ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፳


ምዕራፍ ፳

የአሶር መጥፋት ኃጢአተኞች በዳግም ምፅአት እንደሚጠፉት ምሳሌ ነው—ጌታ እንደገና ከመጣ በኋላ ጥቂት ሰዎች ይቀራሉ—የያዕቆብ ቅሪቶች በዚያን ቀን ይመለሳሉ—ኢሳይያስ ፲ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

፩ ጻድቅ ያልሆኑ ሕጎችን ለሚደነግጉ፣ የጻፉአቸውን የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ ወዮላቸው፤

፪ ፍትህ የሚፈልጉትን ለመከልከል፣ እናም የድሃ ሕዝቦቼን መብት ለመውሰድ፣ መበለቶችንም ሰለባቸው እንዲሆኑላቸው፣ እናም አባት አልባዎችን ለመዝረፍ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት አዝዘዋል!

፫ እናም ከሩቅ በሚመጡት በመጎብኘታችሁና በመውደሚያችሁ ቀን ምን ታደርጋላችሁ? ለእርዳታስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዋታላችሁ?

፬ ከእኔ ውጭ ከእስረኞች በታች ይጎነበሳሉ፣ በሚገደሉትም መካከል ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳን ጌታ ቁጣው አልበረደችም፣ ነገር ግን አሁንም ገና እጁ ተዘርግታለች።

፭ ሶርያ ሆይ፣ የቁጣዬ በትር፣ እናም በእጃቸው ያለው መሳሪያ ቁጣቸው ነው።

፮ በግብዝ ሀገሮችም መካከል እልከዋለሁ፣ እናም ምርኮንና ብዝበዛውንም ይወስድ ዘንድ፣ እና እንደ አደባባይ ጭቃ የተረገጡ ይሆኑ ዘንድ በተቆጣሁአቸው ህዝብ ላይ እልከዋለሁ።

፯ ነገር ግን እርሱ ይህን አላቀደውም፣ ልቡም ቢሆን እንደዚህ አያስብም፤ በልቡ ውስጥ ያለው ግን ብዙ ሀገሮችን ለማጥፋትና ለመቁረጥ ነው።

፰ እንዲህ ይላል፥ መሳፍንቶቼ ሁሉ ነገሥታት አይደሉምን?

፱ ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማትስ እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?

፲ የተቀረፁ ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ ምስሎች የበለጡትን፣ የጣዖቶችን መንግስታት እጄ እንዳገኘች፤

፲፩ በሰማርያና በጣዖቶቿ እንደአደረግሁት በኢየሩሳሌምና በጣዖቶቿ አላደርግምን?

፲፪ ስለዚህ እንዲህ ይሆናል ጌታ ስራውን በሙሉ በፅዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ሲፈፅም፣ የአሶርን ንጉስ የኩሩ ልብ ፍሬውን የዐይኑንም ከፍታ ትምክህት እቀጣለሁ።

፲፫ እርሱ እንዲህ ብሎአልና፤ በእጄ ጥንካሬና በጥበቤ እነዚህን ነገሮች አድርጌአለሁ፤ እኔ አስተዋይ ነኝና፤ የህዝቦችንም ድንበር ገፋሁ፣ ሀብታቸውንም ዘረፍኩ፣ እናም እንደ ጀግና ሆኜ ፍጥረታትን አጠቃሁ፤

፲፬ እናም እጄ የህዝብን ሀብት እንደ ወፍ ጎጆ አገኘች፤ እና በሰው የተተዉትን እንቁላሎች እንደሚሰበስብ እኔም ደግሞ ምድርን በሞላ ሰበሰብኩ፤ ክንፉን የሚያራግብ፣ ወይም አፉን የሚከፍትም ሆነ የሚጮህ ማንም የለም።

፲፭ ምሳር የሚጠቀምበትን ሰው እበልጣለሁ ብሎ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ላይ እራሱን ያጎላልን? በትርስ በራሱ ያለእጅ እራሷን እንደምትነቀንቅ ወይንም ከዘራ እንጨት እንዳልሆነ ሁሉ እራሱን እንደሚያነሳ!

፲፮ ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ፣ በወፍራሞቹ ላይ መክሳትን ይልካል፣ ከክብሩም በታች እንደ እሳት መቃጠል የሆነ ቃጠሎን ያስነሳል።

፲፯ እናም የእስራኤል ብርሃን ለእሳት ይሆናል፣ ቅዱሷም ነበልባል ይሆናል፣ እሾሁንና ኩርንችቱንም በአንድ ቀን ያቃጥለዋል፣ ይበላዋልም፤

፲፰ እናም የዱሩንም፣ የፍሬያማውን ሜዳ፣ ክብሩንም፣ ነፍሱንና ስጋውንም ያቃጥለዋል፤ እነርሱ አርማ ተሸካሚው እንደ ወደቀ ይሆናሉ።

፲፱ እናም የተቀሩትም የዱር ዛፎቹ ህፃን መቁጠር እስኪችላቸው ድረስ ትንሽ ይሆናሉ።

፳ እናም በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፣ የእስራኤል ቅሪት፣ እናም ከያዕቆብ ቤት የዳኑት፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚያ በመታቸው ላይ አይቆዩም፣ ነገር ግን በጌታ በእስራኤሉ ቅዱስ በእውነት ይመካሉ።

፳፩ ቅሪቶች ይመለሳሉ፣ አዎን፣ የያዕቆብም ቅሪቶች ቢሆኑ እንኳ፣ ወደ ኃያሉ እግዚአብሔር ይመለሳሉ።

፳፪ እስራኤል ሆይ ህዝብሽ እንደ ባህር አሸዋ የበዛ ቢሆንም እንኳ፣ ቅሪቶቻቸው ይመለሳሉ፤ የተነገረውም ጥፋት በፅድቅ ይትረፈረፋል።

፳፫ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ያለቀ የተቈረጠ ነገርን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።

፳፬ ስለዚህ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል—በፅዮን የምትኖሩ ህዝቤ ሆይ፣ አሶርን አትፍራው፤ በበትር ይመታሀል፣ ግብፅም እንዳደረገው ዘንጉን ያነሳብሀል።

፳፭ ቁጣዬ እስኪፈፀም መዓቴም እስኪያጠፋቸው ጥቂት ጊዜ ቀርቷል።

፳፮ እናም የሰራዊት ጌታ ምድያምን በሔሬብ አለት በኩል እንደመታው ጅራፍ ያነሳበታል፣ በትሩም በባህር ላይ ይሆናል፣ በግብፅም እንዳደረገው ያነሳዋል።

፳፯ እናም እንዲህ ይሆናል፣ በዚያን ቀን ሸክሙ ከትከሻህ ላይ ይነሳል፣ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፣ ከቅባቱም የተነሳ ቀንበሩም ይጠፋል።

፳፰ ወደ አንጋይ መጥቷል፣ በሜጌዶን አልፏል፤ በማክማስም እቃውን አስቀምጧል።

፳፱ እነርሱ መተላለፊያውን አልፈዋል፤ ማረፊያቸውንም በጌባ አድርገዋል፤ ራማትም ፈርታለች፤ የሳኦል ጊብአም አምልጣለች።

፴ የጋሊም ልጅ ሆይ፤ ደሀዋ አናቶት ሆይ፣ ለሌሳ እንኳን እስኪሰማ ድረስ ድምፅሽን ከፍ አድርጊ።

፴፩ መደቤና ሸሽታለች፤ የግቤር ህዝቦችም ሊያመልጡ እራሳቸውን ሰብስበዋል።

፴፪ ነገር ግን በዚያን ቀን በኖብ ላይ ይቀራል፤ በፅዮን ሴት ልጆች ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጆቹን ያነቃንቃል።

፴፫ እነሆ፣ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ ቅርንጫፎቹን በሚያስፈራ ኃይል ይቆርጣቸዋል፤ እናም በቁመናቸው ከፍ ያሉት ይቆረጣሉ፤ እብሪተኞቻቸው ዝቅ ይላሉ።

፴፬ ጥቅጥቅ ያለውንም ጫካ እርሱ በብረት ይቆርጠዋል፣ ሊባኖስም በኃይለኛው እጅ ትወድቃለች።

      • ይህም ቅጣት ማለት ነው።

      • ኢሳ. ፲፥፭።

      • ይህም እስራኤልን የሚቃወም ማለት ነው።

      • ሶፎ. ፪፥፲፫።

      • ይህም በኩራት ማጉራት ማለት ነው።

      • ይህም ንጉሱ እግዚአብሔርን በመቃወም ይበለጽጋልን? ማለት ነው።

      • በዚህ ቁጥር ውስጥ ያሉ ምሳሌዎች አንድ አይነት ጥያቄ ይጠይቃሉ፥ ሰም (ለምሳሌ የአሶር ንጉስ) እግዚአብሔርን በመቃወም ሊበለፅግ ይችላል?

      • ይህም አሶር በሙሉ ትጠፋለች ማለት ነው።

      • ይህም የቀሩት የአሶር ጦር ሰራዊት ማለት ነው።

      • ይህም በኋለኛው ቀናት ማለት ነው።

      • ዓሞ. ፱፥፰–፱።

      • ይህም መመካት ማለት ነው።

      • ኢሳ. ፲፩፥፲፩–፲፪።

      • ይህም የታወጀውን ጥፋት አመጣ ማለት ነው።

      • ይህም ግብጻውያን ወደፊት እንደሚያደርጉት ማለት ነው። ዘፀአ. ፩፥፲፫–፲፬።

      • ዘፍጥ. ፳፭፥፩–፪፤ መሳ. ፯፥፳፭።

      • ይህም የአሶር ጦር ሰራዊት ወደ እስራኤል ጉዞን እየተከተሉ ነው፤ ከእዚያም (ቁጥሮች ፴፫–፴፬) በእነርሱ ላይ ጌታ የሚያደርገው በምሳሌ ተገልጸዋል ማለት ነው።