“ነቢዩ ሙሴ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ነቢዩ ሙሴ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዘፀአት 2–3
ነቢዩ ሙሴ
የጌታን ህዝብ ነጻ ለማውጣት የተጠራ
ሙሴ ያደገው እንደ ፈርዖን ሴት ልጅ ወንድ ልጅ ነበር። ሙሴ ግብፃውያን በእስራኤላውያን ላይ ጨካኝ እንደሆኑ አየ። ግብፃውያኑ እስራኤላውያንን ባሪያቸው በማድረጋቸው አዝኖ ነበር።
ዘጸአት 2፥10–11
አንድ ቀን ሙሴ አንድ ግብፃዊ አንድን እስራኤላዊ ሲመታ አየ። እስራኤላዊውን ለመከላከል ሙሴ ግብፃዊውን ገደለው።
ዘጸአት 2፥11–14
ፈርዖን ይህንን ሲያውቅ፣ ሙሴን ለመግደል ፈለገ፤ ነገር ግን ሙሴ ከግብፅ ሸሸ።
ዘፀአት 2፥15
ሙሴ ምድያም ወደምትባል ስፍራ መጣ፣ በዚያም ሲፎራ የተባለች ሴት አገኘ። ተጋቡና ልጆችን ወለዱ።
ዘጸአት 2፥21–22
ሙሴ በምድያም ውስጥ በነበረበት ጊዜ እየነደደ የነበረን ቁጥቋጦ አየ፣ እሳቱ ግን ቁጥቋጦውን አላቃጠለውም። ጌታ በእሳት ውስጥ ተገልጦ ሙሴን አነጋገረው።
ዘጸአት 3፥1–6
ጌታ እስራኤላውያን በግብፅ እየተሰቃዩ እንደሆኑ አውቃለሁ አለ። ወደ ግብፅ እንዲመለስና እስራኤላውያንን በነጻነት እንዲለቅ ለፈርዖን እንዲነግረው ሙሴን አዘዘው። ጌታ ሙሴ እስራኤላውያንን ነፃ እንዲያወጣ እና ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲወስድ እረዳዋለሁ አለ።
ዘጸአት 3፥7–18