ምዕራፍ ፯
[ታህሳስ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]
ሔኖክ ሕዝብን አስተማረ፣ መራ፣ እና ተራሮችንም አንቀሳቀሰ—የጽዮን ከተማም ተቋቋመ—ሔኖክ የሰው ልጅ መምጣትን፣ የኃጢአት ክፍያ መስዋዕቱን፣ እና የቅዱሳንን ትንሳኤን አስቀድሞ አየ—ዳግሞ መመለስን፣ መሰብሰብን፣ የክርስቶስን ዳግም ምፅዓት፣ እና የፅዮንን መመለስ አስቀድሞ አየ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ ሔኖክ ንግግሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥ እነሆ፣ አባታችን አዳም እነዚህን ነገሮች አስተማረ፣ እና ብዙዎችም አመኑና የእግዚአብሔር ሀልጆች ሆኑ፣ እና ብዙዎችም አላመኑምና በኃጢአታቸውም ሞቱ፣ እና ለበፍርሀት፣ በስቃይ፣ የእግዚአብሐርን እሳት አይነት ቁጣ እስከሚፈስባቸው ድረስ ይጠብቃሉ።
፪ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ ሔኖክ መተንበይ ጀመረ፣ ለህዝቡም እንዲህ አለ፥ እየተጓዝኩ በማሁጃ ላይ ስቆም፣ እና ወደ እግዚአብሔር ስጮኽ፣ ከሰማይ ድምጽ መጣ እንዲህም አለኝ—ተመለስ፣ እና ወደ ስምዖን ተራራ ውጣ።
፫ እናም እንዲህ ሆነ ተመለስኩ፣ እና በተራራውም ላይ ወጣሁ፤ እና በተራራው ላይ ቆሜ ሳለሁ፣ ሰማያት ሲከፈቱ አየሁ፣ እና ሀክብርንም ለብሼም ነበር፤
፬ እና ጌታንም አየሁ፤ ሀበፊት ለፊቴም ቆሞ፣ እና ሰው ከሌላው ሰው ጋር እንደሚነጋገርም ፊት ለፊት አነጋገረኝ፤ እናም እንዲህም አለኝ፥ ለተመልከት፣ እና ለብዙ ትውልዶች ለሚሆን ጊዜ አለምን አሳይሀለሁ።
፭ እናም እንዲህ ሆነ፣ እናም አስተውሉ፣ በሹም ሸለቆ ውስጥ በድንኳኖች ውስጥ የሚኖሩትንም የሹምን ህዝብ አየሁ።
፮ ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፥ ተመልከት፤ እና ወደ ሰሜን ተመለከትኩኝ፣ እና በድንኳኖች ውስጥ የሚኖሩትን የከነዓንን ህዝብ አየሁ።
፯ ጌታም ተንብይ አለኝ፤ እና እኔም እንዲህ ብዬ ተነበይኩ፥ እነሆ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የከነዓን ሰዎች ለጦርነት ተዘጋጅተው ወደ ሹም ህዝብ ይሄዳሉ፣ እናም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ይገድሏቸዋል፤ እና የከነዓን ህዝብም በመሬቱ ራሳቸውን ይከፋፍላሉ፣ እናም መሬቱም ዳተኛና ፍሬ ቢስ ይሆናል፣ እና ከከነዓን ህዝብ ሌላ ማንም በዚያ መኖር አይችልም።
፰ እነሆም፣ ጌታ መሬቱን በብዙ ሙቀት ይረግመዋል፣ በዳተኛነትም ለዘለአለም በእዚያ ይሆናል፤ እና በሁሉም ህዝብ ይጠሉ ዘንድ፣ በከነዓን ልጆች ላይ ሁሉ ሀጥቁርነት መጣባቸው።
፱ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ ተመልከት፤ እና ተመለከትኩኝ፣ እና የሼረንን ምድር፣ እና የሔኖክን ምድር፣ እናም የኦምነርን ምድር፣ እናም የሄኒን ምድር፣ እናም የሴምን ምድር፣ እናም የሃነርን ምድር፣ እናም የሃናአኒሀህን ምድር፣ እናም እዚያ የሚኖሩትን ሁሉ አየኋቸው።
፲ እናም ጌታ እንዲህ አለኝ፥ ወደነዚህ ህዝቦች ሂድ፣ እና እንዲህም በላቸው—ሀንስሀ ግቡ፣ አለበለዚያም መጥቼ በርግማን አጠፋቸዋለሁ፣ እና ይሞታሉ።
፲፩ እናም በአብ፣ እና ሀበጸጋና በእውነት በተሞላው በወልድ፣ እና ስለአብና ወልድ ምስክር በሚሰጠው ለበመንፈስ ቅዱስ ስም ሐእንዳጠምቅ ትእዛዝም ሰጠኝ።
፲፪ እና እንዲህ ሆነ ሔኖክ ከከነዓን ህዝቦች በስተቀር ህዝቦችን በሙሉ ንስሀ እንዲገቡ መጥራትን ቀጠለ።
፲፫ እና የሔኖክ ሀእምነት ታላቅ ስለነበረ የእግዚአብሔር ህዝቦችን መራ፣ እና ጠላቶቻቸውም ለጦርነት መጡባቸውም፣ የጌታን ቃል ተናገረ፣ እና መሬትም ተንቀጠቀጠች፣ እና ተራሮችም በትእዛዙ ምክንያት ለሸሹ፤ እና ሐየወንዝ ውሀዎችም መንገዳቸውን ቀየሩ፤ እና የአምበሶችም ግሳት ከዱር ይሰማ ነበር፤ እና የሔኖክም ቃላት በጣም መሀይለኛ ስለነበሩና እግዚአብሔር የሰጠው ቋንቋ በጣም ሀይለኛ ስለነበር ሁሉም ህዝቦች ታላቅ ፍርሀት ነበረባቸው።
፲፬ ከጥልቅ ባህር ውስጥም የደረቀ መሬትም ወጣ፣ እና የእግዚአብሔር ህዝብ ጠላቶች ፍርሀትም ታላቅ ስለነበር ሸሹ እና በሩቅም ቆሙ እና ከባህር ውስጥ ወደ ወጣው መሬትም ሄዱ።
፲፭ ደግሞም የሀገሩ ሀግዙፍ ሰዎችም በሩቅ ቆሙ፤ እናም ከእግዚአብሔር ጋር በተዋጉት ህዝቦች ሁሉ ላይ እርግማን መጣ።
፲፮ እና ከዚያም ጊዜ በኋላ በመካከላቸው ጦርነቶችና ደም ማፋሰስ ነበር፤ ነገር ግን ጌታ መጣ እና ከህዝቡም ጋር ኖረ፣ እና እነርሱም በፅድቅ ኖሩ።
፲፯ በህዝቡ ላይ ያረፈው የጌታ ክብር ታላቅ ስለነበር፣ የእግዚአብሔርም ሀፍርሀት በሁሉም ህዝብ ላይ ነበር። እግዚአብሔርም ምድሪቱን ለባረከ፣ እና በተራራውና በታላቅ ስፍራዎችም ተባረኩ፣ እና በለጸጉም።
፲፰ እነርሱ ሀአንድ ልብ እና አንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ እና በጽድቅም ስለኖሩ፣ ጌታ ህዝቡን ለፅዮን ብሎ ጠራቸው፤ እና በመካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም።
፲፱ እና ሔኖክም በጽድቅ ለእግዚአብሔር ህዝብ መሰበክን ቀጠለ። በእርሱም ቀናት እንዲህ ሆነ፣ የቅድስና፣ እንዲሁም ፅዮን፣ ተብሎ የተጠራ ከተማም መሰረተ።
፳ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ከጌታ ጋር ተነጋገረ፤ እና ለጌታም እንዲህ አለው፥ ሀፅዮን በእርግጥም በደህንነት ለዘለአለም ትኖራለች። ነገር ግን ጌታ ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ ፅዮንን ባርኬአለሁ፣ የሚቀሩትን ህዝቦች ግን ረግሜአለሁ።
፳፩ እንዲህም ሆነ ጌታ ለሔኖክ የምድርን ነዋሪዎችን በሙሉ አሳየው፤ ፅዮን ከጊዜ በኋላ ወደ ሰማይ ሀእንደምትወሰድም ተመለከተ አስተዋለም። እና ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ እነሆ ለዘለአለም መኖሪያዬ ትሆናለች።
፳፪ ሔኖክም ደግሞም የቀሩትን የአዳም ልጆች የሆኑትን ህዝቦች አየ፤ እና እነርሱም ከቃየን ዘሮች በስተቀር ሁሉም የአዳም ልጆች ድብልቆች ነበሩ፣ የቃየን ዘሮች ሀጥቁር ነበሩ፣ እና ከእነርሱ መካከል ስፍራ አልነበራቸውምና።
፳፫ ከዚያም በኋላ ፅዮን ወደ ሀሰማይ ተወሰደች፣ እናም የምድርም ሀገሮች ለሁሉም ከእርሱ ፊት እንደነበሩ ሔኖክ ሐአየ አስተዋለም፤
፳፬ እና በትውልድ ላይ ትውልድም መጣ፤ እና ሔኖክም ሀከፍ ብሎ ወደላይ ተነስቶ ነበር፣ እንዲሁም በአብና በሰው ልጅ እቅፍ ውስጥም ነበር፤ እና እነሆ፣ የሰይጣን ሃይል በምድር ፊት ሁሉ ላይ ነበር።
፳፭ እና መላእክት ከሰማይ ሲወርዱም አየ፤ እና ታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማ፥ በምድር ለሚኖሩት ወዮ፣ ወዮ።
፳፮ ሰይጣንንም አየ፤ እና በእጁም ታላቅ ሀሰንሰለት ነበረው፣ እና ይህም ምድርን በሙሉ ለበጭለማ ሸፈነ፤ እርሱም ቀና ብሎ ሳቀ፣ እና የእርሱም ሐመላእክት ተደሰቱ።
፳፯ እና ሔኖክ ሀመላእክት የአብና ወልድ ለምስክር ይዘው ከሰማይ ሲወርዱ አየ፤ እና መንፈስ ቅዱስ በብዙዎች ላይ አረፈ፣ እና እነርሱም በሰማይ ሀይሎች ወደ ፅዮን አረጉ።
፳፰ እንዲህም ሆነ እግዚአብሔር የቀሩትን ህዝቦች ተመለከተ፣ እናም አለቀሰ፤ ስለዚህም ሔኖክ እንዲህ ብሎ መሰከረ፥ ለምንድን ነው ሰማያት የሚያለቅሱት፣ እና እምባቸውን እንደ ዝናብ በተራራው ላይ እንደሚፈስ የሚያደርጉት?
፳፱ እና ሔኖክ ለጌታ እንዲህ አለ፥ ቅዱስ እና ከዘለአለም ሁሉ እስከ ዘለአለም ሆነህ፣ ለምንድን ነው ሀየምታለቅሰው?
፴ እና የዚህን ምድር፣ አዎን፣ እንደዚህ አይነት ሚልዮን ሀምድሮችን፣ ታናሽ መጠንን ሰው ለመቁጠር የሚችሉ ቢሆንም፣ አንተ ለለፈጠርካቸው የመቆጠሪያ መጀመሪያም አይሆንም፤ እና መጋረጃህ አሁንም ተወጥሯል፤ ነገር ግን አንተ እዚህ አለህ፣ እና እቅፍህም እዚህ አለ፤ ደግሞም አንተ ጻድቅ ነህ፤ ለዘለአለምም ሩህሩህና ደግ ነህ፤
፴፩ እና ከዘለአለም እስከ ዘለአለም፣ ከፍጥረታትህ ሁሉ፣ ወደ እቅፍህም ፅዮንን ወስደሀል፤ እና የዙፋንህ ነዋሪዎችም ሀከሰላም፣ ለከፍትህ፣ እና ሐከእውነት ሌላ ነዋሪዎች የላቸውም፤ ምህረት በፊት ለፊትህ ይሄዳል እና መጨረሻ የለውም፤ አንተ ለማልቀስ እንዴት ትችላለህ?
፴፪ ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ እነዚህ ወንድሞችህን እይ፤ እነርሱ ሀየእጅህ ስራዎች ናቸው፣ እና በፈጠርኳቸው ቀንም ለእውቀታቸውን ሰጠኋቸው፤ እና በዔደን ገነትም ለሰው ሐነጻ ምርጫውን ሰጠሁት።
፴፫ እና ለወንድሞችህም ይህን ብያለሁ፣ እና ደግሞም እርስ በርስ እንዲዋደዱ፣ እና እኔ አባታቸውን ይመርጡ ዘንድ ትእዛዝን ሰጠኋቸው፤ ነገር ግን እነሆ፣ እነርሱ ሀፍቅር የላቸውም፣ እና የራሳቸውንም ደም ይጠላሉ፤
፴፬ ሀየእሳት አይነት ቁጣዬም እነርሱ ላይ ተቀጣጥሏል፤ እና በእነርሱም ላይ ቁጣዬ ታላቅ ስለሆነ፣ በቅያሜዬም ለየጥፋት ውሀ እልክባቸዋለሁ፣ ጥብቅ ቁጣዬም በእነርሱ ላይ ተቀጣጠላለችና።
፴፭ እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም የቅድስና ሀሰው ነው፤ የምክር ሰውም ስሜ ነው፤ እና መጨረሻ የሌለውና ዘለአለማዊም ደግሞ ለስሜ ነው።
፴፮ ስለዚህ፣ እጆቼን እዘረጋለሁ እና የፈጠርኳቸውን ፍጥረታት ሁሉ ልይዛቸውም እችላለሁ፤ እና ደግሞም ሀአይኔ ሊበሳቸው ይችላል፣ እና በእጆቼ ከሰራኋቸው ፍጥረታት ሁሉ ከወንድሞችህ ውስጥ እንዳለው እንደእነዚህ አይነት ለጥፋቶች አልነበሩም።
፴፯ ነገር ግን እነሆ፣ ኃጢአታቸው በአባቶቻቸው ጭንቅላት ላይ ይሆናል፤ ሰይጣንም አባታቸው ይሆናል፣ ጣርም እጣቸው ይሆናል፤ እናም ሰማያትም በሙሉ ለእነርሱ፣ እንዲሁም በእጆቼ ለሰራኋቸው በሙሉ፣ ያለቅሳሉ፤ ስለዚህ እነዚህ እንደሚሰቃዩ ሲያዩ፣ ሰማያት አያለቅሱም?
፴፰ ነገር ግን እነሆ፣ እነዚህ በአይንህ ያየሀቸውም በጎርፍ ይጠፋሉ፤ እና እነሆ፣ እኔ እዘጋቸዋለሁ፤ ሀእስር ቤት ለእነርሱ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
፴፱ እና ሀያ የመረጥኩትም በፊቴ ለምኗል። ስለዚህ፣ ለኃጢአታቸው ተሰቃየ፤ ንስሀ ከገቡም በዚያ ቀን ለየመረጥኩት ወደ እኔ ይመለሳሉ፣ እና እሰከዚያም ቀን ድረስ ሐበስቃይ ውስጥም ይሆናሉ፤
፵ ስለዚህ፣ ለዚህም ሰማያት፣ አዎን፣ እና በእጆቼ የሰራኋቸውም ሁሉ ያለቅሳሉ።
፵፩ እንዲህም ሆነ ጌታ ሔኖክን አነጋገረው፣ እና ስለሰው ልጆች ድርጊቶች ሁሉም ነገረው፤ ስለዚህ ሔኖክ አወቀ፣ እና ጥፋታቸውንና ስቃያቸውን አየ፣ እና አለቀሰ እናም ክንዶቹን ዘረጋ፣ ሀልቡም እንደ ዘለአለም ተጉረበረበ፤ እና አንጀቱም በጥልቅ ተነካ፤ እናም ዘለአለምም ተንቀጠቀች።
፵፪ ሔኖክም ሀኖህንና ለቤተሰቡን አየ፤ የኖህ ልጆች ዘሮችም በጊዜያዊ ደህንነት ይድናሉ፤
፵፫ ስለዚህ ሔኖክ ኖህ ሀመርከብን እንደሰራም አየ፤ እና ጌታም ፈገግ አለበት፣ እና በእጁም ያዘው፤ ነገር ግን በቀሩት ጥፋተኞች ላይ ጎርፎቹ መጡ እና አጥለቀለቋቸው።
፵፬ ሔኖክም ይህን ተመለከተ፣ የነፍስ መራራነት ተሰማው፣ እና ለወንድሞቹ በማልቀስ ለሰማያት እንዲህ አለ፥ ለመጽናናት ሀእምቢ እላለሁ፤ እግዚአብሔር ግን ሔኖክን አለው፥ ልብህን አንሳ፣ ተደሰትም፤ እና ተመልከት።
፵፭ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ተመለከተ፤ እና ከኖህ ጀምሮ የምድርን ቤተሰቦች አየ፤ እና ለጌታ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ የጌታ ቀን መቼ ይመጣል? የሚያለቅሱት ሁሉ ሀእንዲቀደሱና ዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድ፣ የጻድቁ ደምስ መቼ ነው የሚፈሰው?
፵፮ ጌታም እንዲህ አለ፥ ይህም ሀበመካከለኛው ዘመን፣ በጥፋትና በበቀል ቀናት ነው።
፵፯ እና እነሆ፣ ሔኖክም የሰው ልጅ በስጋ የሚመጣበትን ቀን አየ፤ እና መንፈሱም በመደሰት እንዲህ አለ፥ ጻድቁ ወደላይ ተነስቷል፣ እናም ከምድር መሰረት ጀምሮም ሀበጉ ተገድሏል፤ እና በእምነትም በኩል በአብ እቅፍ ውስጥ ነኝ፣ እና እነሆ፣ ለፅዮንም ከእኔ ጋር ነች።
፵፰ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ሀምድርን ተመለከተ፤ እና ከጥልቁም እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማ፥ ወዮ፣ ለእኔም ለሰው እናት ወዮለኝ፤ በልጆቼ መጥፎነት ምክንያት አሞኛል፣ ደክሞኛልም። መቼ ለአርፋለሁ፣ እና ከእኔ ውስጥ ከወጡት ሐእድፍ እነጻለሁን? አርፍስ ዘንድ ፈጣሪዬ መቼ ይቀድሰኛል፣ ለዘመንም በፅድቅ በፊቴ መቼ ይኖራል?
፵፱ ሔኖክ ምድር ስታለቅስ ሲሰማም አለቀሰ፣ እና ለጌታም እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ ጌታ ሆይ፣ በምድር ላይ ርህራሄ አይኖርህምን? የኖህንን ልጆችንስ አትባርክም?
፶ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ወደጌታ መጮሁን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥ ጌታ ሆይ፣ በአንድያ ልጅህ፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስም ለኖህና ለዘሩ ርህራሄ ይኖርህ ዘንድ፣ መሬትም በመጥፊያው ውሀ ደግሞም እንዳትሸፈን ዘንድ እጠይቅሀለሁ።
፶፩ ጌታም ይህን ሊከለክለው አልቻለም፤ ከሔኖክ ጋር ቃል ገባ፣ እና ከእርሱም ጋር ቃለ መሀላ ሀጎርፉን እንደሚያቆም፤ የኖህ ልጆችንም እንደሚጠራቸው ማለለት።
፶፪ ከዚያም ምድር እስካለች ድረስ የእርሱ ሀየሚቀሩት ዘሮችም በሁሉም ህዝቦች መካከል ይገኙ ዘንድ የማይቀየር አዋጅን ሰደደ።
፶፫ እና ጌታም እንዲህ አለ፥ በዘሩ በኩል ሀመሲህ የሚመጣበት የተባረከ ነው፤ ምክንያቱም እንዳለው—እኔ የፅዮን ለንጉስ፣ እንደ ዘለአለም ሰፊ የሆነው የሰማይ ሐአለት፣ መሲህ ነኝ፣ እና ማንም በበሩ ገብተው ወደ እኔ መየሚወጡትም አይወድቁም፤ ስለዚህ፣ የተናገርኩባቸውም የተባረኩ ናቸው፣ ከዘለአለም ደስታ ሠመዝሙር ጋር በደስታ ይመጣሉና።
፶፬ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ወደጌታ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ የሰው ልጅ በስጋ ሲመጣ፣ ምድርም ታርፋለችን? እነዚህን ነገሮች እንድታሳየኝ እለምንሀለሁ።
፶፭ ጌታም ለሔኖክ አለው፣ ተመልከት፣ እና ተመለከተ፣ እና ሀየሰው ልጅን እንደ ሰው ለበመስቀል ላይ ሲሰቀልም አየ እና ተመለከተ።
፶፮ የደመቀ ድምጽንም ሰማ፤ እና ሰማያት ተሸፍነው ነበር፤ እና የእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ አዘኑ፤ ምድርም ሀአቃሰተች፤ ድንጋዮችም ተሰነጠቁ፤ ቅዱሳንም ለተነሱ፣ እና በሰው ልጅ ሐቀኝ እጅም በክብር መዘውዶች ተጫኑ።
፶፯ እና ሀበእስር ቤት የነበሩትም ሁሉ ለመንፈሶች መጡ፣ እና በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ቆሙ፤ እና የቀሩትም እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በጭለማ ሰንሰለቶች ታሰሩ።
፶፰ ሔኖክም እንደገና አለቀሰ እና ለጌታ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ ምድር መቼ ታርፋለች?
፶፱ ሔኖክም የሰው ልጅ ወደአብ ሲያርግ ተመለከተ፤ እና ወደ ጌታም እንዲህ ብሎ ጠራ፥ በምድር እንደገና አትመጣምን? አምላክም እስከሆንክ ድረስ፣ እና አውቅሀለሁ፣ እና ምለህልኛል፣ እና በአንድያ ልጅህ ስም እጠይቅህ ዘንድ አዝዘኸኛል፤ ሰርተኸኛል፣ እና ለዘውድህ መብትም በራሴ ሳይሆን በጸጋህ ሰጥተኸኝ፤ ስለዚህ፣ ወደ ምድር እንደገና የምትመለስ እንዳልሆነም እጠይቅሃለሁ።
፷ እና ጌታ ለሔኖክ እንዲህ አለ፥ እንደምኖርም፣ እንዲህም ሀበመጨረሻዎቹ ቀናት፣ መጥፎነትንና በበቀልም ቀናት፣ የኖህ ልጆችን በሚመለከት ቃለ መሀላ ላንተ የገባሁትን ለማሟላት ተመልሼ እመጣለሁ፤
፷፩ ምድር ሀየምታርፍበትም ቀን ይመጣል፣ ነገር ግን ከዚያ ቀን በፊት ሰማያት ለይጠቁራሉ፣ የጭለማም ሐመጋረጃ ምድርን ይሸፍናል፤ እና ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፣ ዳግም በምድርም፤ በሰው ልጆችም መካከልም ታላቅ ስቃይ ይኖራል፣ ነገር ግን ህዝቤን መአተርፋቸዋለሁ፤
፷፪ እና ሀፅድቅን ከሰማያት እሰዳለሁ፤ እና ስለ አንድያ ልጄ፣ ከሙታን ለትንሳኤውን፣ አዎን፣ እና ስለሁሉም ሰዎች ከሞት ስለመነሳት ሐእንዲመሰክርም መእውነትን ሠከምድር እልካለሁ፤ እና እንደ ጥፋት ውሀ ፅድቅና እውነት ምድርን አንድታጸዳት፣ የእኔ ተመራጮችን ከምድር አራት ማእዘናት ወደ አዘጋጀሁት ስፍራ፣ ቅዱስ ከተማ፣ ወገባቸውን እንዲታጠቁ እና ለእኔ መመለሻ ወደፊት ይጠብቁ ዘንድ ረእንዲሰበሰቡ አደርጋለሁ፤ በዚያም ድንኳኔም ይገኛልና፣ እና ይህችም ፅዮን፣ ሰአዲስቷ ኢየሩሳሌም ተብላ ትጠራለች።
፷፫ ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ አንተና ሀከተማህ ሁሉ በዚያ ትገናኛቸዋለህ፣ እናም በእቅፋችንም እንቀበላቸዋለን፣ እነርሱም ያዩናል፤ እና አንገታቸውን እናቅፋለን፣ እና እነርሱም አንገታችንን ያቅፋሉ፣ እና እንሳሳማለን፤
፷፬ እኔም በዚያ መኖሪያዬ ይሆናል፣ እና ከፈጠርኳቸው ሁሉ ውስጥ የምትመጣው ፅዮን ትሆናለች፤ እና ለአንድ ሀሺ አመታትም ምድር ለታርፋለች።
፷፭ እንዲህም ሆነ ሔኖክ በኋለኛዎቹ ቀናት ለአንድ ሺህ አመታት በፅድቅ በምድር ለመኖር የሰው ልጅ ሀየሚመጣበትን ቀናት አየ፤
፷፮ ከዚያ ጊዜ በፊት ግን ከመጥፎዎቹ መካከል ታላቅ ስቃይን አየ፤ እና ባህርም እንደተቸገረ አየ፣ እና በመጥፎው ላይ የሚመጣውን የሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርን ሀፍርድ በመፍራት ወደፊት እየተመለከቱ የሰዎች ልብ ለሲወድቁባቸው ተመለከተ።
፷፯ ጌታም ለሔኖክ ሁሉንም ነገሮች፣ እንዲሁም እስከ አለም መጨረሻ ድረስ አሳየው፤ እና የፅድቅን ቀን፣ የቤዛነታቸውንም ሰአት አየ፣ እና ሀየደስታ ሙላትን ተቀበለ፤
፷፰ እና ሀየፅዮን ቀናት ሁሉ፣ በሔኖክ ቀናት፣ ሶስት መቶ ስልሳ አምስት ነበሩ።
፷፱ እና ሔኖክና ሁሉም ህዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ሀተራመዱ፣ እና እርሱም በፅዮን መካከል ኖረ፤ እንዲህም ሆነ ፅዮንም አልነበረችም፣ እግዚአብሔር ወደ እቅፉ ተቀብሏታልና፤ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፅዮን ጠፋች የሚል አባባል ነበር።