በአሞኒሀ ምድር ለነበሩት ሰዎች በአልማ፣ ደግሞም በአሙሌቅ የታወጁት ቃላት። እናም በአልማ ዘገባ መሰረት፣ እነርሱ በወህኒ ቤት ተጣሉ፣ እናም በውስጣቸው ባለው ታምራታዊ የእግዚአብሔር ኃይልም ተለቀቁ።
ከምዕራፍ ፱ እስከ ፲፬ አጠቃሎ የያዘ።
ምዕራፍ ፱
አልማ የአሞኒሀ ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ አዘዘ—ጌታ በመጨረሻው ቀን ለላማናውያን መሀሪ ይሆናል—ኔፋውያን ብርሃኑን ከተዉ፣ በላማናውያን ይጠፋሉ—የእግዚአብሔር ልጅ በቅርቡ ይመጣል—ንስሃ የገቡትን፣ የተጠመቁትንና፣ በስሙም ካመኑት ያድናቸዋል። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም በድጋሚ፣ እኔ አልማ አሙሌቅን ለመውሰድና ለህዝቡም፣ ወይም በአሞኒሀ ከተማ ላሉት ሰዎች፣ በድጋሚ ለመስበክ በእግዚአብሔር በመታዘዜ፣ እንዲህ ሆነ ለእነርሱ መስበኬን ስጀምር እንዲህ በማለት ከእኔ ጋር መጣላት ጀመሩ፥
፪ አንተ ማነህ? ምድር ታልፋለች በማለት ለእኛ ቢሰብክም ሀየአንድን ሰው ምስክርነት እናምናለን ብለህ ትገምታለህን?
፫ እንግዲህ የተናገሩትን ቃላት አልተረዱም፤ ምድር እንደምታልፍም አያውቁምና።
፬ እናም ደግሞ እንዲህ አሉ፥ ይህች ታላቂቱ ከተማ ሀበአንድ ቀን ትጠፋለች በማለት ብትተነብይም ቃልህን አናምንም።
፭ አሁን እነርሱ ልበ ጠጣርና አንገተ ደንዳና ሰዎች ስለነበሩ እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነት ድንቅ ስራን መስራት ይችላል ብለው አላወቁም።
፮ እናም እንዲህ አሉ፥ እንደዚህ ዓይነቱን ታላቅና ድንቅ እውነታ እንዲናገር በህዝቡ መካከል ከአንድ ሰው በላይ ሀምንም ስልጣን ሰጥቶ የማይልክ፣ እግዚአብሔር ለማን ነው?
፯ እናም እጃቸውን በእኔ ላይ ለመጫን ተነሱ፤ ነገር ግን እነሆ፣ አልነኩኝም። እናም ለእነርሱ ለማወጅ በድፍረት ቆምኩ፣ አዎን፣ በድፍረት እንዲህ በማለት መሰከርኩ፥
፰ እነሆ፣ እናንተ ክፉና ጠማማ ሀትውልድ፣ የአባቶቻችሁን ባህል እንዴት ረሳችሁ፤ አዎን የእግዚአብሔርንስ ትዕዛዛት እንዴት በፍጥነት ረሳችሁ።
፱ አባታችን ሌሂስ በእግዚአብሔር ሀእጅ ከኢየሩሳሌም እንደወጣ አታስታውሱምን? ከምድረበዳውስ ሁሉም በእርሱ እንደተመሩ አታስታውሱምን?
፲ እናም አባቶቻችንን ከጠላቶቻቸው እጅ ምን ያህል ጊዜ እንዳስለቀቀና፣ በወንድሞቻቸውም እጅ እንኳን ቢሆን፣ ከመጥፋት እንደጠበቃቸው በፍጥነት ረሳችሁትን?
፲፩ አዎን፣ ለእኛ ባለው ወደር በሌለው ስልጣኑና ምህረቱ፣ እንዲሁም በረዥም ፅናቱ ባይሆን ኖሮ ከዚህ ጊዜ በፊት ከምድረ ገፅ ሊወገድ በማይቻልበት መጥፋት ይገባን ነበር፣ እናም ምናልባት ሀመጨረሻ ለሌለው ጉስቁልና ወዮታ እንሰጥ ነበር።
፲፪ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ አሁን እርሱ ንስሃ እንድትገቡ ያዛችኋል፤ እናም እናንተ ንስሃ ካልገባችሁ በምንም መንገድ የእግዚአብሔርን መንግስት ልትወርሱ አትችሉም። ነገር ግን እነሆ፣ ይህ ብቻ አይደለም—እርሱ ንስሃ እንድትገቡ አዟችኋል፣ አለበለዚያም እናንተን ከምድረ ገፅ ፈፅሞ ሀያጠፋችኋል፤ አዎን፣ በቁጣውም ይጎበኛችኋል፣ እናም ለጽኑ ቁጣው ከእናንተ አይመልስም።
፲፫ እነሆ፣ ትዕዛዛቴን እስከጠበቃችሁ ሀድረስ፣ በምድሪቱ ላይ ትበለፅጋላችሁ ብሎ ለሌሂ የተናገራቸውን ቃላት አታስታውሱምን? እናም በድጋሚም እንዲህ ተብሏል፤ ትዕዛዛቴን እስካልጠበቃችሁ ድረስ ከጌታ ፊት ትለያላችሁ።
፲፬ እንግዲህ ላማናውያን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስካልጠበቁ ድረስ፣ ከጌታ ፊት ሀእንደተለዩ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ። አሁን በዚህ ነገር የጌታ ቃል ማረጋገጫ እንደሆነ እናያለን፣ እናም ላማናውያን በምድሪቱ መተላለፍ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከእርሱ ፊት ተለይተዋል።
፲፭ ይሁን እንጂ እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በኃጢአታችሁ ከቀጠላችሁ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለእነርሱ ሀይቀልላቸዋል፤ አዎን እናም ንስሃ ካልገባችሁ በዚህ ህይወትም ቢሆን እንኳን ለእነርሱ የበለጠ ቀላል ይሆናል።
፲፮ ለላማናውያን ብዙ የተስፋ ቃል ሀተሰጥቶአቸዋልና፤ በአባቶቻቸው ለወግ ምክንያት ነው ሐበድንቁርና እንዲቀሩ ስላደረጋቸውና፤ ስለዚህ ጌታ ለእነርሱ መሀሪ ይሆናል፣ እናም በምድሪቱ ላይ ህይወታቸውን መያረዝማል።
፲፯ እናም በአንድ ወቅት በቃሉ ወደማመንና፣ የተሳሳተውን የአባቶቻቸውንም ወግ ወደ መረዳት ሀይደርሳሉ፤ እናም ብዙዎች ይድናሉ፣ ጌታ ለስሙን ለሚጠሩ ሁሉ መሀሪ ይሆናልና።
፲፰ ነገር ግን እነሆ፣ በኃጢአታችሁ የምትቀጥሉ ከሆነ ሀላማናውያን በእናንተ ላይ የሚላኩ በመሆናቸው በምድሪቱ ላይ የመቆያችሁ ቀን አይረዝምም፤ ንስሃ የማትገቡም ከሆነ እናንተ በማታውቁበት ወቅት ይመጣሉ፣ እናም ለፍፁም በሆነ ጥፋትም ትጎበኛላችሁ፤ ይህም በፅኑ የጌታ ሐቁጣ መሰረት ነው።
፲፱ ህዝቡን ለማጥፋት እናንተ በክፋት እንድትኖሩ አይፈቅድላችሁም። እኔ ግን አይሆንም እላችኋለሁ፤ ለጌታ አምላካቸው ታላቅ ብርሃንን ታላቅ እውቀትን ካገኙ በኋላ በኃጢያትና በመተላለፍ ሀለመውደቅ የሚቻላቸው ከሆነ የኔፊ ህዝብ የተባሉትን ሁሉ ላማናውያን ለእንዲያጠፏቸው ቢፈቅድ ይሻለዋል።
፳ አዎን፣ በጌታ የተወደዱ ሰዎች ከሆኑ በኋላ፣ አዎን፣ ከሁሉም ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ህዝብ በላይ የተወደዱ ከሆኑ በኋላ፣ ሁሉንም ነገሮች በፍላጎታቸው፣ በእምነታቸው፣ በፀሎታቸው መሰረት፣ ስለነበረው፣ እና ስለሆነው፣ እናም ስለሚመጣው ሀእንዲያውቁ ከተደረጉ በኋላ፤
፳፩ በእግዚአብሔር መንፈስ ከተጎበኙ በኋላ፣ ከመልአኩ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፣ የጌታ ድምፅም ከተናገራቸው በኋላና፣ የትንቢት መንፈስና የራዕይ መንፈስ፣ ደግሞም ብዙ ስጦታዎች በልሳን የመናገር ስጦታ፣ እናም የመስበክ ስጦታና፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታና ሀየመተርጎም ስጦታ ከተሰጣቸው በኋላ፤
፳፪ አዎን፣ ከኢየሩሳሌም ምድር በጌታ እጅ ሀበእግዚአብሔር እንዲለቀቁ ከተደረጉ በኋላ፣ ከረሃብ፣ ከበሽታና ከሁሉም ዓይነት ተውሳክ ከዳኑ በኋላ፤ ከዚያም በኋላ እንዳይጠፉ ለጦርነት በመበርታት ጠነከሩ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለከባርነት በመውጣትና፣ እስካሁን እንዲቀመጡና እንዲጠበቁ ሆነዋል፤ እናም በሁሉም ነገሮች ሀብታም እስኪሆኑ ድረስ በልፅገዋል—
፳፫ እናም አሁን እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ይህ ህዝብ ብዙ በረከቶችን ከጌታ አግኝቶ ካለው ብርሃንና እውቀት በተቃራኒ የሚተላለፍ ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ ከሆነ፣ እነርሱም ወደ መተላለፍ የሚወድቁ ከሆነ፣ ከእነርሱ የበለጠ ሀለላማናውያን የሚቀልላቸው ይሆናል እላችኋለሁ።
፳፬ እነሆም፣ የጌታ ሀቃል ኪዳን ለላማናውያን ተዘርግቷል፤ ነገር ግን እናንተ የምትተላለፉ ከሆነ ለእናንተ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ጌታ እናንተ በእርሱ ላይ የምታምፁ ከሆነ ከምድረ ገፅ ፈፅሞ ትጠፋላችሁ በማለት በግልፅ ቃል አልገባምን እንዲሁም በጥብቅ አላወጀምን?
፳፭ እናም አሁን በዚህ የተነሳ፣ እንዳትጠፉ ዘንድ፣ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ሀንስሃ ግቡ በማለት ወደዚህ ህዝብ መሄድ እና መጮህ እንዳለባቸው ለማወጅ ጌታ መልአኩን ብዙ ህዝቦቹን እንዲጎበኝ ልኳል።
፳፮ እናም የእግዚአብሔር ልጅ በክብር በሚመጣበት ቀን ከዚህ በኋላ ሀሩቅ አይደለም፤ እናም ክብሩ የአብ ለአንድያ ልጅ ክብር የሆነ፣ ሐበፀጋ፣ በፍትህና በእውነት፣ በፅናት መመሃሪና በታጋሽነት የተሞላ፣ የህዝቡን ጩኸት ሠለመስማትና መልስ ለመስጠት ፈጣን የሆነው ይሆናል።
፳፯ እናም እነሆ፣ በስሙ በማመን ለንስሃ ሀየሚጠመቁትን ለለማዳን ይመጣል።
፳፰ ስለዚህ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ በነበሩበት መሰረት ሰዎች በሙሉ ሀየስራቸውን ውጤት የሚሰበስቡበት ጊዜ ቀርቧልና—ፃድቃን ከሆኑ በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልና መድሀኒት መሰረት የነፍሳቸውን ደህንነት ለያጭዳሉ፤ እናም ክፉ ከሆኑ በዲያብሎስ ስልጣንና ግዞት መሰረት ለነፍሳቸው ሐእርግማንን ያጭዳሉ።
፳፱ አሁን እነሆ፣ ይህ ወደ ህዝቡ የሚጮኸው የመልአክ ድምፅ ነው።
፴ እናም አሁን፣ ሀየተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እናንተ ወንድሞቼ ናችሁና፣ እናም የተወደዳችሁ መሆን ይገባችኋል፣ ለንስሃ የሚሆን ስራን መስራትም አለባችሁ፣ ምክንያቱም ልባችሁ በጌታ ቃል ላይ እጅግ ጠጥሯልና እናም ለየተሳሳታችሁና የወደቃችሁ ህዝቦች ናችሁ።
፴፩ አሁን እንዲህ ሆነ እኔ አልማ እነዚህን ቃላት ስናገር፣ እነሆ፣ ህዝቡ በእኔ ተቆጥቷል ምክንያቱም እነርሱ ልበ ጠጣር እና ሀአንገተ ደንዳና ሰዎች እንደሆኑ ነግሬአቸዋለሁና።
፴፪ እናም ደግሞ የጠፉና የወደቁ ሰዎች መሆናቸውን በመናገሬ፣ በእኔ ተቆጡ፣ እናም ወደ ወህኒ ቤት ይጥሉኝ ዘንድ እጃቸውን ሊጭኑብኝ ፈለጉ።
፴፫ ነገር ግን እንዲህ ሆነ ጌታ በዚያን ጊዜ እኔን ወስደው ወህኒ ቤት እንዲጥሉኝ አልፈቀደላቸውም ነበር።
፴፬ እናም እንዲህ ሆነ አሙሌቅ ሄደና ወደፊት ቆሞ፣ ደግሞም መስበክ ጀመረ። እናም አሁን ሀየአሙሌቅ ቃላት በሙሉ አልተፃፉም፣ ይሁን እንጂ ከቃሉ የተወሰነው ክፍል በዚህ መፅሐፍ ተፅፏል።