Scripture Stories
አዳም እና ሔዋን


“አዳም እና ሔዋን፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“አዳም እና ሔዋን፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 2–3፤ ሙሴ 3–5፤ አብርሐም 5

አዳም እና ሔዋን

ምርጫዎችን በማድረግ ልምድ ማግኘት

ምስል
አዳም እና ሔዋን ከእንስሳት ጋር

አዳም እና ሔዋን በምድር ከሚኖሩት የእግዚአብሔር ልጆች የመጀመሪያዎቹ ነበሩ። በሁሉም ዓይነት እጽዋት እና ዛፎች በተከበበ ውብ የኤደን ገነት ውስጥ ይኖሩ ነበር። የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እነርሱን ይጎበኟቸው እና ያነጋግሯቸው ነበር።

ዘፍጥረት 2፥8–93፥8ሙሴ 3፥8–9አብርሐም 5፥8፣ 14–19

ምስል
መልካምንና ክፉን የሚያሳውቅ ዛፍ

ከአንዱ በስተቀር ከሁሉም የዛፍ ፍሬ እዲበሉ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው። መልካምንና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ከበሉ፣ ከገነት መውጣት አለባቸው እንዲሁም በመጨረሻም ይሞታሉ። ሰይጣን አዳምን እና ሔዋንን ዋሸ። ሰይጣን፣ ፍሬውን ከበሉ መልካምን እና ክፉን ያውቃሉ እንጂ አይሞቱም አለ።

ዘፍጥረት 2፥16–173፥1–5ሙሴ 3፥94፥6–11አብርሐም 5፥912–13

ምስል
ሔዋን ፍሬ ስትቀጥፍ

ሔዋን ፍሬውን ለመብላት መረጠች።

ዘፍጥረት 3፥5–6ሙሴ 4፥12

ምስል
ፍሬ የያዙ እጆች

ሔዋን ለአዳም ከፍሬው ጥቂቱን ሰጠችው። እርሱም ይህን ለመብላት መረጠ።

ዘፍጥረት 3፥6–7ሙሴ 4፥12

ምስል
አዳም እና ሔዋን ከእግዚአብሔር እና ኢየሱስ ተደብቀው

እግዚአብሔር እና ጌታ እነርሱን ጎበኙ፣ ነገር ግን አዳም እና ሔዋን ፈርተው ነበር እናም ተደበቁ። እግዚአብሔርንም መልካምንና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ፍሬ በልተው እንደሆነ ጠየቃቸው።

ዘፍጥረት 3፥8–13ሙሴ 4፥13–14

ምስል
አዳም እና ሔዋን ከኤደን ገነት ሲወጡ

አዳም እና ሔዋን ፍሬውን ለመብላት እንደመረጡ ለእግዚአብሔር ነገሩት። በምርጫቸውም ምክንያት ከኤደን ገነት መውጣት ነበረባቸው። ከእግዚአብሔር ተለያይተው ነበር፣ ነገር ግን ለእነርሱ እቅድ ነበረው። አሁን መልካምን ከክፉ አወቁ እንዲሁም ልጆችን መውለድ ቻሉ።

ዘፍጥረት 3፥16–24ሙሴ 4፥15–31

ምስል
የአዳም እና ሔዋን ቤተሰብ አሳት ሲመለከት

አዳም እና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ ለማክበር ቃል ገቡ። የእንስሳት መስዋዕት እንዲያቀርቡ ተምረው ነበር። ሲታዘዙም ስለእግዚአብሔር ልጅ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጥ ተማሩ። ቤተሰባቸውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ እርሱ ስለሚረዳቸው ሁለቱም ታላቅ ደስታ ተሰማቸው።

ዘፍጥረት 3፥23ሙሴ 5፥1–12