አልማ ፳፫
  Footnotes

  ምዕራፍ ፳፫

  የኃይማኖት ነፃነት ታወጀ—በሰባት ምድሮች እና ከተሞች ያሉ ላማናውያን ተለወጡ—እራሳቸውንም አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች- ሌሂ ብለው ጠሩ፣ እናም ከእርግማኑ ነፃ ወጥተዋል—አማሌቂውያንና አሙሎናውያን እውነትን አልተቀበሉም። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

  እነሆ እንግዲህ እንዲህ ሆነ የላማናውያን ንጉስ በአሞን፣ በአሮን፣ በኦምነር፣ በሂምኒ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል በማንኛውም ቦታ በየትኛውም በምድሪቱ ክፍል ለመስበክ በሚሄዱት ወንድሞቻቸው ላይ እጃቸውን እንዳይጭኑ በህዝቦቹ ሁሉ መካከል አዋጅ ላከ።

  አዎን፣ ለማሰር እጃቸውን በእነርሱ ላይ በማድረግ ወይንም በወህኒ ቤት እንዳይጥሏቸው፣ ወይም እንዳይተፉባቸውም፣ እንዳይመቱአቸውም፣ ከምኩራባቸው እንዳያባርሩአቸውም፣ እንዳይገርፉአቸውም፣ ድንጋይም እንዳይወረውሩባቸውም፣ ነገር ግን ወደቤቶቻቸው እናም ደግሞ ወደ ቤተመቅደሶቻቸውና ወደተቀደሱት ስፍራዎቻቸው ውስጥ ለመግባት ነጻ ፍቃድ እንዲኖራው በመካከላቸው አዋጅ ላከ።

  እናም እንደዚህ እንደፍላጎታቸውም የጌታን ቃል እንደፍላጎታቸው ለመስበክ ይሄዱ ዘንድ፣ ምክንያቱም ንጉሱና ቤተሰቦቹ ወደጌታ ተለውጠዋልና፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል የሚከላከለው እንዳይኖርበት ነገር ግን በምድሪቱ ላይ በሙሉ እንዲሆን፣ ህዝቡም መጥፎውን የአባቶቻቸውን ወግ ለማሳመን፣ እናም ሁሉም የእርስ በርስ ወንድሞች መሆናቸውን እንዲያምኑ፣ ወይም እንዳይገድሉ፣ ወይም እንዳይዘርፉና፣ ወይም እንዳይሰርቁ፣ ወይም ዝሙትንም እንዳይፈፅሙ፣ ወይም ክፉ የሆኑትንም ነገሮች እንዳይፈፅሙ በምድሪቱ ላይ ሁሉ ለህዝቡ አዋጁን ላከ።

  እናም እንዲህ ሆነ ንጉሱ አዋጁን በላከ ጊዜ፣ አሮንና ወንድሞቹ ከከተማ ወደ ከተማ ተጓዙና፣ ከአንዱ ማምለኪያ ቦታ ወደ ሌላኛው በመጓዝ፣ ቤተክርስቲያኖችን በማቋቋም፣ እናም ካህናትንና መምህራን በላማናውያን ምድር በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰብኩና እንዲያስተምሩ ቀደሱአቸው፤ እናም እንደዚህ ታላቅ ስኬትንም ማግኘት ጀመሩ።

  እናም በሺህ የሚቆጠሩ ጌታን ወደማወቅ መጡ፣ አዎን፣ በሺህ የሚቆጠሩት በኔፋውያን ባህል ወደማመንም መጡ፤ እናም እስከአሁኑ ጊዜ የተላለፉትን መዝገቦችና ትንቢቶችም ተማሩ።

  እናም ጌታ ህያው እንደሆነ፣ በርግጥም ብዙዎች እንዳመኑትም፣ ወይም በራዕይና በትንቢት መንፈስ፣ እናም በውስጣቸው ድንቅ ስራን በሚሰራው በእግዚአብሔር ኃይል መሰረት በአሞንና በወንድሙ ሰበብ ብዙዎች እውነቱን ወደ ማወቅ የሚመጡት—አዎን እንዲሁም እላችኋለሁ፣ ጌታ ህያው እንደሆነ፣ በስብከታቸው አምነው የነበሩ ላማናውያን ሁሉ፣ እናም ወደጌታ ተለውጠው የነበሩ፣ መንገዳቸውንም አልሳቱም ነበር።

  እነርሱም ፃድቃን ህዝቦች ሆኑ፣ ከእንግዲህ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም ከወንድሞቻቸው ጋር እንዳይጣሉ የአመፅ መሣሪያቸውን ጣሉ።

  አሁን፣ ወደጌታም የተለወጡት እነዚህ ናቸው፥

  በእስማኤል ምድር የነበሩት የላማናውያን ሕዝቦች፣

  እናም ደግሞ በሚዶኒ ምድር የነበሩት የላማናውያን ሕዝቦች፣

  ፲፩ እናም ደግሞ በኔፊ ከተማ የነበሩት የላማናውያን ሕዝቦች፤

  ፲፪ እናም ደግሞ በሼለም ምድር የነበሩትና፣ በሼምሎን ምድር የነበሩት፣ እናም በልሙኤል ከተማና፣ በሻምሎንም ከተማ የነበሩት የላማናውያን ሕዝቦች።

  ፲፫ እናም እነዚህ ወደጌታ የተለወጡት የላማናውያን ከተሞች ስም ነበሩ፤ እናም የአመፃቸውን መሳሪያዎች፣ አዎን፣ ሁሉንም የጦር መሳሪያዎቻቸውን የጣሉት እነዚህ ናቸው፤ እናም ሁሉም ላማናውያን ነበሩ።

  ፲፬ እናም ከአንዱ በስተቀር አማሌቂውያን አልተለወጡም ነበር፤ ከአሙሎናውያንም ማንም አልተለወጠም፤ ነገር ግን ልባቸውን፣ ደግሞም በዚያ በከፊል በምድሪቱ፣ አዎን እናም መንደሮቻቸውን ሁሉና ከተሞቻቸውን ሁሉ የሚኖሩት ላማናውያን ልብም አጠጥረውት ነበር።

  ፲፭ ሰለሆነም፣ ንስሃ የገቡባቸውንና እውነትን እንዲያውቁ የተደረጉባቸውን እናም የተለወጡባቸውን የላማናውያን ከተሞች ሁሉ ሰይመናቸው።

  ፲፮ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ንጉሱና የተለወጡት ከወንድሞቻቸው ተለይተው ይታወቁ ዘንድ ስም እንዲኖራቸው ፈለጉ፤ ስለዚህ ንጉሱ ከአሮንና ከብዙ ካህናቶቻቸው ጋር እነርሱ እንዲለዩ የሚሰጣቸውን ስም በተመለከተ ተመካከሩ።

  ፲፯ እናም እንዲህ ሆነ ስማቸውንም አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች በማለት ጠሩአቸው፤ እናም በዚህ ስም ተጠሩና፣ ከዚያን ጊዜ በኋላ ላማናውያን ተብለው አልተጠሩም።

  ፲፰ እናም ታታሪ ሰዎች መሆን ጀመሩ፤ አዎን፣ እናም ከኔፋውያን ጋር ወዳጅ ነበሩ፤ ስለዚህ ከእነርሱም ጋር ጓደኝነትን ጀመሩ፣ እናም የእግዚአብሔር እርግማን ከዚያን ጊዜ በኋላ አልተከተላቸውም።