ምዕራፍ ፴፫
የኔፊ ቃላት እውነት ናቸው—ስለክርስቶስ ይመሰክራሉ—በክርስቶስ የሚያምኑ በፍርድ ወንበር ፊት ምስክር ሆኖ በሚቆመው በኔፊ ቃላት ያምናሉ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን እኔ ኔፊ፣ በህዝቤ መካከል የተነገሩትን ትምህርቶች በሙሉ መፃፍ አልችልም፤ እንደመናገሬ አይነት በፅህፈት ሀጎበዝ አይደለሁም፤ ምክንያቱም ሰው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሲናገር የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ወደ ሰዎች ልጆች ልብ የሚያደርሰው።
፪ ነገር ግን እነሆ፣ በቅዱስ መንፈስ ላይ ልባቸውን ሀአጠጥረው በእነርሱ ውስጥ ቦታ የሌላቸው ብዙዎች አሉ፣ ስለዚህ እነርሱ የፃፉትንና ጠቃሚ አይደለም ብለው የገመቱአቸውን ብዙ ነገሮች ይጥላሉ።
፫ ነገር ግን እኔ ኔፊ፣ መፃፍ ያለብኝን ፅፌአለሁ፣ እና ይህም በልዩ ለህዝቤ ታላቅ ሀዋጋ አለው ብዬ የምገምተው ነው። በእነርሱ የተነሳ ያለማቋረጥም በቀን ለእፀልያለሁ፣ እናም በሌሊት እምባዬ ትራሴን ያረጥባል፤ ወደ ጌታም በእምነት እጮሀለሁ፣ ጩኸቴንም እንደሚሰማ አውቃለሁ።
፬ እናም ጌታ እግዚአብሔር ፀሎቴን ለህዝቤ ጥቅም እንደሚቀድሰው አውቃለሁ። እናም በድካም የፃፍኳቸው ቃላትም በእነርሱ ዘንድ ሀብርቱ ይሆናሉ፤ መልካምም ያደርጉ ዘንድ ለያሳምናቸዋልና፤ ስለአባቶቻቸውም ያሳውቃቸዋል፤ ስለክርስቶስም ይናገራል፤ እናም ሐዘለዓለማዊ ህይወት በሆነው በእርሱ እንዲያምኑና፣ እስከመጨረሻውም እንዲፀኑ ያሳምናቸዋል።
፭ እናም በእውነት ሀበግልፅነት መሰረት፣ ስለኃጢያት ለበፅኑ በመቃወም ይናገራል፤ ስለዚህ፣ ከዲያብሎስ መንፈስ ካልሆነ በቀር እኔ በፃፍኩት ቃላት የሚናደድ ማንም ሰው አይኖርም።
፮ በግልፅነት እደሰታለሁ፤ በእውነት እደሰታለሁ፣ በእኔ ኢየሱስ እደሰታለሁ፣ ነፍሴን ከሲኦል ሀአድኗታልና።
፯ ለህዝቤ ሀልግስና፣ እናም በፍርድ ወንበር ብዙ እንከን የለሽ ነፍሳት እንደማገኝ በክርስቶስ ታላቅ እምነት አለኝ።
፰ ለአይሁድ ልግስና አለኝ—ሀአይሁድ እላለሁ፣ ምክንያቱም እኔ የመጣሁበትን ዘር ማለቴ ነው።
፱ ሀለአህዛብም ደግሞ ልግስና አለኝ። ነገር ግን እነሆ፣ በክርስቶስ ለካልታረቁ፣ እናም ሐበጠባቡ በር ካልገቡ፣ እናም ወደ ህይወት በሚያመራው መበቀጭኑ ጎዳና ሠካልተራመዱ፣ እናም እስከሙከራ ቀናቸውም መጨረሻ ድረስ በጎዳናው ጉዞአቸውን ካልቀጠሉ፣ በማናቸውም ላይ ተስፋ አላደርግም።
፲ እናም አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እናም ደግሞ አይሁድና፣ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ፣ እነዚህን ቃላት አድምጡም፣ በክርስቶስም ሀእመኑ፤ እንዲሁም በእነዚህ ለቃላት የማታምኑ ከሆነ በክርስቶስ እመኑ። እናም በክርስቶስ የምታምኑ ከሆነ በእነዚህ ሐቃላት ታምናላችሁ፣ እነርሱ የክርስቶስ ቃላት ናቸውና፣ እነርሱንም ለእኔ ሰጠኝ፤ እናም ሰዎች ሁሉ መልካም እንዲሰሩ መያስተምራሉ።
፲፩ እናም የክርስቶስ ቃላት ካልሆኑም ፍረዱ—በመጨረሻው ቀን የእርሱ ቃል መሆናቸውን ክርስቶስ ሀበኃይልና በታላቅ ክብር ያሳያችኋል፤ እናም እኔና እናንተ በፍርድ ለወንበር ፊት ለፊት እንቆማለን፤ እናም ምንም እንኳን ደካማ ብሆንም እነዚህን ነገሮች እንድፅፍ በእርሱ እንደታዘዝኩ ታውቃላችሁ።
፲፪ እናም ሁላችንም እንኳን ባንሆን ብዙዎቻችን በታላቁና በመጨረሻው ቀን ሀበመንግስቱ እንድን ዘንድ በክርስቶስ ስም ለአብ እፀልያለሁ።
፲፫ እናም አሁን፣ የእስራኤል ቤት ሁሉ የሆናችሁ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እናም በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ፣ ከመሬት ሀእንደሚጮህ ድምፅ እናገራችኋለሁ፥ ያ ታላቁ ቀን እስኪመጣ መልካም ይሁንላችሁ።
፲፬ እናም ከእግዚአብሔር ቸርነት የማትካፈሉ፣ እናም የአይሁዶችንም ሀቃላት፣ ደግሞም የእኔን ለቃላት፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር በግ አፍ የሚወጣውን ቃል የማታከብሩ፣ እነሆ፣ ዘለዓለማዊ ስንብት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ቃላት በመጨረሻው ቀን ሐይኮንኗችኋልና።
፲፭ በምድር ያተምሁት፣ ሀበፍርድ ወንበር በእናንተ ላይ ይቀርባል፤ ጌታ እንዲህ አዞኛልና፣ መታዘዝ አለብኝ። አሜን።