Scripture Stories
የምድር አፈጣጠር


“የምድር አፈጣጠር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“የምድር አፈጣጠር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 1–2፤ ሙሴ 1–3፤ አብርሐም 3–5

የምድር አፈጣጠር

ለሰማይ አባት ልጆች የሚያምር ቤት

ምስል
እግዚአብሔር እና ጌታ አጽናፈ አለሙን ሲፈጥሩ

የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር በሰማይ የደህንነትን ዕቅድ አቀረበ። ሁላችንም በደስታ ጮኸን! ስጋዊ አካልን ለመቀበል ወደ ምድር መምጣት እንችል ነበር። በምድር ላይ ሳለን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተልን እንማራለን። ጌታ የእግዚአብሔርን መመሪያዎች በመከተል ምድርን ፈጠረ።

ዘፍጥረት 1፥1ኢዮብ 38፥4–7ሙሴ 1፥32–332፥1አብርሐም 3፥22–27

ምስል
ፕላኔት በጠፈር ውስጥ

በመጀመሪያው ቀን፣ ጌታ ብርሀንን ከጭለማ ለየ። ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፣ ጨለማውንም ሌሊት አለው።

ዘፍጥረት 1፥3–5ሙሴ 2፥3–5አብርሐም 4፥1–5

ምስል
ዳመናዎች እና ውቅያኖስ

በሁለተኛው ቀን፣ ውሃዎቹን በሰማይ ባሉ ደመናዎች እና በምድር ላይ ባሉ ውቅያኖሶች መካከል ከፈላቸው።

ዘፍጥረት 1፥6–8ሙሴ 2፥6–8አብርሐም 4፥6–8

ምስል
ጫካ በውቅያኖስ ዳር

በሶስተኛው ቀን፣ ጌታ ታላቅ ውቅያኖሶችን እና ደረቅ ምድርን ፈጠረ። ውሀዎቹን ባህር እና ደረቁን መሬት ምድርብሎ ጠራቸው። ምድርንም በአበቦች፣ በፍሬዎች፣ በዕጽዋት፣ እና በዛፎች አሳመረ።

ዘፍጥረት 1፥9–13ሙሴ 2፥9–13አብርሐም 4፥9–13

ምስል
የምሽት እና የቀን ምልክቶች

በአራተኛው ቀን፣ በቀን እንዲበራ ፀሐይን ፈጠረ። ከዚያም ጨረቃን እና ከዋክብትን በሌሊት እንዲበሩ ፈጠረ።

ዘፍጥረት 1፥14–19ሙሴ 2፥14–19አብርሐም 4፥14–19

ምስል
የባህር ፍጡሮች

በአምስተኛው ቀን፣ ጌታ በባህር ውስጥ ያሉትን ዓሦች እና በሰማይ ያሉትን ወፎች ፈጠረ። ፍጥረታትን እንዲባዙ ባረካቸው እንዲሁም ዓሦቹ ባህሩን እንዲሞሉ ባረካቸው።

ዘፍጥረት 1፥20–23ሙሴ 2፥20–23አብርሐም 4፥20–23

ምስል
የጫካ እንስሳት

በስድስተኛው ቀን፣ በምድር ላይ እንስሳትን ፈጠረ፣ የተወሰኑት የሚራመዱ ጥቂቶቹ የሚሳቡ ነበሩ።

ዘፍጥረት 1፥24–25ሙሴ 2፥24–25አብርሐም 4፥24–25

ምስል
አዳም እና ሔዋን በኤደን ገነት

የሰማይ አባት እና ጌታ በስድስተኛው ቀን ወደ ምድር ወረዱ። ወንድና ሴት በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠሩ። የሰማይ አባትም እርስ በርሳቸው እንክብካቤ እንዲሰጣጡ እና ልጆች እንዲወልዱ ነገራቸው። ወንድና ሴትም መሬቱንና እንስሳቱን እንዲንከባከቡ ሀላፊነት ተሰጣቸው።

ዘፍጥረት 1፥26–27ሙሴ 2፥26–27አብርሐም 4፥26–315፥7–8

ምስል
አዳምና ሔዋን እንስሳትን እየተመለከቱ

የሰማይ አባት በፈጠሩት ሁሉ ደስተኛ ነበር። በሰባተኛው ቀን ከሥራቸው ሁሉ አረፉ። ምድር ውብና በሕይወት የተሞላች ነበር።

ዘፍጥረት 2፥1–3ሙሴ 3፥1–3አብርሐም 5፥1–3