“ዳዊት እና ጎልያድ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ዳዊት እና ጎልያድ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
1 ሳሙኤል 17
ዳዊት እና ጎልያድ
ግዙፍ ፈተናን መጋፈጥ
ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ያጠቁ ነበር። በየጠዋቱም ጎልያድ የሚባለው ግዙፍ ፍልስጥኤማዊ ማንኛውም እስራኤላዊ ከእርሱ ጋር እንዲዋጋ ይገዳደር ነበር። ጎልያድ ከማንም ሰው በላይ ትልቅ እና ረጅም እንዲሁም ጨካኝ ነበር። ከባድ ጥሩር ይለብስ ነበር፤ እንዲሁም ሰይፍ፣ ጦር፣ እና ትልቅ ጋሻ ይይዝ ነበር። ከእርሱ ጋር ለመዋጋት የደፈረ ማንም አልነበረም።
1 ሳሙኤል 17፥1–11
ዳዊት በጌታ እምነት የነበረው ወጣት እረኛ ነበር። የእርሱ ታላላቅ ወንድሞች በእስራኤል ሰራዊት ውስጥ ወታደሮች ነበሩ። አንድ ቀን ዳዊት ለወንድሞቹ ጥቂት ምግብ ወሰደ። በጦር ሰፈሩም ሲደርስ፣ የጎልያድን ፉከራ ሰማ።
1 ሳሙኤል 17፥20–23
ዳዊት ለምን ማንም እስራኤልን እንደማይከላከል ወታደሮቹን ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ተናደዱ እናም በጎቹን ወደመጠበቁ እንዲሄድ ነገሩት። ነገር ግን ዳዊት ጌታ እስራኤልን እንደሚከላከል ያውቅ ነበር።
1 ሳሙኤል 17፥24–30
ንጉስ ሳኦል ስለዳዊት እምነት ያውቅ ነበር፤ ስለዚህ ዳዊትን አስጠራው። ዳዊት ጎልያድን ለመዋጋት እንደማይፈራ ለሳኦል ነገረው። ዳዊት አንድ ጊዜ በጎቹን ሲጠብቅ አንበሳና ድብ እንደገደለ አብራራ። ያኔ ጌታ ጠብቆት ነበር፣ ጌታ አሁንም እንደሚጠብቀው ዳዊት ያውቅ ነበር።
1 ሳሙኤል 17፥31–37
ሳኦል ለዳዊት የእርሱን ጥሩር ሰጠው። ነገር ግን ይህም አልሆነውም፣ ስለዚህ ዳዊት አወለቀው። ያለጥሩር ለመዋጋት ወሰነ።
1 ሳሙኤል 17፥38–39
ዳዊት አምስት ድብልብል ድንጋዮችን ሰበሰበ እና በኮረጆው ውስጥ አስቀመጣቸው። ወንጭፉን እና የእረኛ በትሩን ይዞ ጎልያድን ለመጋፈጥ ሄደ።
1 ሳሙኤል 17፥40
ጎልያድ ዳዊትን ሲያየው ጮኸበት እንዲሁም ተሳለቀበት። እረኛ ልጅ ሊያሸንፈው እንደማይችል ተናገረ። ዳዊትም ጌታ እንደሚጠብቀው እንደሚያምን በመመለስ ጮኸ። ዳዊትም የጌታን ታላቅነት ለማሳየት ጎልያድን አሸንፋለሁ አለ።
1 ሳሙኤል 17፥42–47
ዳዊት ወደ ጎልያድ እየሮጠ ሄደ። በፍጥነትም ድንጋዩን በወንጭፉ አስወነጨፈው። ድንጋዩ የጎልያድን ግንባር መታው፣ እናም ግዙፉ ሰው ወደምድር ወደቀ። ጌታ ዳዊት ያለ ሰይፍ ወይም ጥሩር ጎልያድን እንዲያሸንፍ ረዳው።
1 ሳሙኤል 17፥48–50
ፍልስጥኤማውያን ጎልያድ እንደሞተ ሲመለከቱ፣ በፍርሀት ሸሹ። እስራኤላውያን ጦርነቱን አሸነፉ። ዳዊት ጌታን አመነ፣ እናም ጌታ እስራኤልን ጠበቀ።
1 ሳሙኤል 17፥51–53