አልማ ፳፱
  Footnotes

  ምዕራፍ ፳፱

  አልማ በመለኮታዊ ቅንዓት ንስሃን ለመጮህ ፈለገ—ጌታ ለሁሉም ሀገር አስተማሪዎችን ሰጠ—አልማ በጌታ ስራ፣ እናም በአሞንና በወንድሞቹ ስኬታማነት ተደሰተ። በ፸፮ ም.ዓ. ገደማ።

  አቤቱ፣ እንድሄድ እናም ምድሪቱን በሚያንቀጠቅጠው ድምፅ፣ በእግዚአብሔር መለከት እናገር ዘንድና ለማንኛውም ሰው ንስሃን እናገር ዘንድ፣ መልዓክ በሆንኩና የልቤም መሻት በሞላልኝ!

  አዎን፣ ንስሃ እንዲገቡና ወደአምላካችን እንዲመጡ፣ በምድሪቱ ገፅ ላይም ከዚህ የበለጠ ሀዘን እንዳይኖር፣ እንደነጎድጓድም ድምፅ ለማንኛውም ነፍስ ንስሃን እናም የቤዛነትን ዕቅድ አውጅ ነበር።

  ነገር ግን እነሆ፣ እኔ ሰው ነኝ፤ እናም በፍላጎቴ ኃጢያትን እሰራለሁ፤ ምክንያቱም ጌታ በሰጠኝ ነገሮች መረካት ይገባኛልና።

  ጠንካራ የሆነውን ፍትሀዊውን የአምላክ አዋጅ በፍላጎቴ መለወጥ አይገባኝም፣ ምክንያቱም ለህይወታቸውም ይሁን ለሞታቸው እንደፍላጎታቸው እርሱ እንዲሰጣቸው አውቃለሁ፤ አዎን ለሰዎች እንደ ፈቃዳቸው ለደህንነትም ይሁን ለጥፋት መደብ፣ አዎን መለወጥ የማይችል አዋጅ በማወጅ እንደሚሰጣቸው አውቃለሁ።

  አዎን፣ እናም መልካምና መጥፎ የሆነው በሰዎች ሁሉ ፊት እንደመጣ አውቃለሁ፤ መልካሙን ከመጥፎው የማያውቅ እንከን የለሽ ነው፤ ነገር ግን መልካምና መጥፎውን ለሚያውቅ ለእርሱ እንደፍላጎቱ፣ ፍላጎቱ መልካምም ይሁን መጥፎ፣ ህይወትም ይሁን ሞት፣ ደስታም ይሁን የህሊና ፀፀት ይሰጠዋል።

  እንግዲህ፣ እነዚህን ነገሮች ማወቄን በመመልከት፤ ከተጠራሁበት የበለጠ ስራስ ለማከናወን ለምን እፈልጋለሁ?

  ለምንስ መልአክ ሆኜ እስከምድር ዳርቻ መናገር እስከምችል እመኛለሁ?

  እነሆም ጌታ ለሀገሮች ሁሉ ቃሉን በጥበብ፣ አዎን፣ ሊኖራቸው የሚገባውን ነገር ሁሉ እንዲያስተምሩ የራሳቸውን ሀገር እና ቋንቋ ሰጥቷል፤ ስለዚህ ጻድቅና እውነት በሆነው መሰረት ጌታ በጥበቡ እንደሚመሰክር እንመለከታለን።

  ጌታ ያዘዘኝን አውቃለሁ፣ እናም በዚህም እደሰታለሁ። በራሴ አልኮራም፣ ነገር ግን ጌታ እኔን ባዘዘኝ በዚያ እኮራለሁ፤ አዎን፣ ይህም ምናልባት ጥቂት ነፍሳትን ወደ ንስሃው በማምጣት በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ እሆን ዘንድ በዚህ እመካለሁ፤ እናም ይህም የእኔ ደስታ ነው።

  እናም እነሆ፣ ብዙዎቹ ወንድሞቼ በእውነት ንስሃ መግባታቸውን፣ እና ወደጌታ አምላካቸው መምጣታቸውን በተመለከትኩ ጊዜ፣ ከዚያም ነው ነፍሴ በደስታ የተሞላችው፤ በዚያም ጌታ ምን እንዳደረገልኝ፣ አዎን፣ ፀሎቴንም እንኳን እንደሰማልኝ ለማስታወስ እችላለሁ፤ አዎን በዚያም የምህረት ክንዶቹ በእኔ ላይ መዘርጋታቸውንም አስታውሳለሁ።

  ፲፩ አዎን፣ እናም ደግሞ የአባቶቻችንን ምርኮ አስታውሳለሁ፤ ጌታ ከባርነት እንደለቀቃቸው በእርግጥ አውቃለሁ፣ እናም በዚህም ቤተክርስቲያኗን አቋቁሟል፤ አዎን፣ ጌታ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሀቅ አምላክ፣ እንዲሁም የያዕቆብ አምላክ ከባርነት ለቋቸዋል።

  ፲፪ አዎን፣ የአባቶቻችንን ምርኮ ሁልጊዜም አስታውሳለሁ፤ እናም ከግብፃውያን እጅ ያስለቀቃቸው አምላክ ከባርነት እነርሱንም አስለቅቋል።

  ፲፫ አዎን፣ እናም ይኸው አምላክ ቤተክርስቲያኗን በመካከላቸው አቋቁሟል፤ አዎን፣ ይኸውም አምላክ ቃሉን ለህዝቡ እንድሰብክ በቅዱሱ ጥሪው ጠራኝ፤ እናም ብዙ ድልም ሰጠኝ፤ በዚህም ደስታዬ የተሞላ ነው።

  ፲፬ ነገር ግን በራሴ ስኬታማነት ብቻ አልደሰትም፣ ነገር ግን በኔፊ ምድር በነበሩት ወንድሞቼ ስኬታማነት ደስታዬ ይበልጥ ሙሉ ነው።

  ፲፭ እነሆ፣ እነርሱ እጅግ ሰሩም፣ በርካታ ፍሬን አምጥተዋልም፤ እናም ደመወዛቸው እንዴት ታላቅ ይሆናል!

  ፲፮ አሁን፣ የእነዚህን የወንድሞቼን ስኬት ባሰብኩ ጊዜ ነፍሴ ከስጋዬ እንደተለየች ያህል ትወሰዳለች፣ በመሆኑም ደስታዬም ታላቅ ነው።

  ፲፯ እናም አሁን እግዚአብሔር ለወንድሞቼ በእግዚአብሔር መንግስት እንዲቀመጡ ለእነርሱ ይፈቀድላቸው፤ አዎን፣ እናም ደግሞ የስራቸው ውጤት የሆኑት ሁሉ ከእንግዲህ እንዳይሄዱባቸው፤ ነገር ግን ለዘለዓለም እርሱን ያወድሱት። እናም እኔ እንደተናገርኩት እንደቃሌም እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን። አሜን።