“ምስክሮች የመፅሐፈ ሞርሞንን ሰሌዳዎች ተመለከቱ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])
“ምስክሮች የመፅሐፈ ሞርሞንን ሰለዳዎች ተመለከቱ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
መጋቢት–መስከረም 1829 (እ.አ.አ)
ምስክሮች የመፅሐፈ ሞርሞንን ሰሌዳዎች ተመለከቱ
ምስክርነትን ለአለም መስጠት
ጆሴፍ፣ ኤማ እና ኦሊቨር ፔንስልቬንያ በሚገኘው የስሚዝ ቤተሠብ ቤትውስጥ የወርቅ ሰሌዳዎቹን መተርጎማቸውን ቀጠሉ። ሆኖም በከተማቸው የነበሩ ሰዎች ሊያስቆሟቸው ፈለጉ። ኦሊቨር በኒው ዮርክ የሚኖር ዴቪድ ዊትመር የሚባል ጓደኛ ነበረው። ኦሊቨር፣ ትርጉሙን መጨረስ እንዲችሉ ወደ ዊትመር ቤተሰብ ቤት መዛወር ይችሉ እንደሆነ ዴቪድን ጠየቀው።
ቅዱሳን፣ 1፥68
ዴቪድና ቤተሰቡ ተስማሙ። ለጆሴፍ፣ ለኤማ እና ለኦሊቨር በቤታቸው አቀባበል አደረጉላቸው። አሁን የትርጉሙን ሥራ በሰላም ሊያከናውኑ ይችላሉ። በዊትመር ቤተሰብ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ያ ማለት በተለይ የዴቪድ እናት ሜሪ ብዙ የሚሠራ ሥራ ነበረባት።
ቅዱሳን፣ 1፥68–70።
አንድ ቀን፣ ሜሪ እየሰራች ሳለች፣ መልአኩ ሞሮኒ ጎበኛት። ተጨማሪ ሥራው እንደሚያደክማት እንደሚያውቅ ተናገረ። እምነቷን ሊያጠናክርላት ፈለገ። አንድ ቦርሳ ከፍቶ የወርቅ ሰሌዳዎቹን አወጣቸው። ገጾቹን ገለጣቸውና ጽሑፉን ለሜሪ አሳያት። ሜሪ እንደምትባረክ ቃል ገባላት።
ቅዱሳን፣ 1፥70–71።
አንዳንድ ሰዎች ሰሌዳዎቹ የእውነት ስለመሆናቸው አላመኑም ነበር። ሳህኖቹን ለማንም እንዳያሳይ የሠጠውን የጌታን ትዕዛዝ ታዝዞ ነበር። ጌታ፣ ተጨማሪ ሶስት ምስክሮች ሰሌዳዎቹን እንዲያዩ እንደሚፈቅድ ተናገረ፡፡ ዴቪድ ዊትመር፣ ማርቲን ሃሪስ እና ኦሊቨር ካውድሪ ምስክሮች መሆን ይችሉ እንደሆነ ጥያቄ አቀረቡ። ጌታም ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናገረ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥11–12፤ 17፤ ቅዱሳን፣ 1–73
ጆሴፍ፣ ማርቲን፣ ኦሊቨር እና ዴቪድ ወደ ጫካ ሄዱ። ተንበርክከው ሰሌዳዎቹን ማየት ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔርን በየተራ ጠየቁ ሆኖም ምንም ነገር አልሆነም ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥73
ማርቲን ሃሪስ ጸሎታቸው እየተመለሰ ያልነበረው በእርሱ ምክንያት እንደሆነ ተሰምቶት ነበር። ማርቲን ትቶ ሄደ፣ ሌሎቹ ግን መጸለያቸውን ቀጠሉ።
ቅዱሳን፣ 1፥73
ከዚያም አንድ መልአክ በደማቅ ብርሃን ውስጥ ታየ። የወርቅ ሰሌዳዎቹን እና በላያቸው ላይ ያለውን ጽሑፍ ለኦሊቨር እና ለዴቪድ አሳያቸው። ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን በእግዚአብሔር ኃይል እንደተረጎማቸው እና ትርጉሙም ትክክል እንደሆነ የእግዚአብሔር ድምፅ ሲናገር ሰሙ። እግዚአብሔርም ያዩትን እና የሰሙትን ለሁሉም ተናገሩ አላቸው።
“የሶስቱ ምስክሮች ምስክርነት”፤ ቅዱሳን፣ 1፥73–74
ጆሴፍ ማርቲንን ለመፈለግ ሄደ። አሁንም እየፀለየ ነበር። ጆሴፍ አብሮት ፀለየ። ከዚያም መልአኩ ተገለጠና ለኦሊቨር እና ለዴቪድ እንዳደረገው ሰሌዳዎቹን ለማርቲን አሳየው።
ቅዱሳን፣ 1፥74
ከዚያም፣ ጆሴፍ ሜሪ ዊትመርን እየጎበኙ የነበሩትን ወላጆቹን ለማግኘት ሄደ። ሌሎች ሰዎች ሰሌዳዎቹን በማየታቸው ምን ያህል እንደተደሰተ ነገራቸው። አሁን ምስክሮቹ ጆሴፍ እውነቱን እየተናገረ እንደነበረ ለሰዎች ለመንገር ቻሉ። ማርቲን፣ እግዚአብሔር ከምሥክሮቹ አንዱ እንዲሆን ስለፈቀደለት ምን ያህል እንደተደሰተ ለሁሉም ተናገረ።
ቅዱሳን፣ 1፥74–75።
ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ጌታ፣ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ለተጨማሪ ስምንት ሰዎች እንዲያሳይ ለጆሴፍ ነገረው—እነርሱም አባቱ፣ ሁለት ወንድሞቹ፣ የዴቪድ አራት ወንድሞች እና የዴቪድ ሚስት ወንድም ነበሩ። ሰሌዳዎቹን ያዙ እንዲሁም ገፆቹን ገለጡ። ሰሌዳዎቹ እውነተኛ መሆናቸውን አወቁ።
“የሶስቱ ምስክሮች ምስክርነት”፤ ቅዱሳን፣ 1–75
አሁን የመጽሐፈ ሞርሞን ትርጉም ተጠናቋል። ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ለመልዓኩ ሞሮኒ መልሶ ሰጠው። አሁን፣ ሁሉም ሰው አንብቦ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ያውቅ ዘንድ የመጽሐፉን ቅጂዎች የማተም ጊዜ ነው።
ቅዱሳን፣ 1፥75–76።
መፅሐፈ ሞርሞንን ማሣተም ብዙ ወጪ ጠይቋል፡፡ ማርቲን ሃሪስ ክፍያውን ለመፈፀም የእርሻውን የተወሰነ ክፍል ሠጠ። ይህንን ያደረገው መፅሐፈ ሞርሞን እውነት መሆኑን ስላወቀ ነበር። ሁሉም ያነበው ዘንድ እያንዳንዱ የመጽሐፉ ቅጂ የማርቲን እና የሌሎች ምስክሮች ምስክርነት አለበት። ምስክሮቹ የሠጧቸውን ምስክርነት በፍጹም አልካዱም።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥26–27፣ 34–35፤ ቅዱሳን፣ 1፥76–78