Scripture Stories
ሩት እና ኑኃሚን


“ሩት እና ኑኃሚን፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ሩት እና ኑኃሚን፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ሩት 1–4

ሩት እና ኑኃሚን

ፈተናዎችን በፍቅር እና በታማኝነት መቋቋም

ምስል
ኑኃሚን እና ቤተሰብ በከተማ ሲራመዱ

ኑኃሚን እና ቤተሰቧ በይሁዳ ምድር በቂ ምግብ ስላልነበረ ወደ ሞዓብ ተዛወሩ። ከዚያም የኑኃሚን ባለቤት ሞተ። የኑኃሚን ወንድ ልጆች የሞዓብ ሴቶችን ዖርፋን እና ሩትን አገቡ። ኑኃሚንን ለአስር አመታት ተንከባከቡ።

ሩት 1፥1–4

ምስል
ዖርፋ፣ ሩት እና ኑኃሚን ሲተቃቀፉ

ከዚያም የዖርፋ እና የሩት ባለቤቶች ሞቱ። አሁን ሴቶቹ ብቻቸውን ነበሩ። ኑኃሚን ለዖርፋ እና ሩት ምግብ ለማቅረብ አልቻለችም።

ሩት 1፥5፣ 8–10

ምስል
ሩት እና ኑኃሚን በግመል ሲጓዙ

ዖርፋ ወደ ቤቷ ተመለሰች። ነገር ግን ሩት ለመቆየትና ኑኃሚንን ለመንከባከብ ፈለገች። ሩት እና ኑኃሚን በይሁዳ ምድር እንደገና ሰብሎች እንዳሉ ስለሰሙ ወደዚያ ተጓዙ።

ሩት 1፥16–19

ምስል
ሩት እህል እየሰበሰበች

ሩት እና ኑኃሚን በመከር ወቅት ወደ ይሁዳ መጡ። ምግብ ያስፈልጋቸው ነበር። ቦዔዝ የተባለ የኑኃሚን ዘመድ ይሁዳ ውስጥ እርሻዎች ነበሩት። ሩት የተረፈውን እህል ከእርሻው ውስጥ እንድትወስድ ፈቀደላት። ይህም ከባድ ስራ ነበር።

ሩት 1፥222፥3

ምስል
ቦዔዝ ከሩት ጋር ሲነጋገር

ቦዔዝ ሩትን ጠንክራ ስለሰራች እና ለኑኃሚን እና ለጌታ ታማኝ በመሆኗ አክብሯት ነበር። ተጨማሪ እህል በእርሻ ውስጥ ለሩት እንዲተው አገልጋዮቹን አዘዛቸው።

ሩት 2፥5–17

ምስል
ሩት እና ኑኃሚን

ኑኃሚን ሩት ቤተሰብ እንዲኖራት ፈለገች። ሩት ቦዔዝን እንድታገባ አበረታታቻት። ሩት እሷ እና ቦዔዝ ከተጋቡ ኑኃሚንን በአንድነት መንከባከብ እንደሚችሉ ተገነዘበች።

ሩት 3፥1–24፥15

ምስል
ሩት እና ቦዔዝ

ሩት ቦዔዝ እንዲያገባት ለመጠየቅ ወሰነች። ቦዔዝም ሩት ታማኝ እና በጎ ሴት እንደነበረች ያውቅ ነበር። እርሱም ተስማማ።

ሩት 3፥3–184፥13

ምስል
ሩት፣ ቦዔዝ፣ እና ህጻን

ሩት እና ቦዔዝ ተጋቡ። ወዲያውኑም ሩት ወንድ ልጅ ወለደች። እርሱም የወደፊቱ ንጉስ ዳዊት አያት ሆነ። ከብዙ አመታት በኋላ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ቤተሰብ ዘር ተወልዶ ነበር።

ሩት 4፥13–17