“አብርሐም እና ይስሀቅ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“አብርሐም እና ይስሀቅ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፍጥረት 17፤ 21–22
አብርሐም እና ይስሀቅ
አባት፣ ልጅ፣ እና መስዋዕት
አብርሐም እና ሣራ፣ ልክ ጌታ ቃል እንደገባው፣ ወንድ ልጅ ወለዱ። ስሙንም ይስሀቅ ብለው ሰየሙት።
ይስሀቅን ይወዱት ነበር። ትክክለኛውን እንዲመርጥ እና በጌታ እንዲታመን አስተምረውትም ነበር።
በይስሐቅ በኩል መላ ምድርን ለመባረክ እንደሚያድጉ ጌታ ለአብርሃምና ለሣራ ቃል ገባላቸው። ነገር ግን አንድ ቀን ይስሀቅን ወደ ሞሪያ ተራራ እንዲወስድና ይስሀቅን እንደ መሥዋዕት እንዲያቀርብ ጌታ ለአብርሐም ነገረው።
ወደ ተራራው እየተጓዙ ሳሉ፣ ይስሐቅ የመሥዋዕቱ በግ የት እንዳለ ጠየቀ። አብርሐምም ጌታ ይሰጠናል ብሎ መለሰለት።
በምሪያ ተራራ ላይ፣ አብርሐም መሰዊያ ገንብቶ በላዩ ላይ እንጨት አኖረ።
እግዚአብሔር እንዳዘዘውም፣ አብርሐም ይስሐቅን በመሠዊያው ላይ እንዲተኛ ጠየቀው። ልክ አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ እንደታመነ፣ ይስሀቅም አብርሃምን አመነ።
አብርሐም ይስሀቅን ሊሠዋ ሲል፣ የጌታ መልአክ አቆመው። አብርሐም በጌታ ያለውን እምነት አሳየ። አብርሐም ሁልጊዜ ጌታን እንደሚከተል ያውቅ ነበር።
አብርሐም ቀና ብሎ ተመለከትና አንድ አውራ በግ በቁጥቋጦች ውስጥ ተይዞ ተመለከተ። ጌታ ለመሥዋዕት አውራ በግ አቀረበ።
የሰማይ አባት ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ መስዋዕት እንዴት እንደሚያቀርብ አብርሐም እና ይስሀቅ ተማሩ። ታዛዥ በመሆኑ ምክንያት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አብርሐምን አመነው። አብርሐምም አንድ ቀን ቤተሰቦቹ ከሰማይ ከዋክብት ብዛት በላይ እንደሚያድጉ ጌታ የሰጠውን የተስፋ ቃል አመነ።