አልማ ፶፫
  Footnotes

  ምዕራፍ ፶፫

  የላማናውያን እስረኞች የለጋስን ምድር እንዲመሽጓት ጥቅም ላይ ውለዋል—በኔፋውያን መካከል የነበረው አለመስማማት ላማናውያን እንዲያሸንፉ አደረገ—ሔለማን በሁለት ሺህ የአሞን ህዝብ ብላቴና ወንዶች ላይ ባለስልጣል ሆነ። ከ፷፬–፷፫ ም.ዓ. ገደማ።

  እናም እንዲህ ሆነ ኔፋውያን በላማናውያን እስረኞች ላይ ጠባቂዎችን አስቀመጡ፣ እናም እነርሱ እንዲሄዱና፣ የእራሳቸውን ሙታን፣ አዎን፣ እናም ደግሞ የተገደሉትን ኔፋውያንን እንዲቀብሩ አስገደዱአቸው፤ ሞሮኒም እነርሱ ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ እንዲጠብቁአቸው ሰዎችን አስቀመጠ።

  እናም ሞሮኒ ከሌሂ ጋር ወደ ሙሌቅ ከተማ ሄደና፣ የከተማዋን ስልጣን ወሰደና ለሌሂ ሰጠው። እናም እነሆ፣ ይህ፣ ሌሂም፣ ከሞሮኒ ጋር በጦርነቱ በአብዛኛው ክፍል የነበረ ነው፤ እናም ሌሂ እንደ ሞሮኒ ዓይነት ሰው ነበር፣ ሁለቱም ለየራሳቸው በሚያደርጉት ጥበቃ ተደሰቱ፤ አዎን፣ እርስ በእርስም ይዋደዱ ነበር፤ ደግሞም በኔፊ ህዝብ ሁሉ ይወደዱ ነበር።

  እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን ከእነርሱ ወገን የሞቱትን፣ እናም ደግሞ ከኔፋውያን የሞቱትን ቀብረው ከጨረሱ በኋላ፤ ወደ ለጋስም ምድር ተመልሰው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እናም ቴአንኩም፣ በሞሮኒ ትዕዛዛት፣ እነርሱ ጉድጓዶችን በምድሪቱ ዙሪያ እንዲሁም በለጋስ ከተማ በመቆፈር ስራ እንዲጀምሩ አደረገ።

  እናም ለከተማዋ ቅርብ በሆነው ወንዝ ዳርቻ በጉድጓዱ በኩል ከእንጨት አጥር እንዲሰሩ አደረገ፤ እናም በእንጨት በተሰራው አጥር ላይም ከጉድጓዱ አፈር በማውጣት አስቀመጡ፤ እናም እንደዚህ ላማናውያንን ለጋስን ምድርና ዙሪያውን በጠንካራ እንጨት አጥርና አፈር ትልቅ ከፍታም እንዲኖረው እስከሚያደርጉ ድረስ እንዲሰሩ አደረጓቸው።

  እናም ይህች ከተማም ከዚህም በኋላ እጅግ ጠንካራ ምሽግ ሆነች፤ በዚህችም ከተማ፣ አዎን፣ በራሳቸው እጅ እንዲሰሩ በአደረጉአቸው ግንብ ውስጥ የላማናውያን እስረኞችን ጠበቁ። እንግዲህ ላማናውያን እስረኞች በሚሰሩበት ወቅት መጠበቅ ቀላል በመሆኑ ሞሮኒ ላማናውያንን እንዲያሰራቸው ተገዶ ነበር፣ እናም በላማናውያን ላይ ጥቃት በሚያደርግ ጊዜ ጦሩ በሙሉ ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ ፈልጎ ነበር።

  እናም እንግዲህ ሞሮኒ ታላቅ ከሆኑት የላማናውያን ሠራዊቶች በአንዱ ላይ ድልን ተቀዳጅቶ ነበር፤ እናም በኔፊ ምድር የላማናውያን ጠንካራ ምሽግ የነበረውን የሙሌቅን ከተማ አግኝቷል፤ እናም እስረኞችን ለመጠበቅም ደግሞ ጠንካራ ምሽግ እንደዚህ ሰርቷል።

  እናም እንዲህ ሆነ በዚያን ዓመት ከላማናውያን ጋር ጦርነትን አልሞከረም ነበር፤ ነገር ግን የራሱን ሰዎች ለጦርነት እንዲዘጋጁ፤ አዎን፣ እናም ከላማናውያንም ለመጠበቅ ምሽግን እንዲሰሩ፤ አዎን፣ እናም ደግሞ ሴቶቻቸውና ልጆቻቸውን ከረሃብና ከስቃይ እንዲወጡና፣ ለወታደሮቻቸው ምግብ እንዲያገኙ አስደርጓል።

  እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ በባህሩ በስተምዕራብ በደቡብ በኩል ሞሮኒ በሌለበት፣ በኔፋውያን መካከል በነበረው አለመስማማት በመካከላቸው መለያየት እንዲፈጠር በመደረጉ፣ አዎን፣ በዚያች ምድር ክፍል የነበሩትን ከተሞች እስከሚያገኙ ድረስ የላማናውያን ወታደሮች በኔፋውያን ላይ ጥቂት ብልጫን አገኙ።

  እናም በመካከላቸው በነበረው ክፋት የተነሳ፤ አዎን፣ በነበረው መለያየትና ሴራ እጅግ አደገኛ በሆነ ሁኔታ ነበሩ።

  እናም አሁን እነሆ፣ በመጀመሪያ ላማናውያን ስለነበሩት የአሞን ሰዎች የምናገረው አንድ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን በአሞንና በወንድሞቹ፣ ወይንም በእግዚአብሔር ቃልና ኃይል፣ ወደ ጌታ ተለውጠዋል፤ እናም ወደ ዛራሔምላ ምድር ተወስደዋል፣ እና በኔፋውያን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተጠብቀዋል።

  ፲፩ እናም በመሃላቸው ምክንያት በወንድሞቻቸው ላይ የጦር መሳሪያዎቻቸውን ከመውሰድ ተቆጥበዋል፤ ከዚህ በኋላ በጭራሽ ደም ላለማፍሰስ መሃላን ሰጥተው ነበር፤ እናም በመሀላቸው ምክንያት ይጠፉም ነበር፤ አዎን፣ አሞንና ወንድሞቹ ለህዝቡ ሩህሩህና ታላቅ ፍቅር ባይኖራቸው ኖሮ እራሳቸውን በወንድሞቻቸው እጅ እንዲወድቁ ባደረጉነበር።

  ፲፪ እናም በዚህ የተነሳ ወደ ዛራሔምላ ምድር ተወስደው ነበር፣ እናም በኔፋውያን ያለማቋረጥ ተጠበቁ

  ፲፫ ነገር ግን እንዲህ ሆነ አደጋውንና፣ ስቃዩን፣ እናም ለእነርሱ ሲሉ ኔፋውያን የደረሰባቸውን መከራ በተመለከቱ ጊዜ አዘኑ፣ እናም ሀገራቸውን ለመከላከል የጦር መሳሪያዎቻቸውን በማንሳት ለመዋጋት ፈለጉ

  ፲፬ ነገር ግን እነሆ፣ የጦር መሳሪያዎቻቸውን ለማንሳት ሲሉም፣ በሔለማንና ወንድሞቹ ማግባባት ተሸነፉ፣ ምክንያቱም የገቡትን መሃላ ለማፍረስ ተቃርበው ነበርና።

  ፲፭ እናም ሔለማን ይህንን በማድረጋቸው ነፍሳቸውን ያጣሉ ብሎ ፈርቶ ነበር፤ ስለዚህ ወደዚህ ቃል ኪዳን የገቡ ሁሉ በዚህ ጊዜ በአደገኛው ሁኔታ ላይ ያሉትን የወንድሞቻቸውን ስቃይ እንዲመለከቱ ተገድደው ነበር።

  ፲፮ ነገር ግን እነሆ፣ እንዲህ ሆነ እነርሱ ከጠላቶቻቸው ለመከላከል የጦር መሳሪያዎቻቸውን ላለማንሳት ወደቃል ኪዳኑ ያልገቡ ብዙ ወንድ ልጆች ነበሯቸው፣ ስለዚህ በዚህ ጊዜ የጦር መሳሪያዎቻቸውን ለማንሳት የሚችሉ ሁሉ እራሳቸውን ሰብስበው፣ እናም እራሳቸውን ኔፋውያን ብለው ጠሩ።

  ፲፯ እናም ለኔፋውያን ነፃነት ለመዋጋት ቃል ኪዳን ገቡ፤ አዎን፣ ህይወታቸውን እስከማጣት ድረስ ሀገራቸውን ለመከላከል፤ አዎን፣ ነፃነታቸውን አሳልፈው በጭራሽ እንደማይሰጡ፣ ነገር ግን በሁሉም ሁኔታዎች ኔፋውያንን እናም እራሳቸውን ከባርነት ለመከላከል እንደሚዋጉ ቃል ገብተዋል።

  ፲፰ እናም እነሆ፣ ሁለት ሺህ የሚሆኑ ወጣት ወንዶች ቃል ኪዳን ገብተዋል፣ እናም ሀገራቸውን ለመከላከል የጦር መሳሪያዎቻቸውን አነሱ።

  ፲፱ እናም አሁን እነሆ፣ ከዚህ በፊት ኔፋውያንን ፈፅሞ ጉዳት ያልነበሩ ቢሆኑም በዚህ ጊዜ ደግሞ ታላቅ ረዳት ሆኑላቸው፤ ምክንያቱም የጦር መሳሪያዎቻቸውን ወስደዋል፣ እናም ሔለማን መሪያቸው እንዲሆንም ፈልገዋል።

  እናም ሁሉም ወጣት ወንዶች ነበሩና፣ በድፍረትም፣ እናም ደግሞ በብርታትና በእንቅስቃሴአቸው በጣም ጀግኖች ነበሩ፤ ነገር ግን እነሆ ይህ ብቻም አልነበረም—በሁሉም ጊዜ በተሰጣቸው በማንኛውም ነገር ታማኝ ሰዎች ነበሩ።

  ፳፩ አዎን የእውነት እና የጥሞና ሰዎች ነበሩ፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዲጠብቁና በፊቱም በቅንነት እንደሚራመዱ ተምረዋልና።

  ፳፪ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ሔለማን በምድሪቱ በደቡብ በባህሩ በምዕራብ በኩል ግንባር ያሉትን ሰዎች ለመርዳት ከሁለት ሺህዎቹን ብላቴና ሠራዊት በመምራት ዘመተ።

  ፳፫ እናም በኔፊ ህዝብ ላይ የመሣፍንቱ ሀያ ስምንተኛ የንግስና ዘመን ተፈፀመ።