“የዴዚዴሪያ ህልም፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የዴዚዴሪያ ህልም፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1880–1886 (እ.አ.አ)
የዴዚዴሪያ ህልም
በሜክሲኮ ውስጥ በጌታ መመራት
ዴዚዴሪያ በናፓላ፣ ሜክሲኮ ውስጥ ትኖር ነበር። በአንድ ሌሊት፣ ዴዚዴሪያ በሜክሲኮ ከተማ ውስጥ እየተሰራ ስላለ አንድ ትንሽ መጽሐፍ ህልም አየች። እርሱም ይሰኝ የነበረው Voz de amonestación፣ ወይም የማስጠንቀቂያ ድምጽ ነበር። ዴዚዴሪያ በነቃች ጊዜ፣ ያንን መጽሐፍ ማግኘት እንደነበረባት አወቀች።
ቅዱሳን፣ 2፥477
ነገር ግን የሜክሲኮ ከተማ ሩቅ ስለነበር የዚህ አይነቱን ረዥም ጉዞ ለማድረግ የዴዚዴሪያ እድሜ በጣም የገፋ ነበር። እርስዋም ያንን መጽሐፍ ፈልጋ እንድታገኝ ጌታ የሚፈልግ መሆኑ ተሰማት። በመሆኑም ለልጇ፣ ለሆሴ፣ ስለህልሙ ነገረችው። መጽሀፉ አስፈላጊ የነበረ መሆኑንም ጭምር አመነች። እርሱም ፈልጎ እንደሚያገኝላት ለእናቱ ነገራት።
ቅዱሳን፣ 2፥478
ሆሴ በሜክሲኮ ከተማ በደረሰ ጊዜ፣ መንገዶቹ የተጨናነቁ፣ ድምጽ የበዛባቸው እና በህዝብ የተሞሉ ነበሩ። እንደዚህ ባለ በህዝብ በተጨናነቀ ስፍራ ውስጥ መጽሐፉን እንዴት ሊያገኝ ይችላል?
ቅዱሳን፣ 2፥478
ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ሆሴ ጄምስ ስቲዋርት የተባለን ሚስዮናዊ አገኘ። ጄምስ አንድን መጽሐፍ ለማሳተም በመስራት ላይ እንደሆነ እና መጽሐፉም Voz de amonestación [የማስጠንቀቂያ ድምጽ] እንደሚሰኝ ተናገረ።
ቅዱሳን፣ 2፥478
ሆሴ በጣም ተደስቶ ነበር! ስለ እናቱ ህልም ለጄምስ ነገረው። ጄምስም ሚስዮናውያን Voz de amonestación [የማስጠንቀቂያ ድምጽ]ን በመጠቀም ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና መፅሐፈ ሞርሞን ስለተባለው አዲስ ቅዱስ መጽሐፍ ለህዝቡ ለማስተማር እንደሚችሉ ገለጸለት።
ቅዱሳን፣ 2፥478
Voz de amonestación [የማስጠንቀቂያ ድምጽ] እስካሁን አላለቀም ነበር፣ እናም መፅሐፈ ሞርሞንም ወደ ስፓኒኛ ቋንቋ አልተተረጎመም ነበር። ነገር ግን እርሱን እና እናቱን ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለመፅሐፈ ሞርሞን፣ እና ዳግም ስለተመለሰችው ቤተክርስቲያን ለመማር እንዲረዳቸው፣ ጄምስ ለሆሴ ሌሎች መጽሀፍትን እና ወረቀቶችን ሰጠው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥11፤ ቅዱሳን፣ 2፥478–79
ሆሴ እናቱን ለማግኘት ወደ ቤቱ በፍጥነት ሄደ። አብረውም ወንጌልን አጠኑ፣ እና እውነት እንደነበር አወቁ። ዴዚዴሪያ ሚስዮናውያን መጥተው እንዲያጠምቋት ጠየቀች።
ቅዱሳን፣ 2፥479
ዴዚዴሪያ በሜክሲኮ ውስጥ በመጀመሪያ ከተጠመቁት ሴቶች እንዷ ነበረች። ሆሴ እና ሴት ልጁም እንዲሁ ተጠምቀዋል።
ቅዱሳን፣ 2፥479
Voz de amonestación [የማስጠንቀቂያ ድምጽ] መታተሙ ሲፈጸምም፣ ሆሴ በኖፓላ ከሌሎች ጋር ለመካፈል አስር ቅጂዎችን ለእናቱ ለመስጠት አገኘ። ከዓመታት በኋላ፣ መፅሐፈ ሞርሞን በመጨረሻ በስፓኒኛ ቋንቋ ሲታተም፣ ዴዚዴሪያ በሜክሲኮ ውስጥ ይህንን ለማግኘት የመጀመሪያዋ ግለሰብ ነበረች። እርስዋም ጌታ ዳግም ወደተመለሰው ቤተክርስቲያኑ እንደመራት አውቃለች።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥81፤ ቅዱሳን፣ 2፥479