ምዕራፍ ፱
አይሁዶች በቃልኪዳናቸው ምድር ላይ ሁሉ እንደሚሰበሰቡ ያዕቆብ ገለጸ—የኃጢያት ክፍያው ለሰው ከውድቀት ቤዛ ይሆናል—የሙታን አካል ከመቃብር እንዲሁም መንፈሳቸው ከሲኦልና ከገነት ይመጣል—ይፈረድባቸዋል—የኃጢያት ክፍያው ከሞት፣ ከሲኦል፣ ከዲያብሎስ፣ ማለቂያ ከሌለው ስቃይ ያድናል—ፃድቃን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ይድናሉ—የኃጢያት ቅጣቶች ተገልፆአል—የእስራኤሉ ቅዱስ የመግቢያው በር ጠባቂ ነው። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ጌታ ከእስራኤል ቤት ሁሉ ጋር የገባውን ሀቃል ኪዳን ታውቁ ዘንድ እኔ እነዚህን ነገሮች አንብቤአለሁ—
፪ እናም እርሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ወደ እውነተኛው ቤተ ክርስቲያንና ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ሀደግመው እስከሚመጡ ድረስ፣ እነርሱ ወደ ቤታቸው ወደ ለርስት ምድራቸው በሚሰበሰቡበትና የቃልኪዳናቸው ምድር ሁሉ ሐበሚመሰርቱበት ጊዜ ለአይሁድ በቅዱስ ነቢያቱ አፍ እንደተናገረ አንብቤአለሁ።
፫ እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እነዚህን ነገሮች ለእናንተ የምናገረው ጌታ እግዚአብሔር በልጆቻችሁ ላይ ባፈሰሰበት በረከት ምክንያት እንድትደሰቱና ራሳችሁን ለዘለዓለም ሀእንድታነሱ ነው።
፬ ከእናንተ ብዙዎቹ ወደፊት ስለሚመጡ ነገሮች ለማወቅ ብዙ እንደመረመራችሁ አውቃለሁ፤ ስለዚህ ስጋችን አርጅቶ ከዚያም እንደሚሞት እንደምታውቁም አውቃለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ ሀበአካላችን እግዚአብሔርን እናያለን።
፭ አዎን፣ እኛ ከመጣንበት በኢየሩሳሌም ውስጥ ላሉት እራሱን በአካል እንደሚያሳይ እንደምታውቁ አውቃለሁ፤ በእነርሱ መካከል ይህ መሆኑ አስፈላጊ ነውና፤ ምክንያቱም ታላቁ ሀፈጣሪው ሁሉም ሰዎች ለእርሱ ይገዙ ዘንድ እርሱ ለሰው ልጆች በስጋ ለመገዛት እንዲፈቅድና፣ ለሰዎች ለሁሉ ይሞት ዘንድ አስፈላጊ ነበረበት።
፮ ምህረት የተሞላበት የታላቁ የፈጣሪ ሀዕቅድ ይፈጸም ዘንድ፣ ሞት በሰው ልጆች ላይ ስለመጣ፣ ለየትንሣኤ ኃይል ይኖር ዘንድ ያስፈልጋል፣ ሐበውድቀት የተነሳ ትንሣኤ ለሰው መምጣቱ አስፈላጊ ነው፣ እናም ውድቀት የመጣው በመተላለፍ ምክንያት ነው፤ እና ሰውም በመውደቁ ምክንያት ከጌታ ፊት መተለይቷል።
፯ ስለዚህ፣ ሀወሰን የሌለው ለየኃጢያት ክፍያ ይኖር ዘንድ ያስፈልጋል—በዚህ ወሰን በሌለው የኃጢያት ክፍያ ባይሆን ኖሮ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን አይለብስም ነበር። ስለዚህ፣ በሰው ላይ የመጣው ሐየመጀመሪያው ፍርድ ለዘለዓለም መየሚቆይ መሆን ነበረበት። እናም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ይህ ስጋ ሞቶ፣ በስብሶ፣ ተበታትኖ ወደ እናት ምድሩ በመመለስ፣ በድጋሚ ሳይነሳ በቀረ ነበር።
፰ አቤቱ የእግዚአብሔር ሀጥበብ፣ ለምህረቱና ሐፀጋው! እነሆም፣ መስጋ የማይነሳ ቢሆን ኖሮ መንፈሳችን ከዘለዓለማዊው አምላክ ፊት ተነጥሎ ዳግም እንዳይነሳ ሠከተጣለውና ረዲያብሎስ ለሆነው መልአክ ተገዢዎች ይሆኑ ነበር።
፱ እናም መንፈሶቻችን እንደርሱ ሊሆኑ በተገባቸው ነበር፣ እናም እኛ ዲያብሎሶች፣ ለዲያብሎስ ሀመላእክቶች በመሆን ከአምላካችን ፊት ለየጠፋንና፣ ሐከሀሰት አባት ጋር፣ በችግር፣ ልክ እንደእርሱ የቀረን እንሆን ነበር፤ አዎን፣ በዚያ የመጀመሪያ ቤተሰቦቻችንን መእንዳታለለው፣ እራሱን እንደብርሃን ሠመልአክ እንዲመስል ራሱም ረእንደቀየረውና፣ የሰው ልጆችን በግድያ ሰሚስጥራዊ ሴራዎች እና በሁሉም የጨለማ ሚስጥር ስራዎች እንደሚበጠብጠው እንሆን ነበር።
፲ አቤቱ፣ ከዚህ ከሚያስቀይመው አስፈሪ እቅፉ፣ አዎን፣ እኔ የስጋ ሞት፣ እናም ደግሞ የመንፈስ ሞት ብዬ የምጠራው ያ አስፈሪ ሀሞትና ለሲኦልን ሊያስመልጠን መንገዱን ያዘጋጀልን የአምላካችን ጥሩነት እንዴት ታላቅ ነው።
፲፩ እናም የእኛ አምላክ የእስራኤል ቅዱስ ሀማምለጫውን መንገድ ስላዘጋጀልን፣ ጊዜያዊ የሆነው እኔ የተናገርኩት ይህ ለሞት፣ ሙታኖቹን ያስረክባል፤ ይህም ሞት መቃብር ነው።
፲፪ እናም መንፈሳዊ ሞት የሆነው ይህ እኔ የተናገርኩት ሀሞት፣ ሙታኖቹን ያስረክባል፤ ይህም መንፈሳዊ ሞት ለሲኦል ነው፤ ስለዚህ፣ ሞትና ሲኦል ሙታኖቻቸውን ማስረከብ አለባቸው፣ እናም ሲኦል የያዛቸውን መንፈሶች ማስረከብ አለበት፣ መቃብርም የያዘቻቸውን አካላት ማስረከብ አለባት፣ እናም የሰዎች ስጋና ሐመንፈስ አንዱ ወደ ሌላው መደግሞ ይመለሳል፤ ይህም በእስራኤል ቅዱስ የትንሳኤ ሀይል ነው።
፲፫ አቤቱ የአምላካችን ሀዕቅድ እንዴት ታላቅ ነው! በሌላው በኩል፣ የእግዚአብሔር ለገነት የቅዱሳንን መንፈስ ማስረከብ አለባት፤ መቃብርም የፃድቃንን ስጋ ታስረክባለች፤ እናም ስጋና መንፈስ እንደነበሩ ሐበድጋሚ ይገጣጠማሉ፣ ሁሉም ሰዎች የማይበሰብሱና፣ መየማይሞቱ ይሆናሉ፣ እና የእኛም ሠእውቀት ረፍፁም ከመሆኑ በቀር፣ እነርሱም ልክ እንደእኛ በስጋ ፍፁም እውቀት ያላቸው ነፍሳት ይሆናሉ።
፲፬ ስለዚህ፣ ሀስለስህተቶቻችን ሁሉና፣ ንፁህ አለመሆናችንን፣ እናም ለስለራቁትነታችን ፍፁም ሐእውቀት ይኖረናል፤ መጻድቃንም ሠንፅህናን ረለብሰው የጽድቅ ሰመጎናፀፊያ ተደርቦላቸው ስለደስታቸውና ጻድቅነታቸው ፍፁም እውቀት ይኖራቸዋል።
፲፭ እናም እንዲህ ይሆናል ሁሉም ሰዎች ከዚህ ከመጀመሪያው ሞት ወደ ሕይወት ሲያልፉና፣ ህያዋን ሲሆኑ፣ በእስራኤል ቅዱስ ሀየፍርድ ወንበር ፊት መምጣት አለባቸው፤ እናም ከዚያ ለፍርዱ ይመጣል፣ ከእዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ቅዱስ ፍርድ መሰረት ይፈረድባቸው ይገባል።
፲፮ እናም በእርግጥ፣ ጌታ ህያው እንደሆነ፣ ጌታ አምላክ ተናግሮታልና፣ እናም ይህ የእርሱ ሀሳይከናወን የማይቀር ዘለዓለማዊ ለቃሉ ነው፣ ፃድቅ የሆኑት አሁንም ፃድቅ ይሆናሉ፣ ሐየረከሱትም አሁንም መርኩሳን ይሆናሉ፤ ስለዚህ፣ የረከሱት ሠዲያብሎስና መላዕክቱ ናቸው፤ እነርሱም ደግሞ ለእነርሱ ወደ ተዘጋጀላቸው ወደ ረዘለዓለማዊ እሳት ይሄዳሉ፤ እናም ስቃያቸው እሳቱ ወደላይ ለዘለዓለም እንደሚነሳ ወላፈን፣ መጨረሻ እንደሌለው በዲን እንደሚቃጠል ሰየእሳት ባህር ይሆናል።
፲፯ አቤቱ የአምላካችን ሀፍትህና ታላቅነት እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ ቃሉን ሁሉ ይፈፅማል፣ እነርሱም ከአፉ ወጥተዋል፣ እናም የእርሱ ህግ መፈፀም አለበት።
፲፰ ነገር ግን፣ እነሆ፣ ፃድቃን፣ የእስራኤሉ ቅዱሰ ሀቅዱሳኖች፣ በእስራኤሉ ቅዱስ ያመኑት፣ የዓለምን ለመስቀሎች የታገሱ፣ እፍረቷንም የናቁ፣ እነዚህ ሐከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ የተዘጋጀላቸውን የእግዚአብሔርን መመንግስት ሠይወርሳሉ፣ እናም ደስታቸው ረለዘለዓለም ሙሉ ይሆናል።
፲፱ አቤቱ የአምላካችን የእስራኤል ቅዱስ ታላቅነትና ምህረት እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ ቅዱሳኑን ከሚያስቀይመው ሀከአስፈሪው ዲያብሎስና፣ ከሞትና፣ ለከሲኦል፣ እናም ከዚያ መጨረሻ የሌለው ስቃይ ከሆነው በዲን ከሚቃጠለው የእሳት ባህር ሐአድኗቸዋልና።
፳ አቤቱ የአምላካችን ሀቅዱስነት እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ ሁሉን ነገሮች ለያውቃልና፣ እናም እርሱ ከሚያውቀው በስተቀር ምንም ነገር የለም።
፳፩ እናም እርሱ ሰዎች ሁሉ የእርሱን ድምፅ የሚያዳምጡ ከሆነ ሀሊያድናቸው ዘንድ ወደ እዚህ ዓለም ይመጣል፤ እነሆም፣ እርሱ በሁሉ ሰዎችን ለህመም፣ አዎን፣ ሐበአዳም ቤተሰብ አባል በሆኑት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረታት፣ በወንድም፣ በሴትም፣ በልጆችም ህመም ይሰቃያል።
፳፪ እናም እርሱ ይህን ሁሉ የሚሰቃየው ትንሣኤ በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ያልፍ ዘንድና፣ ሁሉም በእርሱ ፊት በታላቁና በፍርድ ቀን ይቆሙ ዘንድ ነው።
፳፫ እናም እርሱ ሁሉም ሰዎች፣ በእስራኤል ቅዱስ ፍፁም የሆነ እምነት ኖሯቸው ሀንስሀ መግባትና፣ በእርሱ ስም ለመጠመቅ እንዳለባቸው ያዝዛል፣ ካልሆነ ግን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መዳን አይችሉም።
፳፬ እናም በእርሱ ስም የማያምኑና ንስሀ የማይገቡ፣ ሀበስሙም የማይጠመቁና፣ እስከመጨረሻው ለየማይጸኑ ከሆነ ግን ሐመኮነን ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም ጌታ አምላክ የእስራኤል ቅዱስ ተናግሮታልና።
፳፭ ስለዚህ፣ እርሱ ሀህግን ሰጥቷል፤ እናም ለህግ ባልተሰጠበት ቅጣት የለም፤ እናም ቅጣት በሌለበት ኩነኔ የለም፤ እናም መኮነን በሌለበት በኃጢያት ክፍያው የተነሳ የእስራኤል ቅዱስ ምህረት በእነርሱ ላይ ውጤታማ ይሆናል፤ ምክንያቱም በእርሱ ኃይል ድነዋልና።
፳፮ ከአስቀያሚ ከአስፈሪው ከሞትና ከሲኦል፣ እናም ከዲያብሎስና፣ መጨረሻ ከሌለው በዲን ከሚቃጠለው የእሳት ባህር ስቃይ ይተርፉ ዘንድ፣ ሀህጉ ለባልተሰጣቸው ሁሉ ላይ ሐየኃጢያት ክፍያው መለፍትህ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያደርጋል፤ እናም ሠእስትንፋስ ወደሰጣቸው እስራኤሉ ቅዱስ ወደሆነው እግዚአብሔር ይመለሳሉ።
፳፯ ነገር ግን ሀህጉ ለተሰጠው፣ አዎን፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ልክ እንደ እኛ ያለው፣ እናም የሚተላለፋቸውና፣ የሙከራውን ጊዜ የሚያባክን ወዮለት፣ መጨረሻው አሰቃቂ ነውና!
፳፰ አቤቱ የክፉ የብልጠት ሀዕቅድ! አቤቱ የሰው ለግብዝነትና ድክመትና፣ ሞኝነት! ሐበተማሩ ጊዜ ራሳቸውን መእንደብልህ ይቆጥራሉ፣ እናም የእግዚአብሔርን ሠምክር የማይሰሙ፣ በራሳቸው እንደሚያውቁ በማሰብ፣ ይህን ችላ ይሉታልና፣ ስለሆነም ጥበባቸው ሞኝነታቸው ነው እና አይጠቅማቸውም። እነርሱም ይጠፋሉ።
፳፱ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሀምክሮች ለየሚያደምጡ ከሆነ መማር ጥሩ ነው።
፴ ነገር ግን በዓለም ሀብት ሀሀብታም ለሆኑት ወዮላቸው። ሀብታም በመሆናቸው ለድሆችን ይጠላሉና፣ ትሁቶችን ያሳድዳሉና፤ ልባቸውም በሀብታቸው ላይ ነውና፤ ስለዚህ፣ ሀብታቸው አምላካቸው ነው። እናም እነሆ፣ ሀብታቸው ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይጠፋል።
፴፩ እናም ሀመስማትን ለማይፈልጉ ለደንቆሮዎች ወዮላቸው፤ ይጠፋሉና።
፴፪ ማየትንም ለማይፈልጉ ለዕውሮች ወዮላቸው፤ እነርሱም ደግሞ ይጠፋሉና።
፴፫ ልባቸውን ላልተገረዙት ወዮላቸው፣ የኃጢአታቸው እውቀት በመጨረሻው ቀን ይጎዳቸዋልና።
፴፬ ሀለውሸታም ወዮለት፣ ወደታች ወደ ለሲዖል ይጣላልና።
፴፭ እያወቀ ሀለሚገድል ለነፍሰ ገዳይ ወዮለት፣ ለይሞታልና።
፴፮ ለሚያመነዝሩ ሀለአመንዝራዎች ወዮላቸው፣ ወደታች ወደ ሲኦል ይጣላሉና።
፴፯ አዎን፣ ጣኦትን ሀለሚያመልኩ ወዮላቸው፣ የዲያብሎሶች ሁሉ ዲያብሎስ በእነርሱ ይደሰትባቸዋልና።
፴፰ እናም፣ በአጠቃላይ፣ በኃጢአታቸው ለሚሞቱ ሁሉ ወዮላቸው፤ ወደ እግዚአብሔር ሀይመለሳሉና፣ እናም ፊቱን ያያሉ፣ በኃጢአታቸውም ይቀራሉ።
፴፱ አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ቅዱስ የሆነውን እግዚአብሔርን መተላለፍ እንዴት መጥፎ እንደሆነ፣ እናም ደግሞ ለዚያ ሀለተንኮለኛ ፈተናዎች መጋለጥ እንዴት አስቀያሚ እንደሆነ አስታውሱ። ለስለዓለም ማሰብ ሐሞት እንደሆነና፣ ስለመንፈሳዊ ነገር ማሰብ መዘለዓለማዊ ሠህይወት እንደሆነ አስታውሱ።
፵ አቤቱ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ቃሌን አድምጡ። የእስራኤሉን ቅዱስ ታላቅነት አስታውሱ። እኔ በእናንተ ላይ ከባድ ነገሮችን እንደተናገርኩ አትበሉ፤ ይህንንም ካላችሁ፣ እውነትን ትቃወማላችሁ፤ እኔ የእናንተን ፈጣሪ ቃላት ተናግሬአለሁና። ሀየእውነት ቃላት ንፁህ ላልሆኑ ሁሉ ላይ ለአስቸጋሪ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ጻድቆች አይፈሯቸውም፣ እውነትን ይወዳሉና እናም አይጨነቁም።
፵፩ ከዚያም አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ወደ ጌታ ወደ ቅዱሱ ሀኑ። መንገዱ ፅድቅ እንደሆነ አስታውሱ። እነሆ፣ ለሰው ለመንገዱ ሐጠባብ ነው፣ ነገር ግን በእርሱ ፊት በቀጥተኛ አቅጣጫ ይጓዛል፣ መመግቢያውን ጠባቂ የእስራኤሉ ቅዱስ ነው፤ እናም እርሱ በዚያ ቦታ ምንም አገልጋይ አይቀጥርም፤ እናም በመግቢያው ካልሆነ በቀር ምንም ሌላ መንገድ የለም፤ እርሱ ሊታለል አይችልምና፣ ጌታ አምላክ የእርሱ ስም ነውና።
፵፪ እናም ለሚያንኳኳ ሁሉ ለእርሱ ይከፍትለታል፤ እና ሀብልሆችም፣ የተማሩትና፣ ሀብታም ለሆኑት፣ በትምህርታቸው፣ በጥበባቸውና በሀብታቸው ኩራት ለከፍ ያሉ—አዎን፣ እነርሱን ነው እርሱ የሚጠላው፤ እናም እነዚህን ነገሮች ካልጣሉም፣ እራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ሐሞኞች አድርገው ካላሰቡና፣ ራሳቸውን በጥልቅ መትህትና በጣም ዝቅ ካላደረጉ፣ ለእነርሱ አይከፍትላቸውም።
፵፫ ነገር ግን የብልሆችና የአስተዋዮች ነገሮች—አዎን፣ ለቅዱሳን የተዘጋጀው ያ ደስታ፣ ከእነርሱ ለዘለዓለም ሀይደበቃሉ።
፵፬ አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ቃላቴን አስታውሱ። እነሆ፣ ካባዬን አውልቄ በፊታችሁ አራግፈዋለሁ፤ የመዳኔ አምላክ ሀሁሉን በሚያይ ዐይኑ እንዲመለከተኝ እፀልያለሁ፤ ስለዚህ፣ ሁሉም ሰዎች እንደስራቸው በሚፈረድባቸው በመጨረሻው ቀን፣ የእስራኤል አምላክ ኃጢአታችሁን ከላዬ ላይ ለእንዳወረድኩ፣ እናም በእርሱ ፊት በክብር እንደምቆምና ከደማችሁ ሐንፁህ እንደሆንኩ እንደሚመሰክር ታውቃላችሁ።
፵፭ አቤቱ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ከኃጢአታችሁ ተመለሱ፤ አጥብቆ ከሚያስራችሁ የእርሱን ሀሰንሰለት በጥሱ፤ ወደ መዳናችሁ ለዓለት ወደሆነው እግዚአብሔር ኑ።
፵፮ ለዚያ ሀየፍርድ ቀን ለሆነው፣ ለፍትህ ለፃድቃን ለሚሰጥበት ለዚያ ለታላቁ ቀን በአሰቃቂ ፍርሃት እንዳትሸማቀቁ፣ ሐኃጢአታችሁን በፍፁም መልኩ እንዳታስታውሱ፣ እናም በታላቅ ድምፅ፥ ቅዱስ ቅዱስ ነው ፍርድህ፣ አቤቱ መሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ—ነገር ግን ኃጢአቴን አውቃለሁ፤ ህግህን ተላልፌአለሁ፣ መተላለፎቼም የእኔው ናቸው፤ እናም ዲያብሎስ እኔን ይዞኛል፣ ስለዚህ እኔ የእርሱ ጉዳት የደረሰብኝ የመከራው ተሳዳጅ ነኝ በማለት ለመናገር እንድትገፋፉ ነፍሳችሁን አዘጋጁ።
፵፯ ነገር ግን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ ስለእነዚህ መጥፎ ነገሮች እውነታ እንድትነቁ ዘንድ ማድረጌ አስፈላጊ ነውን? አዕምሮአችሁ ንፁህ ቢሆን ኖሮ እኔ ነፍሶቻችሁን አሰቃይ ነበርን? ከኃጢአታችሁ ንፁህ ብትሆኑ ኖሮ በእውነቱ ግልፅነት እኔ ለእናንተ ግልፅ እሆን ነበርን?
፵፰ እነሆ፣ ቅዱሳን ብትሆኑ ኖሮ እኔ ስለቅዱስነት እነግራችሁ ነበር፤ ነገር ግን እናንተ ቅዱስ ስላልሆናችሁ፣ እና እኔን እንደአስተማሪ ስለአያችሁኝ፣ ሀስለኃጢያት ውጤት ለአስተምራችሁ ዘንድ አስፈላጊ ነው።
፵፱ እነሆ፣ ነፍሴ ኃጢያትን ትጠላለች፣ ልቤ ደግሞ በጻድቅነት ትደሰታለች፤ እናም የቅዱስ አምላኬን ስም ሀአሞግሳለሁ።
፶ ወንድሞቼ ሆይ፣ ኑ፣ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ሀውኃው ኑ፤ እና ገንዘብ የሌላችሁ፣ ኑ ግዙና ብሉ፤ አዎን፣ ኑ ወይንና ወተት ለያለገንዘብና ያለዋጋ ግዙ።
፶፩ ስለዚህ፣ ዋጋ በሌለው ነገር ገንዘብ አታባክኑ፣ ወይንም አጥጋቢ ለማይሆን ሀጉልበታችሁን አታባክኑ፣ እናም አድምጡኝ፣ የተናገርኳቸውንም ቃል አስታውሱ፤ ወደ እስራኤሉ ቅዱስ ኑ፣ እናም የማይጠፋውን ሊበላሽ የማይቻለውን ለተመገቡና፣ ነፍሳችሁ በመፋፋት ትደሰት።
፶፪ እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ የአምላካችሁን ቃላት አስታውሱ፤ ያለማቋረጥ በቀን ለእርሱ ፀልዩ፣ እናም በመሸ ጊዜ ለቅዱስ ስሙ ሀምስጋናን አቅርቡ። ልባችሁም ትደሰት።
፶፫ እናም እነሆ የጌታ ሀቃል ኪዳን እንዴት ታላቅ ነው፣ እናም ለሰው ልጆች እራሱን ዝቅ ማድረጉ እንዴት ታላቅ ነው፤ በታላቅነቱ፣ በጸጋውና ለበምህረቱ የተነሳ ለእኛ ዘራችንን በሙሉ በስጋ እንደማይጠፋ፣ ነገር ግን እንደሚጠብቃቸው ቃል ገብቶልናል፤ በሚመጡትም ትውልዶች በእስራኤል ቤት የተቀደሰ ሐቅርንጫፍ ይሆናሉ።
፶፬ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ ሆይ፣ ለእናንተ የበለጠ እናገራለሁ፤ ነገር ግን በማግስቱ የተቀሩትን የእኔን ቃላት እገልፅላችኋለሁ። አሜን።