“የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመሰረተ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች (2024[እ.አ.አ])።
“የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመሰረተ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች።
ሚያዝያ 1830 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመሰረተ
አስደሳች የቤተክርስቲያን ስብሰባ
አሁን መፅሐፈ ሞርሞን ታትሟል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር የክህነት ህይል ዳግም በምድር ላይ ነበር። ጌታ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን የማደራጀት ጊዜው እንደሆነ ለጆሴፍ ነገረው።
ቅዱሳን፣ 1፥84
ሚያዚያ 6፣ 1830(እ.አ.አ)፣ ወደ 40 የሚጠጉ ሴቶች እና ወንዶች ቤተክርስቲያኗን ለማደራጀት ወደ ዊትመር ቤተሰብ መጡ። ጌታ ቤተክርስቲያኑን ይመሩ ዘንድ ጆሴፍን እና ኦሊቨርን ጠርቶ ነበር። ጆሴፍ እና ኦሊቨር እንደ መሪዎቻቸው አድርገው እንደሚደግፏቸው ለማሳየት እጃቸውን እንዲያወጡ ህዝቡን ጠየቁ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥1–3፤ ቅዱሳን፣ 1፥84
ከዚያም፣ ጆሴፍ እና ኦሊቨር ቅዱስ ቁርባኑን ባረኩ። ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ይረዳቸው ዘንድ ለሰዎች ሰጧቸው። ከዚያም ጆሴፍ እና ኦሊቨር በተጠመቁት ሰዎች ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ። የቤተክርስቲያኗ አባል አድርገው ማረጋገጫ ሰጧቸው፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታንም ሰጧቸው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥75–79፣ ቅዱሳን፣ 1፥85
ጌታ ስለአዲሷ ቤተክርስቲያን ለጆሴፍ መልእክት ሰጠው። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስለሚደረጉት ነገሮች እንዲጽፉ ነገራቸው። ጆሴፍ ስሚዝ የእርሱ ነቢይ እንደሆነ ተናገረ። የቤተክርስቲያኗ አባላት፣ ለጆሴፍ የሰጣቸውን ትዕዛዛት የሚከተሉ ከሆነ እንደሚባርካቸው ቃል ገባላቸው። ሰይጣን በእነርሱ ላይ ኃይል አይኖረውም፡፡
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥1–6፣ ቅዱሳን፣ 1፥85
ሰዎቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን በማግኘታቸው በጣም ተደሰቱ! ከስብሰባው በኋላ የጆሴፍን እናት እና አባት ጨምሮ በርከት ያሉ ሰዎች ተጠመቁ። አባቱ ከውኃው በወጣ ጊዜም ጆሴፍ በጣም አቀፈው። “አባቴ በእውነተኛዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሲጠመቅ ለማየት በቅቻለሁ!” ሲል ተናገረ።
ቅዱሳን፣ 1፥86
በዚያ ምሽት፣ ጆሴፍ ብቻውን ይሆን ዘንድ ወደ ጫካ ሄደ። ልቡ በደሥታ ተሞልቶ ነበር። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገለጡለት 10 ዓመታት ሆነውት ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብዙ ነገሮች ተከናውነዋል። ጆሴፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ዳግም በመመለስ መርዳት ስለቻለ በጣም አመስጋኝ ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥86