የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፳፬


ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፳፬፥፯–፲።መዝሙር ፳፬፥፯–፲ ጋር አነጻፅሩ

የክብር ንጉስ በሚመጣበት ጊዜ ህዝቡን ይቤዣቸዋል።

ራሶቻችሁን ከፍ አድርጉ፣ የያዕቆብ ትውልዶች ሆይ፤ እና ወደላይ ከፍ ተደረጉ፤ እና ክብር ንጉስ የሆነው ብርቱና ኃያል ጌታ፣ በሰልፍ ኃያል ጌታ ለዘለአለም ይመሰርታችኋል።

እና ሰማይን ይጠቀልላል፤ እና ህዝቦቹን ለማዳን፣ የዘለአለም ስም ለመስራት፣ በዘለአለም ስለቱ ላይ እንዲመሰርታችሁ ይወርዳል።

ራሶቻችሁን ከፍ አድርጉ፣ የያዕቆብ ትውልድ ሆይ፤ ራሶቻችሁን ከፍ አድርጉ፣ የዘለአለም ትውልዶች ሆይ፤ እና የሰራዊት ጌታ፣ የነገሥታት ንጉሥ፤

እንዲሁም የክብር ንጉስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እና ህዝቦቹን ያድናል፣ እና በጻድቅነትም ይመሰርታቸዋል። ሰላህ