ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፳፪


ምዕራፍ ፳፪

በአንድ ሺህ ዘመን ሰዎች ሁሉ ጌታን ያወድሳሉ—እርሱም በመካከላቸው ይኖራል—ኢሳይያስ ፲፪ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

፩ እናም በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ—አቤቱ ጌታ፣ አመሰግንሀለሁ፤ በእኔ ብትቆጣም እንኳ ቁጣህን አብርደህልኛል፣ አፅናንተህኛልም።

፪ እነሆ፣ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ አምናለሁ፣ እና አልፈራም፤ ጌታ ያህዌህ ጥንካሬዬና ዝማሬዬ ነውና፤ ደግሞም እርሱ መድኃኒቴ ሆኖአልና።

፫ ስለዚህ፣ ውኃንም ከመዳን ጉድጓዶች በደስታ ትቀዳለህ።

፬ እናም በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ—ጌታን አወድሱ፣ ስሙንም ጥሩ፣ በአህዛብም መካከል ስራውን አውጁ፣ ስሙም ከፍ ያለ እንደሆነ አስታውቁ።

፭ ለጌታ ዘምሩ፤ እርሱ ታላቅ ስራን ሰርቶአልና፤ ይህም በምድር ሁሉ ታውቋል።

፮ በፅዮን የምትኖሩ ሁሉ ጩሁ፣ እልልም በሉ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤሉ ቅዱስ ታላቅ ነውና።