Scripture Stories
ሙሴ በሲና ተራራ ላይ


“ሙሴ በሲና ተራራ ላይ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ሙሴ በሲና ተራራ ላይ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘጸአት 19–20፤ 2431–34ዘዳግም 4–7

ሙሴ በሲና ተራራ ላይ

ጌታን እንዲያስታውሱ ህዝቡን መርዳት

ምስል
ሲና ተራራ

ሙሴ እና እስራኤላውያን በምድረበዳ ውስጥ ተጓዙ። ሲና ተራራ ወደሚባል ተራራ መጡ።

ዘጸአት 19፥1

ምስል
ሙሴ እየፀለየ

ሙሴ ጌታን ለማናገር ወደ ተራራው ወጣ። ጌታ ከእስራኤላውያን ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር እንደሚፈልግ ለሙሴ ነገረው።

ዘጸአት 19፥3፤ 9–11

ምስል
ደመና ተራራን ሲከብ

እስራኤላውያን ወደ ሲና ተራራ ግርጌ መጡ፤ ጌታም የጢስ ደመና ተራራውን እንዲከበው አደረገ። ጌታ በደመና ውስጥ ነበር። ከእስራኤላውያን ጋር ተነጋገረ እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጣቸው። እርሱ ሲናገር ተራራው ተናወጠ።

ዘጸአት 19፥16–1920፥1–17ዘዳግም 4፥12–13፣ 335፥4–5

ምስል
እስራኤላዊያን ፈርተው

እስራኤላውያን ፈርተው ነበር፡፡ ጌታ የሚፈልገውን ሊነግራቸው ይችል ዘንድ ከጌታ ጋር እንዲነጋገር ሙሴን ጠየቁት።

ዘጸአት 20፥18–19

ምስል
እስራኤላውያን ሽማግሌዎች በተራራ ላይ

ሙሴ የጌታን ትምህርቶች የበለጠ ለመቀበል አሮንን እና 70 እስራኤላውያን ሽማግሌዎችን ወደ ተራራው ወሰደ። ጌታ ለእነርሱ ተገለጠ።

ዘጸአት 24፥1፤ 9–11

ምስል
ጌታ ለሙሴ በጽላቶች ላይ ሲጽፍ

ከዚያም ሽማግሌዎቹን ትቶ ወደ ተራራው ከፍ ብሎ እንዲወጣ ጌታ ለሙሴ ነገረው። ሙሴ የታዘዘውን አደረገ። ጌታ ህጉን እና ትእዛዛቱን በድንጋይ ጽላቶች ላይ ለመፃፍ ጣቱን ተጠቀመ። ለ40 ቀናት፣ ጌታ ለሙሴ ብዙ ነገሮችን አስተማረው።

ዘጸአት 24፥12–1831፥18

ምስል
እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃ እየሰሩ

ሙሴ በሲና ተራራ ላይ በነበረበት ወቅት የእስራኤል ሕዝብ እርሱን በመጠበቅ ደከሙ። በግብፅ ያደርጉት እንደነበረው ይሰግዱለት ዘንደ ሐውልት እንዲሠራላቸው ለአሮን ነገሩት። አሮን ወርቃቸውን ሁሉ ሰበሰበ እና የጥጃ ሐውልት ሠራ።

ዘጸአት 32፥1–4

ምስል
እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃ አመለኩ

እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃን አመለኩ እናም መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ከግብፅ ነፃ ያወጣቸው ጌታ ሳይሆን የወርቅ ጥጃ እንደሆነ ተናገሩ።

ዘጸአት 32፥4–6፤ 21–24

ምስል
ሙሴ ከተራራ እየወረደ

እስራኤላውያን ጣዖትን እያመለኩ እና እርሱን እየረሱ እንደነበር ጌታ አውቋል። ሙሴም እንዲመለስ እና ህዝቡ ንስሐ እንዲገቡ እንዲነግራቸው አዘዘው።

ዘጸአት 32፥7–10

ምስል
ሙሴ ከእስራኤላውያን ጋር ሲነጋገር፣ የወርቅ ጥጃውም ፈረሰ

ሙሴ ከሲና ተራራ ወረድ እና እስራኤላውያን የወርቅ ጥጃ ሲያመልኩ አየ። በጣም ተቆጥቶ ነበር። ሕዝቡ ጌታ የጻፈውን ሕግና ትእዛዛት ለመታዘዝ ዝግጁ አልነበሩም። ሙሴ ጽላቶቹን ሰበረ እንዲሁም የወርቅ ጥጃውን አፈረሰ። ንስሐ እንዲገቡና እውነተኛ አምላካቸውን እንዲያስታውሱ እስራኤላውያንን ረዳቸው።

ዘጸአት 32፥15–20፣ 25–29

ምስል
ሙሴ እየፀለየ

ሙሴ እስራኤላውያንን ይቅር እንዲላቸው እና ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳኖችን እንዲገባ ጌታን ጠየቀ። ሙሴ እንደሚመራቸውና እንደሚያስተምራቸው ቃል ገባ።

ዘጸአት 32፥30–34

ምስል
ሙሴ ከአሥርቱ ትእዛዛት ጽላቶች ጋር

ጌታ አዲስ የድንጋይ ጽላቶችን እንዲሠራና ወደ ሲና ተራራ እንዲመለስ ሙሴን ጠየቀው። ጌታ ከእስራኤላውያን ጋር አዲስ ቃል ኪዳን ገባ እንዲሁም አሥርቱን ትእዛዛቱን ሰጣቸው።

ዘጸአት 20፥2–1734፥1–17፣ 28ዘዳግም 6፥24–257፥12–13