Scripture Stories
ነቢዩ ኤልሳዕ


“ነቢዩ ኤልሳዕ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ኤልሳዕ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

2 ነገሥት 2፤ 4

ነቢዩ ኤልሳዕ

የጌታ ተአምራቶች

ምስል
ኤልያስ ከኤልሳዕ ጋር ሲነጋገር

በነቢዩ ኤልያስ በኩል ጌታ ኤልሳዕን ቀጣዩ ነቢይ እንዲሆን አዘጋጀው። ከዚያም ጌታ ኤልያስን ወደ ሰማይ ወሰደው።

2 ነገሥት 2፥1–15

ምስል
ሴት ዘይትን እያፈሰሰች

ኤልሳዕ ብዙ ተዓምራት እንዲያደርግ ጌታ ረዳው። ኤልሳዕ በአንድ ወቅት የአንዲት ድሃ ሴት ዘይት ብዙ ማሰሮዎችን እንዲሞላ በረከት ሰጥቷት ነበር። ከዚያም ሴትዮዋ እዳዋን ለመክፈል ዘይቱን ሸጠች።

2 ነገሥት 4፥1–7

ምስል
ኤልሳዕ ከቤተሰብ ጋር ሲነጋገር

በሌላ ጊዜም፣ አንዲት ታማኝ ሴት ኤልሳዕን አገለገለች እንዲሁም ለእርሱ በጣም ደግ ነበረች። ኤልሳዕ እርሷን ለማገልገል ምን ማድረግ እንደሚችል ጠየቃት። እርሷም ልጅ ለመውለድ ተስፋ አደረገች። ኤልሳዕ እርሷንና ባሏን ወንድ ልጅ እንዲወልዱ ባረካቸው።

2 ነገሥት 4፥8–17

ምስል
ቤተሰብ ሲደሰቱ

ነገር ግን ከጥቂት አመታት በኋላ ልጁ ታመመ እና ሞተ። ሴትየዋ ኤልሳዕን ለመፈለግ ሄደች ምክንያቱም ልጅዋን ማዳን እንደሚችል እምነት ነበራት። ኤልሳዕም መጥቶ ልጁን ባረከው እናም እንደገና በህይወት ኖረ። ጌታም ኤልሳዕ ብዙ ታዕምራትን እንዲያደርግ ረዳው። እርሱም ታላቅ የጌታ ነቢይ ነበር።

2 ነገሥት 4፥18–37