“ነቢዩ ሳሙኤል፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ነቢዩ ሳሙኤል፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
1 ሳሙኤል 2–3
ነቢዩ ሳሙኤል
በጌታ የተጠራ ልጅ
ለብዙ ጊዜያት፣ እስራኤላውያን የሚመራቸው የጌታ ነቢይ አልነበራቸውም። በምትኩም፣ መሣፍንት እስራኤልን ለብዙ አመታት ገዙ። በዚህ ጊዜ ሐና ትንሹ ልጇን ሳሙኤልን ከእስራኤል ካህን እና ፈራጅ ከሆነው ዔሊ ጋር እንዲኖር አመጣች። ሳሙኤል ዔሊን በቤተመቅደስ ውስጥ ረዳው።
1 ሳሙኤል 2፥11፣ 18፣ 26፤ 3፥1
የዔሊ ሁለቱ ወንድ ልጆችም በቤተመቅደስ ውስጥ ያገለግሉ ነበር፤ ነገር ግን ለጌታ የተሰጡትን መስዋዕቶች ይሰርቁ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ለዔሊ ቅሬታቸውን አሰሙ፣ ነገር ግን ዔሊ አልቀጣቸውም ነበር።
1 ሳሙኤል 2፥12–17፣ 22–23
አንድ ምሽት ሳሙኤል አንድ ድምፅ ሲጠራው ሰማ። ይህም ዔሊ መስሎት ነበር፣ ስለዚህ ሳሙኤል ወደ እርሱ ሄደ። ነገር ግን ዔሊ አልጠራውም ነበር። ዔሊ ወደ መኝታው እንዲመለስ ለሳሙኤል ነገረው።
1 ሳሙኤል 3፥3–5
ሳሙኤል ድምጹ ለሁለተኛ ጊዜ ሲጠራው ሰማ። ወደ ዔሊ ሂዶ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። ነገር ግን ዔሊ አልጠራውም ነበር። ዔሊ ወደ መኝታው እንዲመለስ ለሳሙኤል ነገረው።
1 ሳሙኤል 3፥6
ሳሙኤል ድምጹ ለሶስተኛ ጊዜ ሲጠራው ሰማ። ወደ ዔሊ ሂዶ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። በዚህ ጊዜ፣ ዔሊ ለሳሙኤል የሚናገረው ጌታ እንደሆነ ተረዳ። ዔሊ ወደ መኝታው እንዲመለስ ለሳሙኤል ነገረው። ጌታ እንደገና ከጠራው፣ ሳሙኤል እንዲያደምጥ ዔሊ ነገረው።
1 ሳሙኤል 3፥8–9
ሳሙኤል ድምጹ ለአራተኛ ጊዜ ሲጠራው ሰማ። በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ጌታ እንዲናገር ጠየቀ እና እርሱም አዳምጣለሁ አለ። ጌታም ዔሊ ኃጢያተኛ ልጆቹን በቤተመቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ መፍቀዱ ትክክል እንዳልሆነ ለሳሙኤል ነገረው። የዔሊ ቤተሰብ በዚያ ውስጥ እንደገና ለማገልገል አይፈቀድላቸውም።
1 ሳሙኤል 3፥10–14
በሚቀጥለው ቀን፣ ዔሊ ጌታ ምን እንዳለው ሳሙኤልን ጠየቀው። ሳሙኤልም ነገረው። ዔሊ ጌታ በሳሙኤል በኩል እንደሚናገር አወቀ።
1 ሳሙኤል 3፥15–18
ዜናውም በእስራኤል ምድር ሁሉ ተሰራጨ። ህዝቡም ጌታ ሳሙኤልን እንደ ነቢዩ እንደመረጠ አወቁ።
1 ሳሙኤል 3፥19–20