“ጆሴፍ እና ስድኒ ስለሰማይ ተማሩ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ጆሴፍ እና ስድኒ ስለ ስለሰማይ ተማሩ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
የካቲት 1832 (እ.አ.አ)
ጆሴፍ እና ስድኒ ስለሰማይ ተማሩ
እግዚአብሔር ለልጆቹ ስላለው በረከቶች የተሰጠ ራዕይ
አንድ ቀን፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን መጽሐፍ ቅዱስን እያነበቡ ነበር። ሰዎች ከሞቱ በኋላ ምን ይከሰታል ስለሚለው አነበቡ። ጆሴፍ እና ስድኒ ስላነበቡት ነገር አሰቡ፣ እና ተጨማሪ ነገሮችን ለመማር ፈለጉ።
ጌታ አስደናቂ ራእይን ሰጣቸው። የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን በመላእክት ታጅበው አዩ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚናገር ድምጽን ሰሙ። ድምጹም ኢየሱስ ለእኛ እንደሞተ እና ከዚያም ከሞት እንደተነሳ—ወደ ህይወት ዳግም እንደተመለሰ ተናገረ። እርሱ ይህን በማድረጉ ምክንያት፣ እኛም እንዲሁ ከሞት እንነሳለን።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥19–24፣ 39–43
ጆሴፍ እና ስድኒ ከሞት ከተነሳን በኋላ፣ መንግስታት በተባሉ በሰማይ ካሉ ከሶስቱ ስፍራዎች በአንዱ እንደምንኖር ተማሩ። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ያልተቀበሉ ሰዎች ወደ ቲለስቲያል መንግስት ይሄዳሉ። ጌታም ይህን መንግስት ከከዋክብት ብርሃን ጋር አመሳሰለ።
ጆሴፍ እና ስድኒ ተረስትሪያል መንግሥት ስለሚባለውም መንግስትም ጨምሮ ተማሩ። ይህ መንግስት መልካም ህይወትን ሲኖሩ ለነበሩ ነገር ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሙሉ በሙሉ ላላከበሩ ሰዎች ነው። በእርሱ ላይ ባላቸው እምነት ጠንካሮች አልነበሩም። ጌታም ይህን መንግስት ከጨረቃ ብርሃን ጋር አመሳሰለ።
ከፍተኛው መንግስት የሰለስቲያል መንግስት ነው። በዚህ መንግስት ያሉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳንን የገቡ፣ እና ቃል ኪዳናቸውን የጠበቁ ናቸው። ንሰሃ ገብተዋል እናም ኢየሱስ ክርስቶስን ተከትለዋል፡፡ እነርሱም ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለም ይኖራሉ እንደ እነርሱም ይሆናሉ። ጌታም ይህን መንግስት ከጸሃይ ብርሃን ጋር አመሳሰለ።
ጌታ ጆሴፍ እና ስድኒ በራእይ ያዩትን ሁሉ ለማንም እንዳያካፍሉ ነገራቸው። ነገር ግን የተወሰነውን ክፍል እንዲጽፉ እና ለሌሎች እንዲያካፍሉ ፈልጎ ነበር። ብዙዎቹ የቤተክርስቲያኗ አባላት ስለራእዩ ለሰዎች ለመናገር ተደስተው ነበር።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥113–119፤ Saints [ቅዱሣን]፣ 1፥149–50
አንዳንድ ሰዎች ራዕዩን አልወደዱም ነበር። እነርሱ ያምኑት ከነበረው የተለየ ነበር። ነገር ግን አብዛኞቹ ቅዱሳን ስለዚህ ራዕይ በማወቃቸው አመስጋኞች ነበሩ። ይህ የሰማይ አባት ልጆቹን እንደወደደ እና ወደ እርሱ እንዲመለሱ መንገድ ያዘጋጀ መሆኑን አሳይቷቸው ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥149–50