በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢዩ ሚልክያ


“ነቢዩ ሚልክያ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ሚልክያ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ሚልክያ 1፤ 3

ነቢዩ ሚልክያ

የአስራት ህግን መኖር

ሰዎች መልካም ያልሆነ አስራት ሲሰጡ

አይሁዶች ከሰብላቸው እና ከከብቶቻቸው አንድ አሥረኛውን ለጌታ አሥራት ሰጡ። አስራትን ሲከፍሉ ጌታ ባረካቸው። ነገር ግን አንዳንድ አይሁዶች መጥፎ እንጀራ ወይም ዕውር ወይም የታመሙ እንስሳትን እንደ አሥራታቸው መስጠት ጀመሩ። ለራሳቸው ምርጡን አስቀመጡ።

ዘፍጥረት 14፥2028፥22ዘዳግም 12፥6፣ 11፣ 17ሚልክያስ 1፥7–8፣ 12–13

ሚልክያ ሰዎችን እያስተማረ

ጌታ ደስ አልተሰኘም። ሚልክያ የተባለ ነቢይ አይሁዶች አሥራት ሲከፍሉ ሐቀኛ ባልሆኑ ጊዜ ከጌታ እንደሚሰርቁ ነገራቸው። ሚልክያ ንስሐ እንዲገቡ ነገራቸው፡፡

ሚልክያ 3፥8–9

ሚልክያ ሕዝቡ ሐቀኛ አሥራት ሲሰጥ እየተመለከተ

ጌታ ለአይሁዶች ቃል ኪዳን ሰጠ። ሐቀኛ አሥራት ከሰጡ፣ ጌታ ከሰማይ ታላላቅ በረከቶችን ያፈሳል።

ሚልክያ 3፥10–12።