Scripture Stories
ኖኅ እና ቤተሰቡ


“ኖኅ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ኖኅ እና ቤተሰቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 6–9፤ ሙሴ 8

ኖኅ እና ቤተሰቡ

መርከብ፣ የጥፋት ውኃ፣ እና የጌታ ቃል ኪዳኖች

ምስል
ኖኅ ሰዎችን ሲመለከት

ኖኅ እና ቤተሰቡ ጌታን ታዘዙ። ሁሉም ሌሎች ሰዎች በጣም ኃጢያተኞች ነበሩ። ህዝቡ ንስሃ ካልገቡ ጌታ በጥፋት ውኃ ምድርን እንደሚሸፍን ለኖኅ ነገረው።

ዘፍጥረት 6፥5–13ሙሴ 8፥13–17

ምስል
ኖኅ ህዝቡን ሲያስተምር

ኖኅ ጌታ እንደወደዳቸው እንዲሁም ንስሐ እንዲገቡ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ ህዝብን አስተማረ። እነርሱም አላደመጡም።

ሙሴ 8፥19–30

ምስል
ኖኅ እና ቤተሰብ መርከብን ሲሰራ

ኖኅ ህዝቡ ንስሐ ባለመግባታቸው አዘነ። ጌታ የኖኅ መርከብ የተባለውን ትልቅ መርከብ እንዲሠራ ነገረው። መርከቡ በጥፋት ውኃው ወቅት የኖኅን ቤተሰብ ደህንነት ይጠብቃቸዋል።

ዘፍጥረት 6፥14–18ሙሴ 8፥25

ምስል
እንስሳት ወደ መርከብ ሲገቡ

የኖኅ ቤተሰብ ምግብ ወደ መርከቡ አመጡ። ጌታ ቢያንስ ከእያንዳንዱ እንስሳት አይነቶች ሁለት ሁለቱን ወደ ኖኅ ላከ። እንስሳቱም ወደ መርከቡ ገቡ፣ እናም ከሰባት ቀናት በኋላ ዝናቡ መጣል ጀመረ።

ዘፍጥረት 6፥18–227፥1–9

ምስል
የኖኅ መርከብ በባህር ላይ ስትንሳፈፍ

ልክ ጌታ እንዳስጠነቀቀውም፣ ለ40 ቀናት እና ለ40 ለሊት ዘነበ። ምድርም በጥፋት ውኃ ተሸፈነች።

ዘፍጥረት 7፥6–23

ምስል
ኖኅ እና ቤተሰብ

የኖኅ ቤተሰብ እና በመርከቡ ውስጥ ያሉት ሁሉም እንስሳት በደህና በውኃው ላይ ተንሳፈፉ።

ዘፍጥረት 7፥248፥1–3

ምስል
ኖኅ፣ ቤተሰብ፣ እና እንስሳት በደረቅ መሬት ላይ

የጥፋት ውኃው ሲያልቅም የኖኅ መርከቡ በደረቅ መሬት ላይ አረፈች። ኖኅ እና ቤተሰቡ ጌታን ለማምለክ መሠዊያ ሠሩና ስለጠበቃቸውም አመሰገኑት። ጌታ ምድርን ዳግመኛ በጥፋት ውኃ በፍጹም እንደማያጥለቀልቅ ቃል ገባ። የገባውን ቃል ለማስታወስ ቀስተ ደመና ላከ።

ዘፍጥረት 8፥13–229፥8–17