ምዕራፍ ፳፮
ክርስቶስ ለኔፋውያን ያገለግላል—ኔፊ የህዝቡን መጥፋት አስቀድሞ አየ—ከምድር ውስጥ ይናገራሉ—አህዛብም ሀሰተኛ ቤተክርስቲያንን እናም ሚስጥራዊ ሴራዎችን ይሰራሉ—ጌታ በክህነት የሚደረገውን ተንኮል ይከለክላል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም ልጆቼና የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ክርስቶስ ከሙታን ሀከተነሳ በኋላ እራሱን ለእናንተ ለያሳያል፤ ለእናንተ የሚናገራችሁ ቃልም ለእናንተ ሐህግ ይሆንላችኋል።
፪ እነሆም እላችኋለሁ፣ ብዙ ትውልድ እንደሚያልፉ፣ እናም በህዝቦቼ መካከል ታላቅ ጦርነትና ፀብ እንድሚኖር ተመልክቻለሁ።
፫ እናም መሲሁ ከመጣም በኋላ ሀስለውልደቱ፣ እንዲሁም ስለሞቱና ትንሳኤው፤ ለህዝቦቼ ለምልክቶች ይሰጣል፤ እናም ለኃጢአተኞች ያ ቀን ታላቅና የሚያስፈራ ይሆናል፣ ምክንያቱም እነርሱ ይጠፋሉና፤ እናም የሚጠፉትም እነርሱ ነቢያትንና፣ ፃድቃንን፣ ስለአወጡአቸውና፣ በድንጋይ ስለወገሩአቸው፣ ስለገደሉአቸውም ነው። ስለዚህ የቅዱሳን ሐደም ጩኸት በእነርሱ ላይ ከምድር ወደ እግዚአብሔር ይወጣል።
፬ ስለዚህ፣ ኩራተኞችና፣ አመፅን የሚያደርጉ ሁሉ፣ የሚመጣው ቀንም ሀያቃጥላቸዋል፣ ይላል የሰራዊት ጌታ፣ እንደገለባ ይሆናሉና።
፭ እናም ነቢያትንና፣ ፃድቃንን፣ የሚገድሉ የምድር ጥልቅ ሀይውጧቸዋል፣ ይላል የሰራዊት ጌታ፤ እናም ለተራሮች ይጫኗቸዋል፣ አውሎ ነፋስም ይወስዳቸዋል፣ ህንፃዎችም በላያቸው ላይ ይወድቃሉ፣ እናም ይሰባብሩአቸዋል እንዲሁም ወደ ዱቄትነት ይለውጡአቸዋል።
፮ እናም በነጎድጓድና፣ በመብረቅ፣ በመሬት መናወጥና፣ በሁሉም አይነት ጥፋት፣ ይቀጣሉ፣ የጌታም የቁጣ እሳት በእነርሱ ላይ ይነዳልና፣ እናም እነርሱ እንደገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን እነርሱን ይበላል፣ ይላል የሰራዊት ጌታ።
፯ አቤቱ በህዝቤ ጥፋትና ሞት የተነሳ፣ የነፍሴ ስቃይ! እኔ ኔፊ አይቼዋለሁ፣ እና ይህም በጌታ ፊት ሊያጠፋኝ ደርሷልና፤ ነገር ግን መንገድህ ሀጻድቅ ነው ብዬ ወደ አምላኬ መጮህ አለብኝ።
፰ ነገር ግን እነሆ፣ ሀየስደት መከራ ቢደርስባቸውም የነቢያትን ቃል የሚሰሙ እናም የማያጠፏቸው፣ ነገር ግን የተሰጠውን ምልክት በመጠባበቅ በእምነት ፀንተው ክርስቶስን ወደ ፊት የሚመለከቱ ጻድቃኖች—እነሆ፣ እነርሱም ለየማይጠፉት ናቸው።
፱ ነገር ግን የፅድቅ ልጅ ሀይገለፅላቸዋል፤ ለይፈውሳቸዋልም፣ እናም ሐሶስት ትውልድ እስከሚያልፍ ድረስ በእርሱ መሰላም ይኖራቸዋል፣ ሠከአራተኛው ትውልድም ብዙዎች በፅድቅ ያልፋሉ።
፲ እናም እነዚህ ነገሮች በሚያልፉበት ጊዜ ፈጣን ሀጥፋት በህዝቤ ላይ ይመጣል፤ ምክንያቱም በነፍሴ ስቃይ ቢኖርም፣ ይህን አይቼዋለሁ፤ ስለዚህ፣ እንደሚሆንም አውቃለሁ፤ እናም እራሳቸውን ያለ ዋጋ ይሸጣሉ፤ ለኩራታቸውና ለሞኝነታቸው ጥፋትን ዋጋ ይቀበላሉና፤ ለዲያብሎስ እጃቸውን ስለሰጡ፣ እናም ከብርሃን ይልቅ የጨለማን ስራ ስለመረጡ፣ ስለዚህ ወደ ለሲኦል ሊወርዱ ይገባቸዋል።
፲፩ የጌታ መንፈስ ሁል ጊዜ ከሰው ጋር ሀአይቆይም። እናም መንፈስ ከሰው ጋር መስራት ሲያቆም ፈጣን ጥፋት ይመጣል፣ እናም ይህ ነፍሴን ያሳዝነዋል።
፲፪ እናም እኔ ሀአይሁዶችን ኢየሱስ፣ እንዲሁም ለያው ክርስቶስ፣ መሆኑን ሐለማሳመን ስናገር፣ አህዛቦችም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘለዓለማዊ አምላክ መሆኑን ሊረዱት ይገባቸዋል፤
፲፫ እናም እሱ በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ እራሱን ሀበመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይገልፃል፤ አዎን፣ ለሁሉም ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋና ህዝብ እንደ እምነታቸው በሰው ልጆች መካከል አስደናቂ ተአምራትን፣ ምልክትን፣ እና ድንቅ ነገርን ይሰራል።
፲፬ ነገር ግን እነሆ፣ እኔ ሀየመጨረሻ ቀናትን በተመለከተ ጌታ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች እነዚህን ነገሮች ለየሚያመጣባቸውን ቀናትም በተመለከተ እተነብይላችኋለሁ።
፲፭ ዘሮቼና የወንድሞቼ ዘሮች ባለማመን ከመነመኑና፣ በአህዛብ ከተመቱ በኋላ፤ አዎን፣ እግዚአብሔር በሰራዊቱ ከከበባቸውና፣ የግንብ ከለላ ካደረገላቸው በኋላ፣ ከሚዋጉአቸውም ከከለላቸው፤ እናም እስከሚጠፉም እንኳን፣ በትቢያም ዝቅ ካደረጋቸው በኋላ፣ ሆኖም የፃድቃን ቃል ይፃፋል፣ የታማኞች ፀሎትም ይሰማል፣ እናም ባለማመን የመነመኑትም ሁሉ አይረሱም።
፲፮ እነዚያ የሚጠፉት ከመሬት ሀይናገራሉ ቃላቸውም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፣ ድምጻቸውም ከመሬት እንደሚወጣ እንደመናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፤ ጌታ እግዚአብሔር እነርሱን በተመለከተ፣ ከመሬት ውስጥ እንደሆኑ ሁሉ፣ ያንሾካሽክ ዘንድ ኃይልን ይሰጠዋል፤ ቃላታቸውም ከአፈር ወጥተው ያንሾካሽካሉ።
፲፯ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና—በእነርሱ መካከል ስለሚደረጉት ነገሮች ሀይፅፋሉ፣ እናም ተፅፈውም በመጽሐፍ ይታተማሉ፣ እናም ባለማመን የመነመኑት አያገኟቸውም፣ ምክንያቱም እነርሱ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለማጥፋት ለይሻሉና።
፲፰ ስለሆነም፣ እነዚያ የሚጠፉት በፍጥነት ጠፍተዋል፤ እናም የጨካኞችም ብዛታቸው እንደሚያልፍ ሀገለባ ይሆናል—አዎን፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ይህም ፈጥኖ፣ በድንገትም ይሆናል—
፲፱ እናም እንዲህ ይሆናል፣ ባለማመን የመነመኑት በአህዛብ እጅ ሀይመታሉ።
፳ እናም አህዛብ በአይናቸው ሀኩራት ምክንያት ለተሰናክለዋል፣ እናም ሐበእንቅፋታቸው ትልቅነት የተነሳ ተሰናክለዋል፣ በዚህም ብዙ መቤተክርስቲያንን ሰርተዋል፤ ይሁን እንጂ፣ ጥቅም ያገኙበትና የድሆችን ፊት ሠይፈጩ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ኃይልና ተአምራት ንቀዋል፣ እናም የራሳቸውን ጥበብና ረትምህርት ለራሳቸው ሰብከዋል።
፳፩ እናም ሀምቀኝነት፣ ጭቅጭቅና ጥላቻ የሚያመጡ ብዙ ቤተክርስቲያኖች ተሰርተዋል።
፳፪ እናም እንደ ጥንቱም እንኳን ቢሆን፣ እንደ ዲያብሎስ ውህደት መሰረት አሁንም ደግሞ ሀሚስጥራዊ ሴራዎች አለ፣ የነዚህ ሁሉ ነገሮች መስራች እርሱ ነውና፤ አዎን፣ የግድያ እና የጨለማ ስራ መስራች፤ አዎን፣ ለዘለዓለም በጠንካራው ገመድ እስከሚያስራቸው፣ በተልባ ገመድ አንገታቸውን ይስባል።
፳፫ እነሆም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ጌታ እግዚአብሔር በጨለማ አይሰራም እላችኋለሁ።
፳፬ እርሱም ለዓለም ጥቅም ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም አያደርግም፤ ምክንያቱም ሰዎችን ሀሁሉ ወደ እርሱ ይስብ ዘንድም ሕይወቱን አሳልፎ እስከመስጠት ዓለምን ለይወዳል። ስለዚህ፣ ማንንም ደህንነቱን እንዳይካፈሉ አያዝም።
፳፭ እነሆ፣ ለሰው ከእኔ ራቁ ብሎ ተናግሯልን? እነሆ፣ እኔ እላችኋለሁ፣ አይደለም፤ ነገር ግን እርሱ እንዲህ ይላል—እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ እኔ ሀኑ፣ ያለገንዘብም ያለዋጋም ወተትና ማር ለግዙ።
፳፮ እነሆ፣ ከምኩራብ ወይም ከማምለኪያ ቤቶች ውጪ መውጣት እንዳለባቸው እርሱ አዟልን? እነሆ፣ እላችኋለሁ አላለም።
፳፯ ሀደህንነቱን እንዳይካፈሉ እርሱ አዝዟቸዋልን? እነሆ እኔ እላችኋለሁ—አላዘዛቸውም፤ ነገር ግን እርሱ ለሰዎች ሁሉ በነፃ ለሰጥቶታል፤ እናም እርሱ ህዝቡን ሁሉንም ሰዎች ሐንስሀ ለመግባት እንዲያሳምኑአቸው አዟል።
፳፰ እነሆ፣ ጌታ ከቸርነቱ እንዳይካፈሉ ያዘዘው አለ? እነሆ እኔ እላችኋለሁ—የለም፤ ነገር ግን ሀሁሉም ሰው እንደሌላው ታድሏል፤ እናም ማንም አልተከለከለም።
፳፱ የክህነት ተንኮል እንዳይኖር አዟል፣ እነሆም፣ ሀየክህነት ተንኮሎችም ጥቅምና ለሙገሳን ከአለም ያገኙ ዘንድ ሰዎች የሚሰብኳቸውና እራሳቸውን በዓለም ውስጥ በብርሃን የሚያስቀምጡበት ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የፅዮንን ደህንነት አይሹም።
፴ እነሆ፣ ጌታ ይህንን ነገር ይከለክላል፤ ስለዚህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሰው ሁሉ ለጋስ መሆን እንዳለበት ትዕዛዝን ሰጥቷል፣ ይህም ሀልግስና ለፍቅር ነው። እናም ለጋስነት ከሌላቸው ከንቱ ናቸው። ስለሆነም፣ ልግስና ቢኖራቸው የፅዮን ሰራተኞች እንዲጠፉ አይፈቅዱም ነበር።
፴፩ ነገር ግን ሀበፅዮን ያሉ ሰራተኞች ለፅዮን ይሰራሉ፤ ምክንያቱም ለለገንዘብ ከሰሩ ይጠፋሉና።
፴፪ እናም ጌታ እግዚአብሔር እንደገና ሰዎች መግደል እንደሌለባቸው፤ መዋሸት እንደሌለባቸው፤ መስረቅ እንደሌለባቸው፤ የጌታን ስም ሀበከንቱ መጥራት እንደሌለባቸው፤ እንዳይመቀኙ፤ ጥላቻ እንዳይኖራቸው፤ አንዱ ከሌላው እንዳይጣላ፤ ዝሙትን እንዳይፈፅሙ፤ እናም ከእነዚህ ውስጥ ማንኛውንም ማድረግ እንደሌለባቸው ለአዝዞአል፤ እነዚህን የሚፈፅሙ ይጠፋሉና።
፴፫ ከእነዚህ ማናቸውም ክፋቶች በጌታ አይመጡምና፤ እርሱ በሰው ልጆች መካከል መልካም የሆነውን ያደርጋልና፤ እናም ለሰዎች ልጆች ግልፅ ከሆነው በስተቀር ምንም አያደርግም፤ እርሱም ከቸርነቱ ይካፈሉ ዘንድ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል፤ እናም ወደ እርሱ የሚመጡትን ማንንም፣ ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውንና ነፃውን፤ ሴትና ወንድን ሀአይክድም፤ ለእምነተቢሶችንም ያስታውሳል፤ እናም አይሁድም ሆኑ አህዛብ፣ ሐሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው።