Scripture Stories
ነቢዩ ኤርምያስ


“ነቢዩ ኤርምያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ኤርምያስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ኤርምያስ 1–52

ነቢዩ ኤርምያስ

ከመወለዱ በፊት ተጠራ

ምስል
ኤርምያስ እንደነቢይ ተጠራ

ኤርምያስ ልጅ እያለ በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር። አንድ ቀን ጌታ ወደ ኤርምያስ መጣና ነቢይ እንዲሆን ጠራው። ከመወለዱ በፊት ነቢይ ለመሆን እንደተመረጠ ጌታ ለኤርምያስ ነገረው። የኤርምያስ ህይወት ከባድ እንደሚሆን ጌታ ያውቅ ነበር። ነገር ግን ሁሌም ከእርሱ ጋር እንደሚሆን ለኤርምያስ ቃል ገባለት።

ኤርምያስ 1፥1–10።

ምስል
ኤርምያስ ህዝቡን እያስጠነቀቀ

በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ከጌታ ጋር የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች አልጠበቁም። በክፋታቸው ምክንያት ድል እንደሚነሱ ኤርምያስ ሕዝቡን አስጠነቀቀ። ጌታም የሰንበትን ቀን በቅድስና ከጠበቁ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደማትደመሰስ ተናገረ። ነገር ግን ህዝቡ አላደመጡም።

ኤርምያስ 6፥1–198–917፥21–27

ምስል
ኤርምያስ በእስር ቤት ውስጥ

ኤርምያስ ህዝቡን ለብዙ ዓመታት አስተማረ። ነገር ግን ንስሃ አልገቡም ነበር። ይልቁንም ኤርምያስን ጎዱትና ወደ እስር ቤት ጣሉት።

ኤርምያስ 20፥226፥8–937፥15–1838፥6

ምስል
ኢየሩሳሌም ስትደመሰስ ኤርምያስ እየተመለከተ

ኤርምያስ ህዝቡን ይወድ ነበር። በኃጢያታቸው ምክንያት አለቀሰ። እርሱ እንዳለውም ኢየሩሳሌም ተደመሰሰች፤ ህዝቡም ተማረኩ።

ኤርምያስ 9፥1–825፥9–1252፥1–10

ምስል
ኤርምያስ ትንቢቶችን እየፃፈ

ኤርምያስ ወደ ግብፅ ተወሰደ። ጌታ ትንቢቶቹን እንዲፅፍ ነገረው። ነገሮች ከባድ በነበሩበት ጊዜም ጭምር ኤርምያስ ጌታን ታዘዘ። ከጌታ ጋር የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች እንዲጠብቁ ለህዝቡ መንገሩን ቀጠለ።

ኤርምያስ 36፥1–2፣ 27–32