በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ፓርሊ ምህረት ለማግኘት ጠየቀ


“ፓርሊ ምህረት ለማግኘት ጠየቀ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ፓርሊ ምህረት ለማግኘት ጠየቀ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ጥር– ሐምሌ 1837 (እ.አ.አ)

ፓርሊ ምህረት ለማግኘት ጠየቀ

የጓደኛው ምስክርነት እምነቱን አሳደገለት።

ታንክፉል እና ፓርሊ ፕራት አዲስ የተወለደ ልጃቸውን ይዘው።

የታንክፉል እና ፓርሊ ፕራት ልጅ የመውለጃ ጊዜያቸው ሲደርስ፣ ለሚስዮን ከሄዱበት ከካናዳ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። ልክ ጌታ ቃል እንደገባላቸው ጤነኛ ወንድ ህጻን ልጅን አገኙ።

Saints [ቅዱሳን]1፥270

ፓርሊ በታንክፉል መቃብር አጠገብ ህጻኑን ይዞ።

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ታንክፉል ህጻኑ ከተወለደ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ሞተች። ያለእርስዋ ህጻኑን መንከባከብ የማይችል መሆኑን ፓርሊ አውቋል። ሚሲዮኑን ለመጨረስ ወደ ካናዳ በተመለሰ ጊዜ በከርትላንድ የነበረች አንዲት ሴት ህጻኑን እንድትንከባከብለት ጠየቃት።

Saints [ቅዱሳን]1፥270

ጆሴፍ ስሚዝ ስለ አዲሱ ባንክ ሰዎችን ሲያነጋግር።

በከርትላንድ ውስጥ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ለእግዚአብሔር ስራ ገንዘብን ለማሰባሰብ ባንክ ጀመረ። ባንኩ ገንዘባቸውን እበመጠቀም ሌሎች መበደር እንዲችሉ እንዲያደርግ ሰዎችን ጠየቀ። ነገር ግን፣ በተለያዩ ምክንያቶች፣ ባንኩ በቂ ገንዘብ ስላልነበረው መዘጋት ነበረበት። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ባንኮችም አልተሳካላቸውም ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥260–61264–68

ቅዱሳን በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ስለባንክ ሲከራከሩ።

ለቅዱሳን ህይወት አስቸጋሪ ሆነ። አንዳንዶች ስራቸውን አጡ እና አሁን ምግብ ወይም አልባሳትን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም። አንዳንድ ሰዎች በጆሴፍ ላይ ተበሳጭተዋል፣ የቅርብ ጓደኞቹም እንዲሁ። ባንኩ ስላልተሳካለት ጆሴፍ እውነተኛ ነቢይ አልነበረም በማለት አሰቡ።

Saints [ቅዱሳን]1፥264–68272275

ፓርሊ ጨቅላ ልጁን ይዞ።

ይህ እየሆነ እያለ፣ ፓርሊ ከሚስዮን አገልግሎቱ ወደ ቤቱ ተመለሰ። በባንኩ የነበረው ችግር በፓርሊ ላይም ህይወትን ከባድ አደረገ። ለቤቱ የሚከፍለው ገንዘብ ሊኖረው አይችልም ነበር፣ እና ሊኖርበት የሚችልም ቤት አይኖረውም ነበር።

Saints [ቅዱሳን]1፥270–71

ፓርሊ ለጆሴፍ ደብዳቤን ጻፈ።

አሁን ፓርሊ በጆስፍ ላይም እንዲሁ ተቆጣ። ለጆሴፍ ደብዳቤ ጻፈ። አሁንም በመፅሐፈ ሞርሞን እንደሚያምን ለጆሴፍ ነገረው። ነገር ግን፣ ስለ ነቢዩ ያልተገቡ ነገሮችን ተናገረ። መጀመሪያውኑ ጆሴፍ ባንክ መጀመሩ ስህተት የነበረ መሆኑን ነገረው።

Saints [ቅዱሳን]1፥271

ፓርሊ በካናዳ ለነበሩ ጓደኞቹ ሰላምታ ሲያቀርብ።

በኋላም፣ በካናዳ የነበሩ የፓርሊ ጓደኞች ወደ ከርትላንድ መጡ። ፓርሊ ወንጌልን አስተምራቸው ነበር፣ እና እንደገና ስላዩት ተደሰቱ።

Saints [ቅዱሳን]1፥279–80

ፓርሊ እና ሌሎች ከጆሴፍ ጋር ሲከራሩ የፓርሊ ጓደኞች ሲመለከቱ።

ነገር ግን ፓርሊ እና ሌሎች ብዙዎች ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ የነበረ የመሆኑን እምነት እንዳጡ በማየታቸው ጭምር ተገርመዋል።

Saints [ቅዱሳን]1፥279–80

ፓርሊ ከጆን ቴይለር ጋር ሲነጋገር።

በካናዳ ከነበሩ የፓርሊ ጓደኞች አንዱ ጆን ቴይለር ነበር። ፓርሊ ባየው ጌዜ፣ ለጆን በጆሴፍ ስሚዝ ምን ያህል እንደተበሳጨ ነገረው። ጆን ጆሴፍ ስሚዝን ከዚህ በኋላ እንዳይከተል ነገረው።

Saints [ቅዱሳን]1፥280

ጆን ለፓርሊ ምስክርነቱን ሲያካፍል።

ጆን ካናዳ በነበሩበት ጊዜ ጆሴፍ ስሚዝ እውነተኛ ነቢይ የነበረ መሆኑን ፓርሊ መስክሮ እንደነበር ለፓርሊ አስታወሰው። ‘’እኔ አሁንም ተመሳሳይ ምስክርነት አለኝ፣’’ በማለት ጆን ተናገረ። ‘’ስራው ከስድስት ወራት በፊት እውነት ከነበረ፣ ዛሬም እውነት ነው። ጆሴፍ ስሚዝ ያኔ ነቢይ ከነበረ፣ አሁንም ነቢይ ነው።’’

Saints [ቅዱሳን]1፥280

ፓርሊ ጆሴፍን እና ሌሎችን በከርትላንድ ቤተመቅደስ ሲያስተውላቸው።

ፓርሊ ጓደኛው ጆን ትክክል የነበረ መሆኑን ያውቅ ነበር። ለጆሴፍ በጻፈው የብስጭት ደብዳቤ አዘነ። ጆሴፍ የጌታን ስራ ለመስራት የሚችለውን ሁሉ ያደርግ እንደነበር ያውቅ ነበር። በባንክ የነበረው ችግር ጆሴፍ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ነቢይ የነበረ ከመሆኑ ጋር የተገናኘ አልነበረም።

Saints [ቅዱሳን]1፥283

ፓርሊ ጆሴፍን ይቅርታ ጠየቀ።

ፓርሊ ወደ ጆሴፍ ቤት ሄደ። እርሱ ስለተናገራቸው ያልተገቡ ነገሮች ያዘነ ስለመሆኑ ለጆሴፍ ነገረው። ጆሴፍ ፓርሊን ይቅር አለው፣ ጸለየለት፣ እና ባረከው። ፓርሊ ሌሎች ብዙ የሚሲዮን አገልግሎቶችን ሰጠ እና በአለም ላይ ለሚገኙ ህዝቦች ሁሉ ጆሴፍ ስሚዝ የጌታ ነቢይ እንደነበር ተናገረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥7–11Saints [ቅዱሳን]1፥283