ምዕራፍ ፮
በዛራሄምላ ያለው ቤተክርስቲያን ከኃጢያት ጠርቷል እናም ተደራጅቷል—አልማ ለመስበክ ወደ ጌዴዎን ሄደ። ፹፫ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ በዛራሔምላ ከተማ ለተቋቋመው ቤተክርስቲያን ሰዎች ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ስርዓት መሰረት ቤተክርስቲያኗን እንዲመሩና ሀእንዲቆጣጠሩ ለእጁን በመጫን ካህናትን እና ሐሽማግሌዎችን መሾመ።
፪ እናም እንዲህ ሆነ ከቤተክርስቲያኗ ያልሆኑ ለኃጢአታቸው ንስሐ የገቡት ወደ ንስሐ ሀተጠምቀው እናም በቤተክርስቲያኗ ተቀባይነትን አግኝተው ነበር።
፫ እናም ደግሞ እንዲህ ሆነ ከቤተክርስቲያኗ የሆኑ ለኃጢአታቸው ሀንስሐ ያልገቡ እናም በእግዚአብሔር ፊት እራሳቸውን ዝቅ የማያደርጉ ሁሉ—ማለትም በልባቸው ለኩራት የተወጠሩ—እንደነዚህ ዓይነቶቹ ተቀባይነትን አላገኙም ነበር፣ እናም ስማቸው ሐተሰርዘዋል፣ ስማቸው ከፃድቃኖች ጋር አልተቆጠረም ነበር።
፬ እና እንደዚህም በዛራሔምላ ከተማ የቤተክርስቲያኗን ስርዓት መመስረት ጀመሩ።
፭ አሁን የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም በነፃ እንደተሰጠ እንድትረዱ እፈልጋለሁ፣ ማንም እራሱን በአንድ ላይ በመሰብሰብ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ልዩ መብቱን የሚከለክለው የለም።
፮ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች እራሳቸውን በአንድ ላይ ሁልጊዜ እንዲሰበስቡ፣ እናም በአንድ ላይ በመሆን እግዚአብሔርን ለማያውቁት ነፍሳት ደህንነት ሀእንዲፆሙና እንዲፀልዩ ታዘዋል።
፯ እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ እነዚህን ህጎች ባዘጋጀ ጊዜ ከእነርሱ፣ አዎን፣ በዛራሔምላ ከተማ ከሚገኘው ቤተክርስቲያን፣ ተለይቶ ሄደ፣ እናም ሀበጌዴዎን ሸለቆ፣ ከሲዶም ወንዝ በስተምስራቅ በኩል ጌዴዎን ተብላ ወደ ምትጠራውና በዚያም ወደታነፀች ከተማ፣ ጌዴዎን ተብሎ ወደ ሚጠራው ሸለቆ ሄደ፣ ስፍራውም ኔሆር በተባለው ሰው እጅ ለበተገደለው ስም የሚጠራ ነበር።
፰ እናም አልማ ሄደና፣ በአባቶቹ በተነገረው በቃሉ እውነታ ራዕይ መሰረትና፣ በውስጡ ባለው የትንቢት መንፈስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው፣ ህዝቡን ከኃጢያት ለማዳን በሚመጣውና ሀበኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት መሰረትና፣ በተጠራበትም ቅዱሱ ስርዓት፣ በጌዴዎን ሸለቆ ለተቋቋመችው ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ ጀመረ። እናም እንዲሁ ተፅፏል። አሜን።