Scripture Stories
ሙሴ እና የነሀሱ እባብ


“ሙሴ እና የነሀሱ እባብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ሙሴ እና የነሀሱ እባብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘኁልቁ 21

ሙሴ እና የነሀሱ እባብ

በጌታ ላይ እምነት ማሳደርን መማር

ምስል
እባቦች ሰዎችን ሲያጠቁ

እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሲጓዙ ብዙ ጊዜ ጌታን ይረሱ እና ያጉረመርሙ ነበር። ትሁት እንዲሆኑ እና እርሱን እንዲያስታውሱ ለመርዳት ጌታ እባቦችን ላከ። እባቦቹ ህዝቡን ነደፉ፤ እናም ብዙዎቹ ሰዎች ሞቱ።

ዘኍልቍ 21፥1–6

ምስል
ሕዝቡ ሙሴን እየለመኑት

ብዙም ሳይቆይ ህዝቡ ንስሃ ገባ። ጌታ እባቦቹ እንዲሄዱ እንዲያደርግ እንዲጸልይ ሙሴን ጠየቁት። ጌታ እባቦቹን እንዲሄዱ አላደረገም። ነገር ግን ከተነደፉ ህዝቡ የሚድኑበትን መንገድ አዘጋጀ።

ዘኍልቍ 2፥17

ምስል
ሙሴ የነሀስ እባብ ይዞ

ጌታ ሙሴን ከናስ እባብ እንዲሠራና በበትር ላይ እንዲሰቅለው ነገረው። ሕዝቡ ተነድፈው በነበረ ጊዜ እና የናሱን እባብ በመለከቱ ጊዜ ጌታ አዳናቸው። ጌታም እስራኤላዊያን ትሁት እንዲሆኑ እና በእርሱ እንዲታመኑ ረዳቸው።

ዘኍልቍ 21፥8–91ኛ ኔፊ 17፥41ሔለማን 8፥14–15