“የያናጊዳ ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የያናጊዳ ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1950–1951 (እ.አ.አ)
የያናጊዳ ቤተሰብ
አስራት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን
ቶሺኮ እና ቶኪቺ ያናጊዳ በጃፓን ይኖሩ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በእርሱ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ሕይወት በጃፓን ውስጥ አስቸጋሪ ነበር። ጦርነት ብዙ ቤቶችን እና ሕንፃዎችን አውድሞ ነበር። ቶሺኮ እና ቶኪቺ ለቤተሰባቸው ቤት መገንባት ፈልገው ነበር፣ ነገር ግን በጣም ድሆች ነበሩ።
ቅዱሳን፣ 3፥543
የያናጊዳ ቤተሰብ ጌታ አስራት እንዲከፍሉ እንደሚፈልግ ያውቁ ነበር፣ ነገር ግን ይህን ለማድረግ እንደሚችሉ እርግጠኞች አልነበሩም። ቶሺኮ አንድን ሚስዮናዊውን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠየቀ። “አሥራት መክፈል ለእኛ በጣም ከባድ ነው” አለች። ሚስዮናዊው አስራት ከከፈሉ ቤት የመግዛት ግባቸው ላይ እንዲደርሱ ጌታ እንደሚረዳቸው ቃል ገባላቸው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119፤ ቅዱሳን፣ 3፥543–44
ቶሺኮ እና ቶኪቺ እርግጠኞች አልነበሩም። ለልጃቸው የትምህርት ቤት ምሳ እንኳን የሚገዙበት በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም። ነገር ግን በጌታ በመታመን አሥራትን ለመክፈል ወሰኑ።
ቅዱሳን፣ 3፥543–44።
ጌታ የያናጊዳ ቤተሰብን ባረከ። ብዙም ሳይቆይ መሬት ገዝተው ቤት መገንባት ጀመሩ።
ቅዱሳን፣ 3፥544
አንድ ቀን አንድ ተቆጣጣሪ መጣ። በመሬታቸው ላይ ችግር እንዳለ እና በእዚያ ቦታ ቤት መሥራት እንደማይችሉ ነገራቸው። ሰራተኞቹም እንዳይገነቡ አስቆማቸው።
ቅዱሳን፣ 3፥544
የያናጊዳ ቤተሰብ በጣም አዘኑ። የሆነውን ሁሉ ለሚስዮኖች ነገሩ። ሚስዮኖች ከያናጊዳ ቤተሰብ ጋር እንደሚጾሙ እና እንደሚጸልዩ ተናገሩ።
ቅዱሳን፣ 3፥545
በኋላ ሌላ ተቆጣጣሪ መጣ። በመሬታቸው ላይ ያለው ችግር ሊስተካከል ይችላል አለ። የያናጊዳ ቤተሰብ ቤታቸውን መገንባት ይችላሉ። ተቆጣጣሪው ቶሺኮ እና ቶኪቺን “ሁለታችሁ ጥሩ ነገር አድርጋችሁ መሆን አለበት” አላቸው። እነርሱ ጌታ እንደባረካቸው አወቁ። በእርሱ ታምነው አሥራት በመክፈላቸው ተደሰቱ።
ቅዱሳን፣ 3፥545