አልማ ፶፯
  Footnotes

  ምዕራፍ ፶፯

  ሔለማን የአንቲፓራን መያዝ፣ እናም የቁሜኒ ከተማን መከበብና፣ መከላከል በተመለከተ በዝርዝር አወራ—ወጣት አሞናውያኑ በጀግንነት ተዋጉ፤ ሁሉም ቆሰሉ፣ ነገር ግን አንድም አልተገደለም—ጊድ የላማናውያን እስረኞችን ሞትና ማምለጥ ሀተታ አቀረበ። በ፷፫ ም.ዓ. ገደማ።

  እናም እንዲህ ሆነ ከንጉስ፣ አሞሮን፣ የጦር ምርኮኞቹን የምንለቅለት ከሆነ የአንቲፓራ ከተማ እንደሚለቅልኝ የሚገልፅ ደብዳቤ ደረሰኝ።

  ነገር ግን ባሉን ወታደሮች የአንቲፓራን ከተማ ለመውሰድ እርግጠኞች እንደሆንን፣ እናም ለከተማዋ ሲባል እስረኞችን በመለዋወጥ እራሳችንን እንደ ሞኝ መገመት እንደሚገባንና፣ እስረኞቻችንን በመለዋወጥ ብቻ ነው እንደምንለቃቸው ለንጉሱ ደብዳቤ ላክኩለት።

  እናም አሞሮን እስረኞችን ስለማይቀያየር ደብዳቤዬን አልተቀበለውም፤ ስለዚህ ወደ አንቲፓራ ከተማ ለመሄድ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን።

  ነገር ግን የአንቲፓራ ከተማ ህዝብ ከተማዋን ትተው ሄዱ፣ እናም ወደ ሌለኛው የያዙአቸው ከተማቸው ለመመሸግ ሸሹ፤ እናም የአንቲፓራ ከተማ በእጃችን ወደቀች።

  እናም የመሣፍንቱ ሀያ ስምንተኛ ዓመት የንግስ ዘመን እንደዚህ ተፈፀመ።

  እናም እንዲህ ሆነ በሀያ ዘጠነኛው ዓመት መጀመሪያ ቀለብ ተቀበልን፣ እናም ደግሞ ከዛራሔምላ ምድር ለወታደሮቻችን ተጨማሪ ኃይልና በዙሪያውም ካሉት ሀገሮች ስድስት ሺህ ሰዎችን፣ ከዚህ በተጨማሪ ስልሳ አሞናውያን ልጆች ከእኔ ትንንሾች ሁለት ሺህ ክምችቶች ወንድሞቻቸው ጋር ለመቀላቀል መጡ። እናም አሁን እነሆ፣ እኛ ጠንካሮች ነበርን፤ አዎን፣ እናም ደግሞ በርካታ ቀለብ መጥተውልን ነበር።

  እናም እንዲህ ሆነ የቁሜኒን ከተማ ለመከላከል ከተቀመጡት ሠራዊት ጋር ውጊያ ማድረግ ፍላጎታችን ነበር።

  እናም አሁን እነሆ፤ በቅርቡ ፍላጎታችንን እንደፈጸምን አሳይሀለሁ፤ አዎን፣ በጠንካራው ኃይላችን፣ ወይም ከጠንካራ ኃይላችን ክፍል ጋር፣ የስንቅ አቅርቦትን ከመቀበላቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በምሽት የቁሜኒን ከተማ ከበብናት።

  እናም እንዲህ ሆነ በከተማዋ ዙሪያ ለበርካታ ምሽት መሸግን፤ ነገር ግን ከነጎራዴያችን ተኝተን ነበር፤ እናም ላማናውያን ብዙ ጊዜ እንደሞከሩት በምሽት መጥተው እንዳይገድሉን ጠባቂዎችን አስቀመጥን፤ ነገር ግን ይህን በሚሞክሩበት ጊዜ ሁሉ ደሞቻቸው ፈስሶ ነበር።

  ከጊዜ በኋላ ስንቆቻቸው ደረሱ፣ እናም ወደከተማዋ በምሽት ለመግባት ተቃርበው ነበር። እናም ላማናውያንን ሳይሆን ያገኙት እኛን ኔፋውያንን ነበር፤ ስለዚህ፣ እነርሱንና ቁሳቁሶቻቸውን ወሰድን።

  ፲፩ እናም በዚህ ሁኔታ ላማናውያን ከሚደገፉበት ቢቆረጡም፣ እነርሱ ከተማዋን ለማስቀረት ቆርጠው ነበር፤ ስለዚህ እነዚህን ስንቆች ወስደን ወደ ይሁዳ፣ እናም እስረኞቻችን በዛራሔምላ መላካችን አስፈላጊ ነበር።

  ፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ብዙ ቀናት ከማለፋቸው በፊት ላማናውያን የእርዳታ ተስፋቸውን ሁሉ ማጣት ጀመሩ፤ ስለዚህ ከተማዋን በእጃችን ሰጡን፤ እናም የቁሜኒን ከተማ ለማግኘት ያቀድነውን አከናወንን።

  ፲፫ ነገር ግን እንዲህ ሆነ እስረኞቻችን ብዙ ስለነበሩ፣ ቁጥራቸው ብዙ ቢሆንም ሠራዊታችንን ሁሉ እስረኞቹን በመጠበቅ እንድንጠቀም ወይንም እነርሱን እንድንገድላቸው ተገድደን ነበር።

  ፲፬ እነሆ በርካታ እስረኞች ያመልጡና በድንጋይና፣ በዱላ፣ እናም በእጃቸው ባሉት ማንኛውም ዓይነት መሳሪያዎች ስለሚዋጉን፣ የጦር ምርኮኞች እንዲሆኑ እራሳቸውን አሳልፈው ከሰጡ በኋላ ከሁለት ሺህ የሚበልጡትን ገድለናል።

  ፲፭ ስለዚህ ህይወታቸውን ማጥፋት ወይንም እስከ ዛራሔምላ ምድር ድረስም በእጃችን ባለው ጎራዴ መጠበቃችን አስፈላጊ ሆነብን፤ እናም ደግሞ ከላማናውያን የወሰድናቸው ቢኖረንም፣ ቀለባችን ለራሳችንም ሰዎች እንኳን የሚሆን በቂ አልነበረም።

  ፲፮ እናም አሁን፣ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ፣ የጦር ምርኮኞቹን በተመለከተ መወሰን እጅግ አስቸጋሪ ጉዳይ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ እነርሱን ወደ ዛራሔምላ ምድር ለመላክ ወሰንን፤ ስለዚህ ሰዎችን መረጥን፣ እናም ለእስረኞቻችን ወደ ዛራሔምላ ምድር እንዲወስዱ ኃላፊነት ሰጠናቸው።

  ፲፯ ነገር ግን እንዲህ ሆነ በማግስቱ ተመለሱ። እናም አሁን እነሆ፣ እስረኞቹን በተመለከተ አልጠየቅናቸውም፤ እነሆም፣ ላማናውያን በእኛ ላይ ነበሩ፣ እናም በጊዜው በእጃቸው ከመውደቅ አድነውን ነበር። እነሆም፣ አሞሮን እነርሱን ለመርዳት አዲስ ቀለብና፣ ደግሞ ብዙ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን ልኮላቸው ነበርና።

  ፲፰ እናም እንዲህ ሆነ ከእስረኞች ጋር የላክናቸው ሰዎች እኛን ለማሸነፍ በተቃረቡ ጊዜ ላማናውያንን ለመያዝ በወቅቱ ደረሱ።

  ፲፱ ነገር ግን እነሆ፣ ሁለት ሺህ ስልሳ የሆኑት ወታደሮቼ በኃይል ተዋጉ፤ አዎን፣ በላማናውያን ፊት የማይበገሩም ነበሩ፤ እናም ተቃዋሚዎቻቸውን በሙሉ ገደሉአቸው።

  እናም ቀሪዎቹ ወታደሮቻችን ከላማናውያን ፊት ለመሸሽ በተቃረቡበት ጊዜ፣ እነሆ፣ ሁለት ሺህ ስልሳዎቹ የማይበገሩ እንዲሁም ተስፋ የማይቆርጡ ነበሩ።

  ፳፩ አዎን፣ እናም የታዘዙትን ቃላት በሙሉ በትክክል አከናወኑ፣ እንዲሁም ጥረት አደረጉ፤ አዎን፣ እንደ እምነታቸውም ለእነርሱ ሆነ፤ እናም ከእናቶቻቸው የተማሩትን ለእኔ የተናገሩትን ቃላት አስታወስኩኝ።

  ፳፪ እናም አሁን እነሆ፣ ይህንን ታላቅ ድል ለማግኘት ያስቻሉ እነዚህ ልጆቼ፣ እናም እስረኞቹን እንዲያጓጉዙ የተመረጡት ሰዎች ነበሩ፤ ላማናውያንን ያሸነፉት እነርሱ ነበሩና፤ ስለዚህ ወደ ማንቲ ከተማ ተነድተው ተመለሱ።

  ፳፫ እናም የቁሜኒ ከተማችንን በመያዝ ቀጥልን፣ እናም ሁላችንም በጎራዴ አልጠፋንም ነበር፤ ይሁን እንጂ ብዙም ጥፋት ደርሶብናል።

  ፳፬ እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን ከሸሹ በኋላ፣ ከሞቱት ሰዎቼ መካከል የቀሩት ቁስለኞች እንዲወሰዱና፣ ቁስላቸው እንዲታሰር ትዕዛዝ በፍጥነት ሰጠሁኝ።

  ፳፭ እናም እንዲህ ሆነ ብዙ ደም ስለፈሰሰባቸው ከእኔ ሁለት ሺዎቹ መካከል ሁለት መቶ የሚሆኑት እራሳቸውን ስተው ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ እናም ለመደነቃችንና፣ ደግሞ ለሠራዊታችን ደስታ መሰረት፣ ከእነርሱ አንድም ነፍስ አልጠፋብንም ነበር፤ አዎን፣ እናም ከእነርሱ መካከልም በብዙ ያልቆሰለ አንድም ነፍስ አልነበረም።

  ፳፮ እናም አሁን፣ መጠበቃቸው ለሠራዊታችን ሁሉ አስገራሚ ነበር፤ አዎን፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ወንድሞቻችን በተገደሉ ጊዜ እነርሱ ተርፈው ነበር። እናም ይህ የሆነው ፃድቅ እግዚአብሔርም እንዳለና፣ ማንም ካልተጠራጠረ በእግዚአብሔር አስደናቂው ኃይል እንደሚጠበቅ እንዲያምኑ በተማሩት ባላቸው ታላቅ እምነት የተነሳ በኃያሉ እግዚአብሔር ድንቅ ስራ እንደሆነ በትክክል እናመለክታለን።

  ፳፯ እንግዲህ እነዚህ የተናገርኩባቸው እምነት ይህ ነበር፤ እነርሱ ወጣቶች ናቸው፣ እናም አስተሳሰባቸው ፅኑ ነው፣ እናም እምነታቸውን ሳያቋርጡ በእግዚአብሔር አድርገዋል።

  ፳፰ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ የቆሰሉትን ሰዎች ከተንከባከብንና፣ የሞቱብንን፣ እናም ደግሞ ብዙ የነበሩትን የሞቱትን ላማናውያን ከቀበርን በኋላ፣ እነሆ፣ ወደ ዛራሔምላ ምድር ይዘዋቸው ጉዞ ስለጀመሩት እስረኞች በተመለከተ ጊድን ጠየቅነው።

  ፳፱ እንግዲህ ጊድ ምድሪቱ እየጠበቁ እንዲወስዷቸው በተመደቡት ቡድኖች ላይ የተሾመው ሊቀ ሸምበላቸው ነበር።

  እናም አሁን፣ ጊድ የተናገረኝ ቃላት እነዚህ ናቸው፤ እነሆ፣ ከእስረኞቻችን ጋር ወደ ዛራሔምላ ምድር ጉዞ ጀምረን ነበር። እናም እንዲህ ሆነ የላማናውያንን የጦር ሰፈር እንዲጠብቁ የተላኩትን የሠራዊታችንን ሰላዮች አገኘናቸው።

  ፴፩ እናም እንዲህ ሲሉ ወደ እኛ ጮኹ—እነሆ፣ የላማናውያን ሠራዊት ወደ ቁሜኒ ከተማ በመሄድ ላይ ናቸው፣ እናም እነሆ፣ ላማናውያን ያጠቋቸዋል፤ አዎን፣ እናም ህዝባችንን ያጠፋሉ።

  ፴፪ እናም እንዲህ ሆነ እስረኞቻችን እንዲበረቱ ያደረጋቸውን ጩኸታቸውን ሰሙ፤ እናም በአመፅ በእኛ ላይ ተነሱ።

  ፴፫ እናም እንዲህ ሆነ በማመፃቸው ጎራዴዎቻችንን በእነርሱ ላይ አሳረፍንባቸው። እናም እንዲህ ሆነ በአንድነትም ወደ ጎራዴው ሮጡ፣ በእርሱም ብዙ ቁጥር ያላቸው ተገደሉ፤ እናም ቀሪዎቹ አመለጡና፣ ከእኛ ሸሹ።

  ፴፬ እናም እነሆ፣ በሸሹ ጊዜ፣ እኛም ልንደርስባቸውም ስላልቻልን፣ ጉዞአችንን በፍጥነት ወደ ቁሜኒ ከተማ አደረግን፤ እናም እነሆ፣ ወንድሞቻችን ከተማዋን እንዲጠብቁ እንረዳቸው ዘንድ በጊዜ ደረስን።

  ፴፭ እናም እነሆ ከጠላቶቻችን እጅ በድጋሚ አመለጥን። እናም የአምላካችን ስም የተባረከ ይሁን፤ እነሆም እርሱ ነው እንድንተርፍ ያደረገን፤ አዎን፣ ይህንን ታላቅ ነገር ለእኛ አድርጎልናል።

  ፴፮ እንግዲህ እንዲህ ሆነ የጊድን ቃል፣ እኔ ሔለማን፣ በሰማሁኝ ጊዜ፣ እኛን እንዳንጠፋ በመጠበቅ በነበረው በጌታ ቸርነት በታላቅ ደስታ ተሞልቼ ነበር፤ አዎን፣ እናም የሞቱት ነፍስም በአምላካቸው ዘንድ እንደሚያርፍ አምናለሁ።