረውን አመኑ እና በቤተክርስቲያኗ መቀላቀል ፈለጉ። ኢላጃ አጠመቃቸው።

Saints [ቅዱሳን]1፥316

ኢላይጃ ህልም እያየ።

ኢላይጃ በሌላ ከተማ ወንጌልን ለማካፈል ሄደ። በአንድ ሌሊት፣ ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ስለ ጓደኛው ዩነስ ህልም አየ። በህልሙም፣ ዩኒስ ከዚህ በኋላ መጽሐፈ ሞርሞን እውነት ስለመሆኑም ሆነ ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ ስለመሆኑ እርግጠኛ አልነበረችም። ኢላይጃ ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ ስለ ዩኒስ ለማረጋገጥ ወዲያውኑ ተመለሰ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥27Saints [ቅዱሳን]1፥315–16

ኢላይጃ ከዩኒስ ጋር ሲነጋገር።

ዩኒስ ኢላይጃን በበሯ ስላየችው ተገረመች! የኢላጃ ህልም እውነት ነበር፤ ዩኒስ ከዚህ በኋላ በመጽሐፈ ሞርሞንም ሆነ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አላመነችም ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥317

ኢላይጃ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ሲሰብክ።

ኢላጃ በትምህርት ቤት ውስጥ ሲሰብክ እንድትሰማው ዩኒስን ጠየቃት። የኢላጃን ቃላት በሰማች ጊዜ፣ እንደገና መንፈስ ቅዱስ ተሰማት። ወንጌልም እውነት እንደነበር አወቀች።

Saints [ቅዱሳን]1፥317

ኢላይጃ ከትምህርት ቤቱ ውጪ ሰዎችን ሲያነጋግር።

ኢላይጃ ከሁለት ሳምንታት በኋላ እንደገና ለመስበክ እንደሚመለስ ለዩኒስ ቃል ገባላት። ነገር ግን በከተማው የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ዳግም ተመልሶ እንዲመጣ አልፈለጉም ነበር። ኢላይጃ ከሄደ በኋላ፣ ለእያንዳንዱ ሰው ኢላይጃ ሰዎችን እንደገደለ መናገር ጀመሩ። ለሚያገኘው ሰው ወሮታውን እንደሚከፍሉ ተናገሩ።፣

Saints [ቅዱሳን]1፥318

ዩኒስ በከተማው ከነበሩ ሰዎች ጋር ስትከራከር።

ዪኒስ ሰዎቹ ስለኢላይጃ የሚናገሩት ነገር ሀሰት እንደነበር ታውቅ ነበር። እርሱ ማንንም አልገደለም። እርሱ መልካም ሰው እና የእግዚአብሔር አገልጋይ ነበር። የእነርሱ ሀሰት ኢላይጃን ተመልሶ በመምጣት ከመስበክ እንደማያስቆመው አውቃለች። ዩኒስ ለሰዎቹ ኢላይጃ ደግሞ እንደሚመለስ ተናገረች፡፡ ‘’እግዚአብሔር እርሱን ይጠብቀዋል፣’’ በማለት ተናገረች።

Saints [ቅዱሳን]1፥318

ኢላይጃ ወደ ትምህርት ቤቱ ሲመለስ።

ኢላይጃ ተመለሰ። ከዚህ በፊት ወደ ሰበከበት ወደዚያው ትምህርት ቤት መጣ። እንዲታሰር በሚፈልጉ ሰዎች ተሞልቶ ነበር። ኢላይጃ ከህዝቡ ፊት ቆመ። እርሱም ሊያስሩት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት፣ አሁን ማድረግ እንዳለባቸው ተናገረ። ካልሆነም፣ እንዲያስተምር እንዲተዉት ነገራቸው።

Saints [ቅዱሳን]1፥318

ሰዎቹም ኢላይጃ ሲያስተምር በእርሱ ላይ አተኩረው።

ማንም አልተንቀሳቀሰም። ኢላይጃ ጠበቀ፣ ነገር ግን ህዝቡ በጸጥታ ተቀመጡ። ኢላይጃ መዝሙር ዘመረ፣ ጸሎት አደረገ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አስተማረ። የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር ነበር፡፡ ማስተማሩን ከጨረሰ በኋላ፣ ከጓደኞቹ ከዩኒስ እና ቻርልስ ጋር ተነጋገረ እና የሚስዮኑን አገልግሎቱን በሰላም ቀጠለ።

Saints [ቅዱሳን]1፥319