“ሐና፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ሐና፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
1 ሳሙኤል 1–2
ሐና
ለታማኝ ሴት የጌታ መልስ
በየዓመቱ፣ ሐና እና ባለቤቷ የጌታ ቤት ወደሆነው ወደ ቤተመቅደስ ይጓዙ ነበር። ሐና ልጆች አልነበሯትም፣ ስለሆነም በጣም አዘነች። ወንድ ልጅ ይኖራት ዘንድም ፆመች እና ፀለይች። ሐና ወንድ ልጅ ቢኖራት ልጇ ሲያድግ እርሱን እንደሚያገለግል ለጌታ ቃል ገባች።
1 ሳሙኤል 1፥1–11
ዔሊ የሚባል አንድ ካህን ሐና ስታለቅስ አያት። ጌታ ፀሎቷን እንደሚመልስላት ነገራት። ሐና በእግዚአብሔር ታመነች እንዲሁም ተስፋ አደረገች።
1 ሳሙኤል 11፥12፣ 17–18
በዚያም አመት ሐና ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው።
1 ሳሙኤል 1፥20–23
ሐና ለጌታ ቃል የገባችውን አከበረች። ሳሙኤል ዕድሜው በደረሰ ጊዜ በጌታ ቤት ውስጥ እንዲያገለግል ወሰደችው። እርሱ ከካህኑ ዔሊ ጋር አገለገለ። ሐና ሳሙኤልን መጎብኘቷን ቀጠለች። ለእርሱ የሰፋችለትን ልብሶች አመጣችለት። እግዚአብሔር ሐናን በአምስት ተጨማሪ ልጆች ባረካት።
1 ሳሙኤል 1፥24–28፤ 2፥21