በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሲድኒ እና ፊቢ ሪግደን


“ሲድኒ እና ፊቢ ሪግደን፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ሲድኒ እና ፊቢ ሪግደን፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ጥቅምት–ህዳር 1830 (እ.አ.አ)

ሲድኒ እና ፊቢ ሪግደን

ወንጌልን ለመቀበል ሕይወታቸውን መለወጥ

ፓርሊ ፕራት ጓደኛውን ስድኒን እንዲጎበኙ ለጓደኞቹ ሐሳብ አቀረበ።

ፓርሊ ፕራት እና ሌሎች ለጥንታዊ አሜሪካውያን ወንጌልን ሊያካፍሉ እየሄዱ ነበር። በመንገዳቸው ላይ፣ ፓርሊ ጓደኛውን ስድኒ ሪግደንን ለመጎብኘት ቆም ለማለት ፈለገ። ሲድኒ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፓርሊ ያስተማረው ሰባኪ ነበር። አሁን ፓርሊ ሲድኒን ከመፅሐፈ ሞርሞን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያስተምረው ፈለገ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 32ቅዱሳን1–99

ፓርሊ መጽሐፈ ሞርሞንን ለሲድኒ ሪግደን እያካፈለ።

ፓርሊ፣ ስለመጽሐፈ ሞርሞን ለሲድኒ ነገረው እንዲሁም እንዲያነበው ጋበዘው። ሲድኒ እርግጠኛ አልነበረም፣ ሆኖም ፓርሊ ጓደኛው ስለነበረ እንደሚያነበው ቃል ገባ።

ቅዱሳን1፥100

ሲድኒ መፅሐፈ ሞርሞንን እያነበበ፤ እንዲሁም ለሚስቱ እያካፈለ።

ሲዲኒ መፅሐፈ ሞርሞንን ባነበበው ጊዜ ከእግዚአብሔር የመጣ እንደሆነ አመነ። ስሜቱን ለሚስቱ ለፊቢ አካፈለ።

ቅዱሳን1፥101

ሲድኒ ከቤተሠቡ ጋር እየተነጋገረ።

ሆኖም ሲድኒ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንደነበረበት እርግጠኛ አልነበረም። ከተጠመቀ በእርሡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የሰባኪነት ስራውን ያጣል። ፊቢን እና ስድስት ልጆቻቸውን እንዴት መንከባከብ ይችላል? በእርሡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ይሰማቸዋል? እርዳታ ለማግኘት ወደ ሰማይ አባት ጸለየ፣ ከዚያም ሠላማዊ ሥሜት ተሠማው።

ቅዱሳን1:101ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥23

ፊቢ ሪግደን ቤተክርስቲያኗን ለመቀላቀል ፈቃደኛ እንደሆነች ለሲድኒ እየተናገረች።

ሲድኒ፣ የተደላደለ ኑሯቸውን ለመተው እና ይህን አዲስ ቤተክርስቲያን ከእርሱ ጋር ለመቀላቀል ፈቃደኛ ስለመሆኗ ፊቢን ጠየቃት። “የእኔ ፍላጎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ነው፣ ሞት ወይም ሽረት ቢሆንም” አለች። ለመጠመቅ ወሠኑ።

ቅዱሳን1፥101

ሲድኒ ከጆሴፍ ስሚዝ ጋር እየተገናኘ።

በኋላም፣ ሲድኒ ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጋር ተገናኘ። ጌታ በጆሴፍ በኩል ለሲድኒ መልዕክት ሰጠው። ሲድኒ ያደረጋቸውን መልካም ነገሮች እንደተመለከተ እና ጸሎቱንም እንደሰማው ተናገረ። ጌታ፣ እርሡ የሚሠራው ታላቅ ሥራ እንዳለው ለሲድኒ ነገረው። ሲድኒ ታላላቅ ነገሮችን ያደርጋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 35፥3–4