Scripture Stories
አጋር


“አጋር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“አጋር፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ኦሪት ዘፍጥረት 16

አጋር

ጌታ ለሴት ልጁ ያለው እቅድ

ምስል
እርጉዟ አጋር

አጋር የሳራ አገልጋይ ነበረች። ሣራ አርጅታ ነበር እንዲሁም ልጅ አልነበራትም። ልጅ ለመውለድ ይችሉ ዘንድ አጋርን እንዲያገባት ለባሏ ለአብርሐም ነገረችው። አብርሐምና አጋር ተጋቡ፣ እና ብዙም ሳይቆይ አጋር ልጅ ልትወልድ ነበር።

ዘፍጥረት 16፥1–3

ምስል
አጋር ሄደች

አጋር እና ሣራ አንዳቸው ለሌላው ክፉ መሆን ጀመሩ። አጋር ወደ በረሃ ለመሸሽ መረጠች።

ዘፍጥረት 16፥4–6

ምስል
አጋር በውሃ አከባቢ አረፍች

አጋር እየተጓዘች ሳለች፣ በጣም ደከማት እንዲሁም ተጠማች። በመጨረሻ፣ ውሃ ወዳለበት ቦታ መጥታ እዚያ አረፈች።

ዘፍጥረት 16፥7

ምስል
መልአክ አጋርን ሲያነጋግር

ጌታ ስለ አጋር ችግሮች ያውቅ ነበር፤ እናም እርሷን ለመርዳት እቅድ ነበረው። ወደ አብርሐምና ወደ ሣራ እንድትመለስ ሊጠይቃት መልአኩን ላከ። የአጋር ቤተሰብ እንደሚበዛ ቃል ገባ። የምትወልደው ሕፃን ወንድ ልጅ እንደሚሆንና ስሙንም እስማኤል ብላ ልትጠራው እንደሚገባ ተናገረ።

ዘፍጥረት 16፥7–14

ምስል
አጋር እና እስማኤል ከአብርሐምና ከሣራ ጋር

አጋር በጌታ ታመነች እናም መልአኩን ታዘዘች። ወደ አብርሐምና ወደ ሣራ ተመለሰች። አጋር ወንድ ልጅ ወለደች እናም ስሙ እስማኤል ነበር። ጌታ ጥበቃ እያደረገላት እንደነበር አጋር አወቀች።

ዘፍጥረት 16፥11፣ 15