በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሚስዮን ወደ ጥንታዊ አሜሪካውያን


“ሚስዮን ወደ ጥንታዊ አሜሪካውያን፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ሚስዮን ወደ ጥንታዊ አሜሪካውያን፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ጥቅምት 1830 (እ.አ.አ)–ጥር 1831 (እ.አ.አ)

ሚስዮን ወደ ጥንታዊ አሜሪካውያን

የደለዌር ሕንዳውያን ወንጌልን ሠሙ።

ፓርሊ ፕራት፣ ኦሊቨር ካውድሪ እና ሌሎች ሚስዮናውያን የደለዌር ሕንዳውያንን አንድ ቤት እየጎበኙ።

ፓርሊ ፕራት እንደተጠመቀ ብዙም ሳይቆይ፣ ከኦሊቨር ካውድሪ እና ከሌሎች ጋር በሚስዮን እንዲያገለግል ጌታ ጥሪ ሠጠው። ለጥንታዊ አሜሪካውያን ወንጌልን እንዲሰብኩ ፈልጎ ነበር። ሚስዮናውያኑ ለብዙ ሣምንታት በጥልቅ በረዶ ላይ ተጓዙ። በመጨረሻም፣ የደለዌር ሕንዳውያን አለቃ የነበረውን ኪክታዌኑንድን አገኙ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥1430፥5–632ቅዱሳን1፥98115

ኦሊቨር እና ፓርሊ የመፅሐፈ ሞርሞንን መልዕክት እያካፈሉ።

አለቃው ሚስዮናውያንን የተቀበላቸው በወዳጅነት መንፈሥ ነበር። የእነርሱን መልዕክት ይሠሙ ዘንድ ጓደኞቹን ጋበዛቸው። ኦሊቨር፣ እርሱ እና ፓርሊ መፅሐፈ ሞርሞንን ለእነርሱ ለማምጣት ሩቅ እንደተጓዙ ተናገረ። መጽሐፉ ከረጅም ጊዜ በፊት በአሜሪካ አህጉር ስለኖሩ ሰዎች ይናገራል። እግዚአብሄር፣ ሁሉም ሰው ስለኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ያውቅ ዘንድ መጽሐፉን እንዲያካፍሉ ፈለገ።

ቅዱሳን1፥115–16

ኦሊቨር የመፅሐፈ ሞርሞንን ቅጂ ለኪክታዌኑንድ እየሰጠ።

ኦሊቨር የመፅሀፈ ሞርሞንን ቅጅ ለኪክታዌኑንድ ሠጠው። ኦሊቨር እና ጓደኞቹ መፅሐፉን ለእርሱ ህዝብ ለማካፈል ይህን ያህል ርቀት ተጉዘው በመምጣታቸው አመስጋኝ ነበር። ተመልሰው እንዲመጡና መጽሐፈ ሞርሞንን እንዲያነቡላቸው እንዲሁም ስለእሱ ይበልጥ እንዲያስተምሯቸው እንደሚፈልግ ለኦሊቨር እና ለፓርሊ ነገራቸው።

ቅዱሳን1፥116–17