“በምዙሪ ውስጥ የነበረ ችግር፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“በምዙሪ ውስጥ የነበረ ችግር፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
ሐምሌ 1831–ሐምሌ 1833 (እ.አ.አ)
በምዙሪ ውስጥ የነበር ችግር
በአደገኛ ጊዜያት እምነትን አጠንክሮ መያዝ
ብዙዎቹ ቅዱሳን በኢንዲፔንደንስ፣ ምዙሪ ለመኖር መጥተዋል። ጌታ በዚያ የጽዮንን ከተማ እንዲገነቡ ፈልጓል። ነገር ግን በኢንዲፔንደንስ እየኖሩ የነበሩ ቅዱሳን እና በዚያ የነበሩት ህዝቦች አልተስማሙም። በብዙ ነገሮች አይስማሙም ነበር። በከተማው የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ብስጩዎች ነበሩ እና ቅዱሳኑ እንዲወጡላቸው ይፈልጉ ነበር።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 57፥1–3፤ Saints [ቅዱሣን]፣ 1፥171–74
ኤድዋርድ ፓርትሪጅ በኢንዲፔንደንስ ኤጲስ ቆጶስ ነበር። ከከተማው መሪዎች ጋር ለስብሰባ መጣ። እነርሱም ቅዱሳኑ ከኢንዲፔንደንስ ለቀው መውጣት አለባቸው አሉ። ኤጲስ ቆጶስ ፓትሪጅ እግዚአብሔር ቅዱሳንን በኢንዲፔንደንስ ጽዮንን እንዲገነቡ እንደሚፈልግ ያውቅ ነበር። ቅዱሳኑ ለቀው መውጣት አይችሉም አለ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥176
ቁጡ ሰዎች ቅዱሳን የገነቧቸውን ቤቶች እና ህንጻዎችን ማፈራረስ ጀመሩ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥177–78፣ 182
ሰዎቹ ኤጲስ ቆጶስ ፓርትሪጅን እና ሌላኛውን ሰው ቻርልስ አለንን ከቤታቸው ወሰዷቸው። ሁለቱን ሰዎች ወደ ከተማው መካከል ጎተቷቸው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥179
ኤጲስ ቆጶስ ፓርትሪጅ፣ ‘’ለሃይማኖቴ መሰቃየት ካለብኝ፣ ከእኔ በፊት የነበሩት ሌሎች ከደረሰባቸው በላይ አይሆንም’’ በማለት ተናገረ። ሰዎቹ ኤጲስ ቆጶስ ፓርትሪጅን እና ቻርልስን ወደምድር ገፈተሯቸው። የፈላ ሬንጅ እና ላባዎችን በመላ በአካላቸው ላይ አደረጉ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥179–80
በኢንዲፔንደንስ የቤተክርስቲያን አባል የነበረው ውልያም መክለለን ቁጡዎቹ ሰዎች ያደርጉ ስለነበረው ነገር ሰማ። እርሱ በጣም ፈራ እና ለመደበቅ ወደ ቁጥቋጦው ውስጥ ሮጠ።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥182
ውልያም ብስጩዎቹ ሰዎች ቢያገኙት ምን ሊፈጠር እንደሚችል አሰበ። በእርሱ ምክንያት ሊገሉት እንኳ ቢፈልጉ፣ አሁንም መጽሐፈ ሞርሞን እውነት ነው በማለት ይናገራልን?
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥182–83
የውልያም ጓደኞች ኦሊቨር ካውድሪ እና ዴቪድ ዊትመር በቁጥቋጦዎቹ ውስጥ አገኙት። ኦሊቨር እና ዴቪድ በመጽሐፈ ሞርሞን እንዳመኑ ውልያም ያውቅ ነበር። መልአክ የወርቅ ሰሌዳዎቹን አሳይቷቸዋል። ‘’ንገሩኝ፣’’ በማለት ውልያም ጠየቃቸው፣ ‘’ያ መጽሐፈ ሞርሞን እውነት ነውን?’’
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥183
ኦሊቨር እና ዴቪድ መጽሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ለውልያም ነገሩት። የተበሳጩት ሰዎች ሊገድሏቸው ቢፈልጉም እንኳ፣ ለህዝቡ ምስክርነታቸውን ማካፈላቸውን በፍጹም እንደማያቆሙ ተናገሩ። ‘’አምናችኋለሁ፣’’ በማለት ውልያም ተናገረ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17፥3–6፣ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥183