በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ለኤማ የመጣ ራዕይ


“ለኤማ የመጣ ራዕይ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ለኤማ የመጣ ራዕይ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሐምሌ 1830 (እ.አ.አ)

ለኤማ የመጣ ራዕይ

የእርሱን ሥራ እንዲሰሩ በጌታ የተመረጡ።

ጆሴፍ እጁን በማውለብለብ ኤማን እየተሰናበተ።

የኤማ እና የጆሴፍ ህይወት በጣም በፍጥነት እየተቀየረ ነበር። ጆሴፍ በግብርና ላይ ማተኮሩን ማቆም እንዳለበት ጌታ ነገረው። ከዚያ ይልቅ፣ ጆሴፍ ጊዜውን ሰዎችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተማር እና የጌታ ቤተክርስቲያን እንድታድግ በመርዳት ማሳለፍ አለበት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥7–9ቅዱሳን1፥96

ኤማ ጆሴፍ ሲሄድ በመስኮት ወደ ውጪ እያየች።

ኤማ ይህን ለውጥ አስመልክቶ ብዙ ጥያቄዎች ነበሯት። ጆሴፍ ጌታን በሚያገለግልበት ጊዜ እርሷ ምን ማድረግ እንዳለባት አታውቅም ነበር። እርሷም ጌታን እና የእርሱን ቤተክርስቲያን ትረዳለች?

ቅዱሳን1፥96

ኤማ እና ጆሴፍ እየሣቁ።

ጌታ ለጆሴፍ በሰጠው ራዕይ በኩል ኤማን ተናገረ። “ኤማ ስሚዝ፣ ልጄ” ብሎ ጠራት። የእርሱን ሥራ እንድትሰራ እንደመረጣት እና እንደጠራት ለኤማ ነገራት። ልዩ ሴት ነበረች እንዲሁም እርሷ የምትሠራው ታላቅ ሥራ ነበረው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥1–3

ኤማ ወንጌልን እያካፈለች።

ኤማ ከጆሴፍ ጋር እንድትጓዝ ጌታ ጠየቃት። ኤማ ቅዱሳት መጻህፍትን እንደምታብራራ እና የቤተክርስቲያኗን አባላት እንደምታስተምር ጌታ ተናግሯል። ኤማ በህይወቷ እንድታስቀድመው እና ቃል ኪዳኖቿን እንድትጠብቅ ነግሯታል። የእርሡ መንፈሥ እንደሚኖራት ለኤማ ቃል ገብቶላታል። እንድትማር፣ እንድታድግ እና የእርሱን በረከቶች እንድትቀበል ፈለገ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥2፣ 6–10፣ 15

ኤማ በቤተክርስቲያን ስብሰባ ላይ መዝሙር እየመራች።

በተጨማሪም፣ ጌታ ልጆቹ ሲዘምሩ መስማት እንደሚወድ ለኤማ ነገራት። የቅዱሳኑ መዝሙሮች ለእርሱ እንደ ጸሎት እንደሆነ ተናገረ። ኤማ ቅዱሳን እያነበቡ በጋራ የሚዘምሩበት የመዝሙር መጽሐፍ እንድታዘጋጅ ጠየቃት። ኤማ ስለጌታ እና ስለወንጌሉ ብዙ ደሥ የሚሉ መዝሙሮችን አገኘች በመዝሙር መፅሐፉ ውስጥም አካተተቻቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥11–12ቅዱሣን1፥221–22

ኤማ እና ጆሴፍ ለጎረቤቶቻቸው እጆቻቸውን ለሠላምታ እያውለበለቡ።

የኤማ እና የጆሴፍ ህይወት መቀየሩን ቀጠለ፣ ሆኖም ኤማ ጌታ እንደሚወዳት እና ለእርሷ ዓላማ እንደነበረው አወቀች። ጌታን እና በዙሪያዋ ያነበሩትን ሠዎች አገለገለች። የኢየሱስን ቤተክርስቲያን በማሳደግ ረዳች።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥13–15ቅዱሣን1፥221–23