Scripture Stories
ረዓብ እና ሰላዮች


“ረዓብ እና ሰላዮቹ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ረዓብ እና ሰላዮቹ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ኢያሱ 2፤ 6

ረዓብ እና ሰላዮቹ

ቤተሰብን የሚያድን ምርጫ

ምስል
በከተማ ውስጥ ሰዎች በርቀት እየተመለከቱ

ረዓብ የተባለች ሴት ኢያሪኮ በእስራኤላውያን ድል ከመነሳቷ በፊት በዚያ ትኖር ነበር። ጌታ ቀይ ባህርን ለእስራኤላውያን እንደከፈለ ሰማች። ረዓብ እስራኤላውያን ከከተማዋ ጋር ሲዋጉ ጌታ እንደሚረዳቸው ታውቅ ነበር። በኢያሪኮ ያሉ ሰዎች ክፉዎች ነበሩ።

ኢያሱ 2፥9–11

ምስል
ሰላዮች ከጠባቂዎች እየተደበቁ

ነቢዩ ኢያሱ የእስራኤላውያንን ሠራዊት ይመራ ነበር። ሁለት ሰላዮችን ወደ ኢያሪኮ ላከ። ነገር ግን ሰላዮቹ ታይተው ነበር፤ እናም የኢያሪኮ ንጉሥ እነሱን ለመያዝ ጠባቂዎችን ላከ።

ኢያሱ 2፥1–3

ምስል
ረዓብ ከሰላዮች ጋር እያወራች

ሰላዮቹ ወደ ረዓብ ቤት መጡ። ረዓብ ሰላዮቹን ለመርዳት ተስማማች፤ ስለሆነም በጣሪያዋ ላይ ሸሸገቻቸው።

ኢያሱ 2፥4–6

ምስል
ረዓብ ሰላዮችን እየደበቀች

የንጉሱ ሰዎች የረዓብን ቤት ፈተሹ ነገር ግን ሰላዮቹን ማግኘት አልቻሉም። እነሱ ከሄዱ በኋላ፣ ረዓብ ሠራዊቶቻቸው ኢያሪኮን ለመዋጋት ሲመጡ ቤተሰቦችዋን እንዲጠብቁላት ሰላዮቹን ጠየቀቻቸው። ሰላዮቹ ቤተሰቧ ደህና እንደሚሆኑ ለረዓብ ቃል ገቡላት። ከዚያም ረዓብ ሰላዮቹ ለማምለጥ እንዲጠቀሙበት በመስኮቷ ላይ ገመድ ጣለች።

ኢያሱ 2፥3፣ 12–15

ምስል
ረዓብ እና ቤተሰቧ ከኢያሪኮ እያመለጡ

ሰላዮቹ ወደ ነቢዩ ኢያሱ ተመለሱ እና በረዓብ ቤት ውስጥ ማንንም እንዳይጎዱ ለእስራኤላውያን ሠራዊት ነገሩ። በኋላም፣ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ ጋር ሲዋጉ ለረዓብ የገቡትን ቃል ጠበቁ። የረዓብ ድፍረት ቤተሰቧን አዳነ። ቤተሰቧ ከእግዚአብሔርን ህዝብ ጋር አንድ ሆኑ።

ኢያሱ 2፥236፥25ዕብራውያን 11፥31