Scripture Stories
አብርሐም እና ሣራ


“አብርሐም እና ሣራ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2021 (እ.አ.አ)]

“አብርሐም እና ሣራ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 11–15፤ 17፤ አብርሐም 1–2

አብርሐም እና ሣራ

የሰውን ልጅ ቤተሰብ ለመባረክ የተሰጠ የተስፋ ቃል

ምስል
መልአክ አብርሐምን ከካህን አዳነው

አብርሐም በዑር ከተማ ውስጥ ይኖር ነበር። በዚያም ክፉ ካህናት ለጣዖቶታቸው ሊሰዉት ፈለጉ። አብርሐም ጸለየ እናም ጌታ አዳነው።

አብርሐም 1፥1–20

ምስል
አብርሐም እና ሣራ በግመል ተጓዙ

ከዚያም ጌታ አብርሐምን እና ባለቤቱን ሣራን ከዑር እንዲወጡ እና ወደ ሩቅ አገር እንዲጓዙ አዘዛቸው። በጉዞአቸውም እንደሚባርካቸው የተስፋ ቃል ሰጣቸው።

ዘፍጥረት 12፥1–3አብርሐም 2፥2–4

ምስል
አብርሐም እና ሣራ በግ እየጠበቁ

አብርሐም እና ሣራ ጌታን አመኑ እናም ከዑር ወጥተው ሄዱ። ነገር ግን ልጆች ለመውለድ ስላልቻሉ አዝነው ነበር። ጌታም አፅናናቸው። ልጅ እንደሚወልዱም የተስፋ ቃል ሰጣቸው።

ዘፍጥረት 11፥30–3115፥1–617፥2–16አብርሐም 2፥6–9

ምስል
እግዚአብሔር ለአብርሐም ሲገለጥለት

አብርሐም ስለእርሱ ይበልጥ ለማወቅ ወደ ጌታ ጸለየ። ጌታ አብርሐምን ጎበኘው እና ራሱንም ያህዌ ብሎ ጠራ። ያህዌ ከአብርሐም ጋር ቃል ኪዳን ገባ። አብርሐም ክህነት እንደሚኖረውም የተስፋ ቃል ሰጠው። በአብርሐም ቤተሰብ በኩል የምድር ቤተሰቦች በሙሉ እንደሚባረኩም ቃል ገባለት።

አብርሐም 2፥6–11

ምስል
አብርሐም እና ሣራ በግመሎች ሲጓዙ

አብርሐም እና ሣራ በሚጓዙበትም ጊዜ ምግብ አስፈልጓቸው ነበር። ከነዓን ተብሎ በሚጠራ አገር ውስጥ ለመኖር ሞከሩ። በዚያም ምንም ምግብ አልነበረም፤ ስለዚህ ወደ ግብፅ መሄድ ነበረባቸው። ነገር ግን በግብፅ ውስጥ መኖር ለእነርሱ አደገኛ ነበር።

ዘፍጥረት 12፥10–20አብርሐም 2፥21–25

ምስል
አብርሐም እና ሣራ እንስሳትን ሲመለከቱ

አብርሐም እና ሣራ ከግብፅ ወጡ እናም በከነዓን ለመኖር ተመለሱ። ከግብፅም ምግብ እና እንስሳትን ይዘው መጡ። ከነዓንም ጌታ ለእነርሱ ቃል የገባላቸው ምድር ክፍል ነበር።

ዘፍጥረት 13፥1–4፣ 12አብርሐም 2፥19

ምስል
መልከ ጼዴቅ ከአብርሐም እና ከሣራ ጋር ሲነጋገር

ጌታ አብርሐም ክህነት እንደሚቀበል ቃል የገባለትንም አከበረ። አንድ ቀን አብርሐም እና ሣራ መልከ ጼዴቅ ተብሎ ከሚጠራ ጻድቅ ንጉስ ጋር ተገናኙ። አብርሐምም ለእርሱ አስራት ከፈለ።

ዘፍጥረት 14፥18–24አልማ 13፥15

ምስል
መልከ ጼዴቅ አብርሃምን ሲባርክ

አብርሐም ከመልከ ጼዴቅ ክህነትን ተቀበለ። ይህም ነቢያቱ አዳም እና ኖኅ ተቀብለውት የነበረው አንድ አይነት ክህነት ነበር።

የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፥36–40አብርሐም 1፥2–4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥14

ምስል
አብርሐም እና ሣራ

አብርሐም እና ሣራ በከነዓን ደስተኛ ነበሩ፤ ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው አሁንም ይጨነቁ ነበር። አንድ ቀን ቤተሰባቸው እንደሚበዛ እና መላውን ምድር እንደሚባርክ ጌታ የሰጣቸውን የተስፋ ቃል መታመን ይገባቸዋል።

ዘፍጥረት13፥1215፥3–6