በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢዩ ሔኖክ


“ነቢዩ ሔኖክ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ሔኖክ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6–7

ነቢዩ ሔኖክ

በጌታ ያለ እምነት እንዴት አንድን ከተማ እንዳዳነ

እግዚአብሔር ሔኖክን ሲያነጋግር

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡ ንስሐ እንዲገቡ እንዲነግራቸው ሔኖክን ጠየቀው። ሔኖክ ግን በደንብ መናገር እንደማይችል አሰበ። ህዝቡ አያደምጡኝም ብሎ ፈርቶ ነበር።

ዘፍጥረት 5፥22ሙሴ 6፥26–31

ህዝቡ በሔኖክ ላይ ሲያፌዙ

አንዳንድ ሰዎች ሔኖክ ያስተማረውን ባይወዱትም፣ ጌታ ሔኖክን ለማጠናከር እና ለመጠበቅ ቃል ገባለት።

ሙሴ 6፥32–39

ሔኖክ ህዝቡን ሲያስተምር

የጌታ ተስፋ ለሔኖክ ድፍረት ሰጠው። ሔኖክ ጌታን በመታዘዝ ህዝቡን በኃይል አስተማረ። ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ንስሀ ስለመግባት፣ ስለጥምቀት፣ እና ስለመንፈስ ቅዱስ አስተማረ። አንዳንድ ሰዎች ሔኖክን አምነው ጌታን መከተል ፈለጉ።

ሙሴ 6፥47–68

ሔኖክ ሴትን ሲያጠምቅ

ሔኖክ ለማጥመቅ ከእግዚአብሔር ስልጣን ነበረው። ሔኖክን ያመኑ ሰዎች በሙሉ ተጠመቁ እንዲሁም ወደ ጌታ ቀረቡ። እርስ በእርስ እንክብካቤ ይሰጣጡ ስለነበር ማንም ድሃ አልነበረም። በፍቅር እና በጽድቅ አብረው ስለኖሩ ፅዮን ተብለው ተጠሩ።

ሙሴ 7፥10–20

የኢየሱስ ህይወት፣ ሞት፣ እና ትንሳኤ

አንድ ቀን ጌታ በምድር ላይ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ለሔኖክ በራእይ አሳየው። ሔኖክ የኢየሱስ ክርስቶስን ህይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ አየ። በመጨረሻዎቹ ቀናት ወንጌል ዳግም እንደሚመለስ ሔኖክ ተረዳ። በተጨማሪም የኢየሱስን ዳግም ምጽዓት አየ።

ሙሴ 7፥21–67

እግዚአብሔር ከፅዮን ህዝብ ጋር ሲነጋገር

በመጨረሻም፣ በፅዮን ከተማ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ሔኖክን አምነው ንስሐ ገቡ። እርስ በእርስ እንክብካቤ ይሰጣጡ ስለነበር እና በሰላም ስለኖሩ፣ ጌታ ከእርሱ ጋር አብረው እንዲኖሩ ወሰዳቸው።

ዘፍጥረት 5፥24ሙሴ 7፥18፣ 21፣ 68–69