ምዕራፍ ፴፪
መላዕክት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይናገራሉ—ሰዎች መፀለይ እናም እውቀትን ከመንፈስ ቅዱስ ማግኘት አለባቸው። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን፣ እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እናንተ በጎዳናው ከገባችሁ በኋላ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ በመጠኑ በልባችሁ እንደምታሰላስሉ እገምታለሁ። ነገር ግን፣ እነሆ፣ ስለምን እነዚህን ነገሮች በልባችሁ ታሰላስላላችሁ?
፪ መንፈስ ቅዱስን ሀከተቀበላችሁ በኋላ በመላዕክት ለልሳን መናገር እንደምትችሉ የተናገርኳችሁን አታስታውሱም? እናም አሁን፣ በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በመላዕክት ልሳን መናገር እንዴት ትችላላችሁ?
፫ ሀመላዕክት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይናገራሉ፤ ስለዚህ፣ የክርስቶስን ቃል ይናገራሉ። ስለሆነም፣ የክርስቶስን ቃል ለተመገቡ እላችኋለሁ፤ እነሆ የክርስቶስ ቃል ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ ይነግራችኋልና።
፬ ስለሆነም፣ አሁን እነዚህን ቃላት ከተናገርኩ በኋላ፣ መረዳት ካልቻላችሁ፣ ይህም ሀስላልጠየቃችሁ፣ ወይም ስላላንኳኳችሁ ነው፤ ስለሆነም፣ ወደ ብርሃኑ አልመጣችሁም፣ ነገር ግን በጨለማው ትጠፋላችሁ።
፭ እነሆም፣ በድጋሚ እላችኋለሁ በመንገዱ የምትገቡ፣ እናም መንፈስ ቅዱስን የምትቀበሉ ከሆነ፣ ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች ሁሉ ያሳያችኋል።
፮ እነሆ፣ ይህ የክርስቶስ ትምህርት ነው፣ እናም ለእናንተ በስጋ እራሱን ሀእስከሚገልፅ ድረስ ሌላ ትምህርት አይሰጥም። እናም እርሱ ራሱን በስጋ ለእናንተ በሚገልፅበት ጊዜ፣ የተናገራችሁን ነገሮች በትጋት ታደርጋላችሁ።
፯ እናም አሁን እኔ ኔፊ፣ ብዙ ማለት አልችልም፤ መንፈስ እንዳልናገር አደረገኝ፣ እናም በሰዎች ሀባለማመን፣ ክፋትና፣ ባለማወቅ፣ እንዲሁም አንገተ ደንዳናነት የተነሳ አዝናለሁ፤ ምክንያቱም እውቀትን አልፈለጉም፣ ወይም ታላቁን እውቀት ለበግልፅ፣ እንዲሁም ቃል መግለጽ እስከሚቻልበት ያህል፣ በተሰጣቸውም ጊዜ አልተረዱምና።
፰ እናም አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ አሁንም በልባችሁ እንደምታሰላስሉ አስተውላለሁ፤ እናም ይህን ነገር በሚመለከት መናገር ስላለብኝ ያሳዝነኛል። ሰዎችን ሀእንዲፀልዩ የሚያስተምረውን መንፈስ ካዳመጣችሁት መፀለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፤ ለእርኩስ መንፈስ ሰዎችን ፀሎት አያስተምርምና፣ ነገር ግን መፀለይ እንደሌለባቸው ያስተምራቸዋል።
፱ ነገር ግን እነሆ፣ ሳትታክቱ ዘወትር ሀመጸለይ እንዳለባችሁ፤ በመጀመሪያ ወደ አብ በክርስቶስ ለስም ካልፀለያችሁ ምንም ነገር ለጌታ ማከናወን እንደማይገባችሁ፣ እርሱም ስራችሁን ቅዱስ እንደሚያደርግላችሁ፣ ስራችሁም ለነፍሳችሁ ሐደህንነት እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።