አልማ ፮
  Footnotes

  ምዕራፍ ፮

  በዛራሄምላ ያለው ቤተክርስቲያን ከኃጢያት ጠርቷል እናም ተደራጅቷል—አልማ ለመስበክ ወደ ጌዴዎን ሄደ። ፹፫ ም.ዓ. ገደማ።

  እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ በዛራሔምላ ከተማ ለተቋቋመው ቤተክርስቲያን ሰዎች ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ስርዓት መሰረት ቤተክርስቲያኗን እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ እጁን በመጫን ካህናትን እና ሽማግሌዎችን ሾመ

  እናም እንዲህ ሆነ ከቤተክርስቲያኗ ያልሆኑ ለኃጢአታቸው ንስሐ የገቡት ወደ ንስሐ ተጠምቀው እናም በቤተክርስቲያኗ ተቀባይነትን አግኝተው ነበር።

  እናም ደግሞ እንዲህ ሆነ ከቤተክርስቲያኗ የሆኑ ለኃጢአታቸው ንስሐ ያልገቡ እናም በእግዚአብሔር ፊት እራሳቸውን ዝቅ የማያደርጉ ሁሉ—ማለትም በልባቸው ኩራት የተወጠሩ—እንደነዚህ ዓይነቶቹ ተቀባይነትን አላገኙም ነበር፣ እናም ስማቸው ተሰርዘዋል፣ ስማቸው ከፃድቃኖች ጋር አልተቆጠረም ነበር።

  እና እንደዚህም በዛራሔምላ ከተማ የቤተክርስቲያኗን ስርዓት መመስረት ጀመሩ።

  አሁን የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም በነፃ እንደተሰጠ እንድትረዱ እፈልጋለሁ፣ ማንም እራሱን በአንድ ላይ በመሰብሰብ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ልዩ መብቱን የሚከለክለው የለም።

  ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች እራሳቸውን በአንድ ላይ ሁልጊዜ እንዲሰበስቡ፣ እናም በአንድ ላይ በመሆን እግዚአብሔርን ለማያውቁት ነፍሳት ደህንነት እንዲፆሙና እንዲፀልዩ ታዘዋል።

  እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ እነዚህን ህጎች ባዘጋጀ ጊዜ ከእነርሱ፣ አዎን፣ በዛራሔምላ ከተማ ከሚገኘው ቤተክርስቲያን፣ ተለይቶ ሄደ፣ እናም በጌዴዎን ሸለቆ፣ ከሲዶም ወንዝ በስተምስራቅ በኩል ጌዴዎን ተብላ ወደ ምትጠራውና በዚያም ወደታነፀች ከተማ፣ ጌዴዎን ተብሎ ወደ ሚጠራው ሸለቆ ሄደ፣ ስፍራውም ኔሆር በተባለው ሰው እጅ በተገደለው ስም የሚጠራ ነበር።

  እናም አልማ ሄደና፣ በአባቶቹ በተነገረው በቃሉ እውነታ ራዕይ መሰረትና፣ በውስጡ ባለው የትንቢት መንፈስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው፣ ህዝቡን ከኃጢያት ለማዳን በሚመጣውና በኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት መሰረትና፣ በተጠራበትም ቅዱሱ ስርዓት፣ በጌዴዎን ሸለቆ ለተቋቋመችው ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ ጀመረ። እናም እንዲሁ ተፅፏል። አሜን።