ምዕራፍ ፴፬
አሙሌቅ ቃሉ ለቤዛነታቸው በክርስቶስ ውስጥ መሆኑን መሰከረ—የኃጢያት ክፍያው ካልተደረገ፣ የሰው ዘር ሁሉ መጥፋት ነበረበት—የሙሴ ህጎች በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ልጅ መስዋዕትነት ይጠቁማሉ—ዘለዓለማዊው የደህንነት ዕቅድ የተመሰረተው በእምነት እና በንስሃ ላይ ነው—ለጊዜያዊውና ለመንፈሳዊው በረከት ፀልዩ—ይህ ህይወት ሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት የሚዘጋጁበት ወቅት ነው—በእግዚአብሔር ፊት በፍርሀት የ ራሳችሁን ደህንነት አከናውኑ። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ እነዚህን ቃላት ከተናገራቸው በኋላ በመሬት ላይ ተቀምጦ ነበር፣ እናም ሀአሙሌቅ ተነሳና፣ እንዲህ በማለት እነርሱን ማስተማር ጀመረ፥
፪ ወንድሞቼ እንደማስበው የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ ያስተማርናችሁን የክርስቶስን መምጣት በተመለከተ የተነገሩትን ችላ ማለት የማይቻል ነው፤ አዎን፣ ከእኛ ከመለየታችሁ በፊት ሀእነዚህን ነገሮች በይበልጥ እንደተማራችሁት አውቃለሁ።
፫ እናም በስቃያችሁ የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እንዲያሳውቃችሁ የተወደደውን ወንድሜን ለመጠየቅ በመፈለጋችሁና፣ እርሱ የ ራሳችሁን አዕምሮ እንድታዘጋጁ በመጠኑ ተናግሯል፤ አዎን እናም እምነትና ትዕግስት እንዲኖራችሁ መክሯችኋል—
፬ አዎን፣ የመልካምነቱን ልምምድ እንድትሞክሩት ዘንድ፣ ታላቅ እምነት ኖሯችሁ ቃሉን በልባችሁ ሀእንድትተክሉትም መክሯችኋል።
፭ እናም ቃሉ በእግዚአብሔር ልጅ ውስጥ መኖሩን፣ ወይም ክርስቶስ እንደሌለ ያላችሁን ታላቅ ጥያቄ በአዕምሮአችሁ ውስጥ እንደሆነ ተመልክተናል።
፮ እናም በብዙ ማስረጃዎች ሀቃሉ ደህንነት በክርስቶስ ውስጥ መሆኑን ወንድሜ እንዳረጋገጠላችሁ ደግሞም ተመልክታችኋል።
፯ ወንድሜም ቤዛነት በእግዚአብሔር ልጅ አማካኝነት እንደሚመጣ የዜኖስን ቃል፣ እናም ደግሞ የዜኖቅን ቃል፣ በመጥቀስ ተናገረ፤ እናም ደግሞ እነዚህ ነገሮች እውነት መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሙሴን ቃላት ጠቀሰ።
፰ እናም አሁን፣ እነሆ፣ እኔ ራሴ እነዚህ ነገሮች እውነት መሆናቸውን ሀእመሰክራለሁ። እነሆ፣ እንዲህም እላችኋለሁ፥ ክርስቶስ የህዝቡን መተላለፍ በእራሱ ላይ ለመሸከም በሰው ልጆች መካከል እንደሚመጣ፣ እናም ለዓለም ለኃጢያት ክፍያን እንደሚከፍል አውቃለሁ፤ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።
፱ የኃጢያት ክፍያ መኖሩ አስፈላጊ ነውና፤ ሀበዘለአለማዊው አምላክ ታላቅ ዕቅድ መሰረት ለየኃጢያት ክፍያ መኖር አለበት፤ አለበለዚያ የሰው ዘር ሁሉ መጥፋት እንዳለባቸው የማይቀር ነበር፤ አዎን ሁሉም ጠጣሮች ናቸው፤ አዎን ሁሉም ሐወድቀዋልና ጠፍተዋል፣ እናም መፈጸሙ አስፈላጊ ከሆነው ከኃጢያት ክፍያ በቀር መጥፋት አለባቸው።
፲ ታላቅ እና የመጨረሻ ሀመስዋዕትነት መኖሩ አስፈላጊ ነውና፤ አዎን፣ የሰውም ሆነ የእንሰሳ እንዲሁም የማንኛውም አዕዋፍ መስዋዕትነት አይደለም፤ ምክንያቱም የሰው መስዋዕትነት መሆን አይገባውም፤ ነገር ግን ለመጨረሻ የሌለው እንዲሁም ዘለአለማዊ ሐመስዋዕት መሆን ይገባዋል።
፲፩ እንግዲህ ለሌላኛው እንደ ኃጢያቶች ክፍያ ደሙን መስዋዕት ሊያደርግ የሚችል ማንም ሰው የለም። እንግዲህ፣ አንድ ሰው ከገደለ እነሆ ሀፍፁም የሆነው ህጋችን የወንድሙን ህይወት ያጠፋልን? እኔ ግን አይሆንም እላለሁ።
፲፪ ነገር ግን ህጉ ሀየገደለውን ሰው ህይወት ይጠይቃል፤ ስለዚህ ለዓለም ኃጢያት ወሰን ከሌለው የኃጢያት ክፍያ በስተቀር ሊበቃ የሚችል ምንም የለም።
፲፫ ስለዚህ፣ ታላቅና የመጨረሻ መስዋዕትነት መኖሩ አስፈላጊ ነው፤ እናም የደም መፋሰሱ ሀመቆም መሆን አለበት፣ እንዲሁም መሆኑ አስፈላጊ ነው፤ ከዚያም ለየሙሴ ህግ ይፈፀማል፤ አዎን፣ እያንዳንዱ ነጥብና ምልክት በሙሉ ይፈፀማል፣ እናም የትኛውም ሳይከናወን አይቀርም።
፲፬ እናም እነሆ፣ ይህ እያንዳንዱ ትንሽ ክፍል ወደ ታላቁና የመጨረሻ ሀመስዋዕት የሚጠቁምበት አጠቃላይ ለየህጉ ሐትርጓሜ ነው፤ እናም የታላቁና የመጨረሻ መስዋዕትነት የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፤ አዎን፣ መጨረሻ የሌለውና ዘለዓለማዊ የሆነው።
፲፭ በዚህም በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ ሀደህንነትን ያመጣል፤ የዚህ የመጨረሻው መስዋዕት ዓላማ ከፍትህ የሚልቀውን ከአንጀት የሆነን ምህረትን ለማምጣት ነው፤ እንዲሁም ለሰዎች በንስሃ እምነት ይኖራቸው ዘንድ መፍትሄ ለማምጣት ነው።
፲፮ እናምእንደዚህም ሀምህረት ለየፍትህን ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል፣ እናም በጠባቂ ክንዶቹ ይከባቸዋል፤ እምነትንም ንስሃ በመግባት ያልተለማመደ ሐፍትህ ለሚፈልግበት ህግጋት ሁሉ የተጋለጠ ይሆናል፤ ስለዚህ ለንስሃ እምነት ላለው ብቻ ታላቁና መየዘለዓለማዊው ዕቅድ ቤዛነት እንዲመጣ የሚሆነው።
፲፯ ስለዚህ ወንድሞቼ ለንስሃ ሀእምነታችሁን መለማመድ ትጀምሩ ዘንድ፣ በእናንተም ላይ ምህረት እንዲኖረው ቅዱስ ስሙን ለመጥራት ትጀምሩ ዘንድ እግዚአብሔር ለእናንተ ይፍቀድላችሁ፤
፲፰ አዎን፣ ለምህረት ወደ እርሱ ጩኹ፤ ምክንያቱም እርሱ ለማዳን ኃያል ነውና።
፲፱ አዎን፣ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፣ እናም ወደ እርሱ ፀሎታችሁን አታቋርጡ።
፳ በመስካችሁ ሳላችሁ ወደ እርሱ ጩኹ፤ አዎን በመንጋዎቻችሁ ሁሉ ላይ።
፳፩ በቤታችሁ፣ አዎን፣ በቤተሰዎቻችሁ ላይ፣ በጠዋት፣ በቀን እንዲሁም በምሽት ወደ እርሱ ሀጩኹ።
፳፪ አዎን፣ የጠላቶቻችሁን ኃይል በመቃወም ወደ እርሱ ጩኹ።
፳፫ አዎን፣ ሀየፅድቅ ሁሉ ጠላት የሆነውን ለዲያብሎስን በመቃወም ወደ እርሱ ሐጩኹ።
፳፬ በእርሻችሁ እህሎች ትበለጽጉ ዘንድ ወደ እርሱ ጩኹ።
፳፭ በመስኩ ላይ ያሉት መንጎቻችሁ ይበዙላችሁ ዘንድ ስለእነርሱ ጩኹ።
፳፮ ነገር ግን ይህ ብቻም አይደለም፤ ነፍሳችሁን ሀበእልፍኞቻችሁ፤ እናም በሚስጥር ቦታዎቻችሁ እንዲሁም በምድረበዳው አፍስሱ።
፳፯ አዎን፣ እናም ወደ ጌታ በማትጮኹበት ጊዜ፣ ሀልባችሁ ለደህንነታችሁና፣ ደግሞ በዙሪያችሁ ላሉት ደህንነት ባለማቋረጥ በፀሎት ወደ እርሱ በመትጋት ለሙሉ ይሁን።
፳፰ እናም አሁን እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ይህ ብቻ ነው ብላችሁ አትገምቱ፤ ምክንያቱም ይህንን ነገር በሙሉ ካደረጋችሁ በኋላ፣ ሀየተቸገሩትንና፣ የታረዙትን ካልረዳችሁ፣ እናም የታመሙትንና የተሰቃዩትን ካልጎበኛችሁና፣ እያላችሁ ለሚሹት ካላችሁ ነገር ለካላካፈላችሁ—እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፥ ከእነዚህ ነገሮች የትኛውንም ካላደረጋችሁ፣ እነሆ፣ ሐፀሎታችሁ መከንቱ ነው፣ እናም ለእናንተ የሚጠቅማችሁ ምንም የለም፤ እናንተም እምነትን እንደሚከዱት ግብዞች ናችሁ።
፳፱ ስለዚህ፣ ሀቸር መሆንን ካላስታወሳችሁ፣ (ምክንያቱም ዋጋ ቢስ ነውና) አጣሪዎቹ እንደሚጥሉዋቸው እናም በሰዎች እግር እንደሚረገጡ አተላ ናችሁ።
፴ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ ብዙ ምስክሮችን ከተቀበላችሁ በኋላ፣ ቅዱሳን መጻሕፍት እነዚህን ነገሮች እንደሚመሰከሩላችሁ እያያችሁ፣ እንድትመጡና ለንስሀ ብቁ የሆነ ሀፍሬ እንድታመጡ ፍላጎቴ ነው።
፴፩ አዎን፣ እናንተ እንድትመጡና፣ ከእንግዲህ ልባችሁን እንዳታጠጥሩ እፈልጋለሁ፤ እነሆም አሁን ሀየደህንነታችሁ ጊዜና ቀን ነው፤ እናም ስለዚህ ንስሃ የምትገቡ ከሆነና፣ ልባችሁን የማታጠጥሩ ከሆነ፣ ታላቁ የቤዛነት ዕቅድ በፍጥነት በእናንተ ላይ ይሆናል።
፴፪ እነሆም፣ ይህ ጊዜ ለሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት ሀየዝግጅት ወቅት ነው፤ አዎን፣ እነሆ የዚህ ህይወት ቀናት ሰዎች ስራቸውን የሚያከናውኑባቸው ቀናቶች ናቸው።
፴፫ እናም አሁን፣ ለእናንተ ብዙ ምስክር እንዳላችሁ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት፣ ስለዚህ እስከመጨረሻው ድረስ ሀየንስሃ ቀናችሁን ለእንዳታዘገዩ እለምናችኋለሁ፤ ለዘለዓለማዊው ህይወት እንድንዘጋጅ ከተሰጠን ከዚህ የህይወት ቀን በኋላ፣ እነሆ፣ በዚህ ህይወት ውስጥ ጊዜያችንን በተሻለ ካልተጠቀምን፣ ከዚያም ስራ ለመስራት የማንችልበት ሐየጨለማ መምሽት ይመጣል።
፴፬ ወደ አሰቃቂው ሀሁኔታ ስትመጡም፣ ንስሃ እገባለሁ፣ እናም ወደ አምላኬ እመለሳለሁ ለማለት አትችሉም። እንደዚህም ለማለት አትችሉም፤ ከዚህ ህይወት በምትወጡ ጊዜ እናንተን የእራሱ ያደረገው ይኸው መንፈስ በዘለዓለማዊው ዓለም እናንተን የእራሱ ለማድረግ ስልጣን ይኖረዋል።
፴፭ እነሆም እስክትሞቱ ድረስ የንስሃ ቀናችሁን የምታዘገዩ ከሆነ፣ እነሆ፣ ለዲያብሎስ መንፈስ ሀተገዢ ትሆናላችሁና፣ የእራሱ አድርጎ ለያትምባችኋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር መንፈስ ከውስጣችሁ ይወጣልና፣ በእናንተ ውስጥ ስፍራ አይኖረውም፣ እንዲሁም ዲያብሎስ በእናንተ ላይ ሁሉም ስልጣን ይኖረዋል፤ እናም የኃጢአተኞች የመጨረሻ ሁኔታ ይህ ነው።
፴፮ እናም ይህን ያወቅሁት ሀበረከሰ ቤተመቅደስ እንደማይኖር፣ ነገር ግን ለበፃድቃኖች ልብ ውስጥ እንደሚያድር ጌታ ስለተናገረ ነው፤ አዎን፣ እናም ደግሞ ፃድቃኖች በመንግስቱ እንደሚቀመጡ፣ ከዚያም ደግሞ እንደማይወጡ ተናግሯል፤ ነገር ግን በበጉ ደም ልብሳቸው ይጸዳል።
፴፯ እናም አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እነዚህን ነገሮች እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ፣ እናም በእግዚአብሔር ፊት በፍርሃት ደኅንነታችሁን ሀእንድትፈፅሙና፣ የክርስቶስን መምጣት ከእንግዲህ እንዳትክዱ እፈልጋለሁ፤
፴፰ ከእንግዲህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሀእንዳትጣሉም፣ ነገር ግን እንድትቀበሉትና፣ ለየክርስቶስን ስም በእራሳችሁ ላይ እንድትወስዱት፤ ራሳችሁን እስከትቢያው ድረስ ዝቅ እንድታደርጉና፣ ባላችሁበት ስፍራ ሁሉ በመንፈስና በእውነት እግዚአብሔርን ሐእንድታመልኩ፤ እናም በየቀኑ በእናንተ ላይ ባደረገው ስለበዛው ምህረቱና በረከቱ መበምስጋና እንድትኖሩ እፈልጋለሁ።
፴፱ አዎን፣ እናም ደግሞ ወንድሞቼ በዲያብሎስ ሀፈተናም እንዳትወሰዱ፣ እርሱም በእናንተ ላይ ስልጣን እንዳይኖረው፣ በመጨረሻው ቀንም በእርሱ ስር እንዳትሆኑ ያለማቋረጥ ለእንድትፀልዩ እመክራችኋለሁ፤ እነሆ እርሱ ሐምንም መልካም ነገር ዋጋ አይሰጣችሁምና።
፵ እናም አሁን የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሀትዕግስት እንዲኖራችሁና፣ ስቃያችሁን ሁሉ እንድትታገሱ እመክራችኋለሁ፤ እጅግ ድሆች በመሆናችሁ ከአስወጧችሁም ላይ አጥብቃችሁ ለአትነቅፉ፣ ያለበለዚያ እንደእነርሱም ኃጢአተኞች ትሆናላችሁና፤
፵፩ ነገር ግን ትዕግስት ይኑራችሁ፣ እናም አንድ ቀን ከስቃያችሁ ሁሉ እንደምታርፉ ተስፋ በማድረግ ስቃያችሁን ታገሱ።